@ebcnewsnow · Post #53539 · 04/14/2026, 05:48 PM
“ከሁለት፣ ሦስት ዓመት በፊት ለአያሌ መንግሥታት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው ይችላል፤ በዚህ ውስጥ ሚና አልባ ሆነን ከቆየን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል የሚል አቋም እናነሣ ነበር። በወቅቱ ምንም ነገር ስላልነበረ እምብዛም ተቀባይነት አልነበረውም። አሁን ግን ብዙዎች እያመኑበት ያለ ጉዳይ ነው። ከባህር መራቅ የባህርን ወይም የየብስን ትራንስፖርት ወይም የአየርን ትራንስፖርት ‘ግዴለም፤ በቀላሉ አገኘዋለሁ’ ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#SeaAccess
Hashtags