TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
ይዘት
የልጥፍ ይዘት
ብዙዎቻችን ስኬትን የምንለካው በማህበረሰቡ ሚዛን ብቻ ነው። ዲግሪ መያዝ፣ ሥራ መያዝ ወይም ትዳር መመስረት የሕይወት ደረጃዎች እንጂ የግል ማንነት ዕድገት ማረጋገጫዎች አይደሉም። እውነተኛ ዕድገት የሚለካው በውስጣዊ ማንነትህ፣ በዓላማህና ለዓለም በምትሰጠው እሴት ነው። ጠዋት ወጥቶ ማታ መግባት፣ ዕዳ መክፈልና በልማድ መመራት ብቻ ሕይወትን ባዶ ያደርጋታል። ወጣቱ ትውልድ ራሱን "ለምንድነው የምኖረው?" ብሎ መጠየቅ አለበት። ብስለት የሚመጣው ዕድሜ ሲጨምር ሳይሆን ለራስህ ሕይወትና ለምትወስዳቸው ውሳኔዎች ሙሉ ኃላፊነት ስትወስድ ነው። ዕድሜህ ስለጨመረ ብቻ እያደግክ ነው ማለት አይደለም። ዛሬ ካለህበት ሁኔታ ነገ በተሻለ አስተሳሰብና ሰብዕና ለመገኘት ጣር። ኑሮን መኖር ብቻ ሳይሆን ሕይወትን በጥበብ መምራትን ተለማመድ። 🤟ማያ አንጀሉ🧘♀