TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Python Заметки

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Најди сличен содржај

Изворен канал @pythonotes · Post #387 · 16 дек.

Доделал свой старый проект - инструмент для восстановления ориентации объектов в пространстве на основе опорных компонентов. Работает в Autdesk Maya. Основные возможности. ▫️просто выделите опорные (обычно симметричные или осевые) компоненты и укажите куда их ориентировать ▫️ операции для доворотов и центрирования ▫️ восстановление исходного расположения после восстановления трансформаций ▫️работает как с одним объектом так и с группой ▫️ открытый API для интеграций с другими инструментами и автоматизаций Все действия происходят с векторами и матрицами объектов, поэтому всё достаточно быстро. Где может применяться? 🪑Нередкая проблема - собрали лейаут сцены и зафризили, или даже смержили всю геометрию в один большой меш. Требуется вернуть все объекты в "Т-позу", сохранить отдельно и расставить обратно в сцену, но с правильными трансформациями. Инструмент как раз заточен под такую работу. 🌲Заскатерили инстансы и потом конвертнули в меш. Нужно обратно преобразовать в инстансы. Здесь поможет API который восстановит положение каждого инстанса в нуле и вернёт его обратно в исходное положение, но с правильными трансформациями. Останется забрать матрицу с объекта для инстанса. Быстрое превью функционала: ▶️https://www.youtube.com/watch?v=JvlHa0NEXu8 Документация и код здесь: 🌍https://github.com/paulwinex/pw-maya-restore-orient #release#source

Резултати

Пронајдени 9 слични објави

Пребарај: #medemer

当前筛选 #medemer清除筛选

የመደመር አንቀፅ "በሀገራችን በዓመት ውስጥ መሬት ሳያመርት የሚያርፍበት ጊዜ ከፍተኛ ከነበረበት በበጋ ግብርና ልማት ልምምድ አማካኝነት የጊዜ ምልከታችንን በመቀየር የምርት ለውጥ አምጥተናል። በዚህም በዐሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የያዝነውን ዋና ዋና የምግብ ፍጆታዎችን በሀገር ውስጥ በማምረትና ከውጭ የሚገባውን በመተካት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አስመዝግበናል።" የመደመር መንግሥት ገጽ 170 Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#medemer#EBC

ሀገራችንን የዘመናዊ ከተሞች ባለቤት የማድረግ ጉዞ በመርሕ መመራት አለበት። ነባር ትንንሽ ከተሞችን ማዘመን፣ እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የታጠቁ አዳዲስ ከተሞችን መገንባት ትኩረት ይፈልጋል። በነባር ከተሞቻችን የተዘረጉ ጊዜ ያለፈባቸውም ይሁኑ ያልተዘረጉ መሠረተ ልማቶች፣ በዘመናዊና የወደፊቱን ታሳቢ ባደረጉ መሠረተ ልማቶች መለወጥ ይኖርባቸዋል። የአዳዲስ ከተሞች ምሥረታ የሚከናወነው ደግሞ እያንዳንዱ የዘመናዊ ከተማ መገለጫዎች ከጅምሩ ታሳቢ ተደርገው ሊሆን ይገባል። የመደመር አንቀፅ 234 Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#EBC#Medemer

የመደመር አንቀጽ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ብዙ ዓምዶች አሉት። አደጋን አስቀድሞ አይቶ ማስወገድ ወይም መከላከል አንዱ ነው። አደጋው ከመጣም አደጋውን ተቋቁሞ ማሳለፍ ሌላው ነው። አደጋው ጉዳት ካደረሰም በቶሎ ለማገገም የሚችል ኢኮኖሚን መገንባት ደግሞ ሌላው የማይበገር ኢኮኖሚ ጠባይ ነው። የመደመር መንግሥት ኢኮኖሚውን የሚፈትኑ አደጋዎችን ማስጠም የሚችል ነው። ተለዋዋጭ ነገሮችን ይላመዳል፤ እንዲሁም ከአደጋ ቶሎ የሚያገግም ኢኮኖሚ መገንባት ትልቁ ትኩረቱና መገለጫው ነው። የመደመር መንግሥት ገጽ 147 Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#medemer#EBC

"የሕዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ ፖለቲካ ውስጥ፣ ሐሳብ የሕዝብ ፍላጎትን ይወክላል። ፖለቲከኞች የሕዝብን ይሁንታ የሚያገኙት የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት በሚያቀርቧቸው አጀንዳዎች ነው። ሕዝብም ከሚቀርቡት አጀንዳዎች መካከል ፍላጎቱን የተሻለ የሚያሟላ ለሚለው ድጋፍ ይሰጣል። በዚህ ዓይነት የሐሳብ ገበያ ውስጥ፣ ከፖለቲካ ገበያ በተለየ ድጋፍና ይሁንታ፣ ትብብርና ፉክክር እንዲሁም ታማኝነት በሐሳብ ላይ በሚኖር ስምምነትና እምነት ይመሰረታል። የሐሳብ ገበያ ሐሳቦቹ በተግባር ሊያመጡት ከሚችሉትና ያመጡት ተብሎ ከሚታሰበው ውጤት አንጻር ተመዝነው የሚሸለሙበት ነው።" የመደመር አንቀፅ ገፅ 381 Ethiopian Broadcasting Corporation #Medemer#EBC#Ethiopia

የመደመር አንቀፅ በአዲሱ ዘመን ዕሳቤ ከተሞች ለመኖሪያ ምቹ፣ ለንግድ ማሣለጫ፣ ለፈጠራና ለቢዝነስ መጀመሪያና መጎልበቻ፣ ለቱሪስት መዳረሻ ሆነው እንዲቆረቆሩ ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲሁም ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር የተሣሠሩና ገጠሩን ከከተማው በማቀናጀት የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን አስቻይ እንዲሆኑ ሊሠራ ይገባል። ለዚህም አዲስ አበባና ሌሎች መካከለኛና አነስተኛ ከተሞችን የመሠረተ ልማት ችግሮቻቸውን መፍታት ይገባል። ያሉባቸውን የዕቅድና የአስተዳደር ፈተናዎች ማቃለል ያስፈልጋል። የመጪውን ጊዜ ተግዳሮቶች ለመፍታትና ለመሻገር ደግሞ የላቀ ሐሳብ፣ ፈጠራና ፍጥነት ያለው ሥራ ይጠይቃል። የመደመር መንግስት 234 Ethiopian Broadcasting Corporation #Medemer#Ethiopia#EBC#addisababa

የመደመር አንቀፅ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማስፋፋት ባለፉት ዓመታት ሰፊ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚቀርበው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትም ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። የሕዳሴ የኃይል ማመንጫን ጨምሮ ሌሎች በጅምር ያሉና በሚገባ አገልግሎት እየሰጡ ያልነበሩ ማመንጫዎችን ወደ መሥመር ለማስገባት ተችሏል፡፡ በዚህም ሀገራችን ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚያስፈልጋትን የኃይል አቅርቦት በሚገባ መሸፈን ችለናል፡፡ ካለን ዕምቅ ዐቅም አንጻር ሌሎች ብዙ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን የምንቀርጽና የምንተገብር ቢሆንም፣ የኃይል አቅርቦት ግን ጎዶሎ ሆኖ አምራችነትን ከሚጎትቱ ጉዳዮች መካከል መሆኑ አብቅቷል፡፡ በሌላ በኩል ግን የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ከማድረግና የኃይል መቆራረጥን ከመቅረፍ አኳያ ቀላል የማይባል የማሻሻያ ሥራ ይጠብቀናል፡፡ የመደመር መንግሥት ገፅ 206 Ethiopian Broadcasting Corporation #Medemer#GERD#Ethiopia

የመደመር አንቀፅ አምራች ኢንዱስትሪው ለአንድ ሀገር አጠቃላይ የውስጥ ምርት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል ሲባል በቀጥታ ከሚኖረው አስተዋጽዖ በላይ ነው፡፡ በሌሎች ዘርፎች ላይ በሚኖረው ተጽዕኖ የሚያበረክተውም አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው። የተሻለ ገቢ ያለው ማኅበረሰብ ለመፍጠር ለሚደረገው ርብርብም ዋነኛው የትኩረት ዘርፍ የአምራች ዘርፍ ነው፡፡ አምራች ኢንዱስትሪውን ወደ ከፍታ የማምጣትና የማበልጸግ ጉዳይ፣ ከኢኮኖሚና ከማኅበራዊ ጥቅሙ ባለፈ፣ ደኅንነትንና ሉዓላዊነትን ከማስከበር አንጻርም ሚናው ከፍተኛ ነው። በሌሎች ሀገራት አምራች ኢንዱስትሪ ላይ ጥገኛ ሆኖ፣ ራስን ሳይችሉ፣ ሉዓላዊ ሀገርነን ማለት ቀልድ ነው፡፡ የመደመር መንግሥት ገፅ 197 Ethiopian Broadcasting Corporation #IPDC#Ethiopia#industry#Medemer

ኢትዮጵያ በአፍሪካና በጣሊያን መካከል የትብብር ድልድይ ****************** ኢትዮጵያ በመደመር መንፈስ 2ኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች:: እንኳን ደህና መጣችሁ! #Ethiopia#Africa#Italy#AfricaItalySummit#PMOEthiopia#Medemer

የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሉዓላዊነት ጉዞና የብሪክስ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ ************** ኢትዮጵያ ከውስጥ ግንባታ እስከ ዓለም አቀፍ መሪነት የምታደርገው የሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ጉዞ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየታየ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማና የገጠር ትስስርን በማጠናከር የዜጎችን የኑሮ ዘይቤ ከመቀየሩ ባለፈ የ"መደመር" ፍልስፍናን በተግባር እያሳየ የሚገኝ ስኬት ነው፡፡ በጤናው ዘርፍም በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አማካኝነት የተጀመረው የሀገር ውስጥ መድኃኒት ምርት የውጭ ጥገኝነትን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ተስፋ ሆኗል፡፡ በዲፕሎማሲው ረገድ ኢትዮጵያ የብሪክስ+ አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከማሳደጉም በላይ የባሕር በር ጥያቄዋንና የንግድ ጥቅሟን ለማስከበር ትልቅ ስትራቴጂካዊ አቅም ፈጥሮላታል፡፡ ይህ ሁሉ የብልፅግና ሰንሰለት ዘላቂ የሚሆነው በሰለጠነ የፖለቲካ ተሳትፎና በዴሞክራሲያዊ ግንባታ በመሆኑ፣ እየተቃረበ ለሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ በመውሰድ በሐሳብ ውድድር ላይ የተመሰረተች ሀገርን ለመገንባት የሁላችንም ሉዓላዊ መብትና ኃላፊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በጀመረችው ሁለንተናዊ ንቅናቄ ወደ ተሟላ ሉዓላዊነትና ብልፅግና እያመራች በመሆኗ በዚህ ታሪካዊ ጉዞ ላይ ሁላችንም አሻራችንን እናሳርፍ፡፡ ሙሉ ትንታኔውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://www.ebc.et/Home/NewsDetails?NewsId=4831 በሰለሞን ገዳ #Ethiopia#Sovereignty#BRICSPlus#EconomicGrowth#Medemer#Development#AfricaRising