TGINSIGHT CHAT
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
@Ethiopian_Orthodox
Educationበዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
ገጽ 1 ከ 85 · 1,013 ልጥፎች
ታትሟል ኤፕሪ 30
@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
ታትሟል ኤፕሪ 30
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ በምድር መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ በመከራም ውስጥ ሁኖ በባሕርም ሆነ በየብስ ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለሁ ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፡፡ ከዚህ በኋላ ራሱን ዘንበል አድርጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ፡፡ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሥጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደ ሀገሩ ልዳም ወሰዱት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው በውስጥዋ አኖሩት ከእርሱም ቍጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ፡፡ የሰማዕቱ ረድኤትና በረከት አይለየን! ©ስንክሳር @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
ታትሟል ኤፕሪ 30
ሚያዝያ ፳፫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ሚያዝያ ሃያ ሦስት በዚህች ቀን ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የምስክርነት ፍጻሜ ሆነ። የዚህም ቅዱስ አባቱ መስፍን ነው ስሙም አንስጣስዮስ ይባላል ከቀጰዶቅያ አገር ነው የእናቱም ስም ቴዎብስታ ይባላል ከፍልስጥዔም አገር ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ አረፈ። ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሔደ፡፡ ንጉሡም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው። ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው። ከዚህ በኋላ በንጉሥ ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። ንጉሡም አባበለው ብዙ ቃልኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም። ለመስማት እንኳ የሚያስጨንቅ ሥቃይን አሠቃየው ጌታችን ግን ያጸናዋል ቍስሉንም ያድነዋል ሦስት ጊዜም እንደ ሚሞት እርሱም እንደሚአሰነሣው በአራተኛውም የምስክርነት አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው። ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ በተጋድሎና መከራ በመቀበልም ጽኑዕ በሆነ ሥቃይም ሰባት ዓመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው። ንጉሡም ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ታላቅ ሥራየኛ አመጣ እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ መልቶ አስማት ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው። ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር። ቅዱሱም ያንን ጽዋ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም። ያ መሠርይም በክብር ባለቤት በጌታ ኢየሱስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ። ከእርሱም ጋራ ሌሎች ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሙተው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ ቍጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ ነፍስ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ። ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን አሉት። በዚያን ጊዜ ጸለየ እንዳሉትም አደረጋቸው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ቍጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ በጌታችን አመኑ። ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት። አቃጥለው አሳርረውም ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት። ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው። ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ስም ሰበከ ቁጥር የሌላቸው አሕዛብ አይተው አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ነገሥታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታሥነሣ አምላክህ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናውቃለን በእርሱም እናምናለን አሉት። ቅዱሱም ጸለየ ከጉድጓድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ጎልማሶችንም አስነሣላቸው እነዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ስም አስተማሩ የገሀነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው አረፉ። ከሀድያን ነገሥታት ግን ሙታንን ያስነሣህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ። ከዚያም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሣ ከአንዲት ድኃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እርሷም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሔርም መልአክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ ማዕድን አቀረበላት። የዚያች መበለትም የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ። ያቺም መበለት በተመለሰች ጊዜ የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ስለ ማዕዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደእኔ መጣ አለች። ቅዱሱም እኔ አምላክ አይደለሁም የአምላክ ባሪያ ነኝ እንጂ አላት። እርሷም እንዲህ ብላ ለመነችው የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ አለምንሃለሁ። ዕውር ደንቆሮ ዲዳ ጐባጣ የሆነ ልጅ አለኝና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ። ስለ ጌታችን እምነትም አስተማራትና በመስቀል ምልክት አማተበው ያንጊዜም አየ። ቅዱሱም በሌላ ጊዜ እንዲሰማ እንዲናገርና እንዲሔድ እንዲአገለግለኝም እኔ እሻለሁ አላት። በዚያን ጊዜ ንጉሡ በአገሩ ሜዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያቺን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለ እርሷም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእርሷ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቷ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት። ንጉሡም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አሰገረፈው በመንኰራኩርም አበራዩት ሙቶም ከከተማ ውጭ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመለሰ ንጉሡም አይቶ ደነገጠ ስለ ሕይወቱም አደነቀ። ከዚህም በኋላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግሥቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስም እየዘበተበት ነገ በጥዋት ለአማልክቶችህ መሥዋዕትን አቀርባለሁ አንተም ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሠዋ እንዲአዩ አለው፡፡ ንጉሡም ዕውነት የሚሠዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግሥቱም እልፍኝ አስገብቶ አሳደረው፡፡ ለጸሎትም ተነሣ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለስክንድርያ ንግሥት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጒምላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ጊዜ የሆነውን ሁሉ ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ ትምህርቱም በልቡዋ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች፡፡ በማግሥቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሠዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ ዐዋጅ ነጋሪ ዞረ የቤቷን ምሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ ዕውነት መስሏት እጅግ እያዘነች ልጅዋን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም በአያት ጊዜ ፈገግ አለ ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት ከዚያም ልጅዋን ጠርቶ ወደ አጵሎን ሒድ ወደእኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው አለው፡፡ ያን ጊዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳዘዘው ወደ ጣዖቱ ቦታ ሒዶ አዘዘው፡፡ በጣዖቱ ያደረ ያ ርኵስ መንፈስም ከማደሪያው ወጥቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አለበት መጥቶ እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለሁም ብሎ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አመነ፡፡ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋራ አጠፋቸው ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር አፈረ፡፡ ብስጭትና ቁጣንም እንደተመላ ወደ ንግሥት ሚስቱ ዘንድ ገባ፡፡ እርሷም አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጣላቸው አላልኩህምን አለችው፡፡ ይህንንም ከእርስዋ ሰምቶ በእርሷ ላይ እጅግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ እንዲጐትቷትና በመጋዝም እንዲሰነጥቋት አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፡፡ በዚያም ጊዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥራ ነገሥታቱ ሁሉም ደነገጡ ኀፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከእርሱም እንዲአርፍ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉሥ ዱድያኖስን መከሩት፡፡ ያን ጊዜም የክቡር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ድል አድራጊ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው፡፡
ታትሟል ኤፕሪ 29
"ማርያም አንቲ" ማርያም አንቲ ደመና ሰማይ ዘአኃዝኪ ዝናመ(፪) ተክላተ መሬት አዳም ወሔዋን ዘፈረዩ ብኪ ዳግመ(፪) ከመሬት የተገኙ አዳምና ሔዋን ሕይወት ያገኙብሽ(፪) ዝናምን የያዝሽ የሰማይ ደመና ማርያም አንቺ ነሽ(፪) ©በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
ታትሟል ኤፕሪ 29
፳፪፤ ንዴተ ሥጋ ወነፍስ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ የሥጋና የነፍስ ችግር እዳይደርስብኝ ዕንቁ ስምሽን ከክብር መዝገብ ወይም ሣጥን ወስጄ ገንዘብ አደረግሁ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ የገጽሽን ጸዳል ለማየት እፈልጋለሁ እኮን፤ ድንግል ሆይ፤ ፈጥነሽ ድረሽልኝ፤ ድንግል ሆይ፤ ገስግሰሽ ድረሽልኝ ሰውነቴ አንችን ጠጠምታለችና፡፡ ፳፫፤ አፈወ ሃይማኖት እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ በዚያ የቁርጥ ፍርድ በሚሰጥባት ዕለት ሁሉን ወደ ሕይወት ጎዳና የምትስቢ መዓዛሽ የጣፈጠ የሃይማኖት ሽቱ ነሽ እኮን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ጻድቃን በትሩፋቸው፤ በተጋድሎአቸው ያገኙሽ መንግሥተ ሰማይ ነሽ እኮን፤ የፍቅርሽ ፄና መዓዛ፤ እንደ ነጭ ዕጣን መዓዛ ሸተተኝ፤ በፍቅርሽ ወይን ጠዕምም ልቡናየ ይደሰታል፡፡ ፳፬፤ አበዊነ ቅዱሳን እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ቅዱሳን አባቶቻችን አንቺን መረጡ መድኃኒታቸው የሆንሽ አንቺንም መልካም ፍሬ አፈሩ፡፡ (አስገኙ) ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ለደካማው የመጠጊያ ተራራ ነሽና ጻድቅስ በበጎ ሥራው ይድናል እንደኔ ያለው ኃጥእ ግን መሸሻው መጠጊያው ከአንቺ በቀር ወዴት ነው፡፡ ፳፭፤ ለመልክእኪ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ መጻሕፍት እደተናገሩት ወይም እንደሚያስረዱት የእግዚአብሔርን ሥነ ራእይ ለሚመስለው ሥነ መልክእሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይ አንቺ ነሽ እኮን፤ የሚወዱሽ የሚያከብሩሽም ሁሉ በረከትሽን ያግኙ፤ የሚጠሉሽ የሚመቀኙሽ ግን ፈጥነው ይጥፉ፡፡ ፳፮፤ ስብሐት ለኪ የአብ ሙሽራው ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባል፡፡ የወልድ እናቱ ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ንጽሕት አዳራሽ ማርያም ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል፤ ወርቅና ብር ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ስለዚህም ከዚህ ዓለም ብልጽግና ይልቅ አንቺን መውደድ እመርጣለሁና፡፡ ቸርነትሽን አታርቂብኝ፡፡ ፳፯፤ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ አሁንም በመዓልትና በሌሊት ጠብቂኝ፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውሪኝ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ©መልክአ ኤዶም @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
ታትሟል ኤፕሪ 29
🌟🌟 ማርያም ፩፤ ለዝክረ ስምኪ በአምኃ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ የሰላም እመቤት ነሽና ሰላምታ ላንቺ ይገባል፡፡ እያልኩ በጠዋትና በማታ የምስጋና እጅ መንሻ አቀርብልሻለሁ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ በገነት መካከል የተተከልሽ ድንኳን ነሽ እኮን የኔ የአገልጋይሽ ኃጢአት ከሰማይ ኮከብ ይልቅ የበዛ ስለሆነ የካህናት አለቃ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነሽና ተገቢውን ንስሐ ሰጭኝ፡፡ ፪፤ ለዝክረ ስምኪ ሀሊብ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ እንደወተት አንጀትን ለሚያርስ ልብን፤ ለሚያቀዘቅዝ የመልካም ወተት ስም አጠራርሽ ሰላምታ ይገባል እያልኩ ሰላም እላለሁ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ርግብየ ርግብየ እያለ የሚያመሰግንሽ የጥበበኛው ሰሎሞን ርግብ ነሽና ድንቁርና ረኃብ እንዳይጸናብኝ እህል ጥበብን መግቢኝ ከብዙ በጎ በጎ ሥራዎች አንዱ መስጠት ነውና፡፡ ፫፤ ልብኪ የዋህ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ኀጥእን ለጥፋት የማይመኝ ቂም በቀልን የማያውቅ ልብሽ ፍጹም የዋህ ነው እኮን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ስለዚህም ይቅርታ ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ፡፡ በልቤ ውስጥ ያለውን ምኑን ስንቱን እነግርሻለሁ? ኅዘኔን ጭንቀቴንም አንች ታውቂዋለሽና፡፡ ፬፤ ከመ ከማኪ ማርያም እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ከነቢያት ከጻድቃን ከሰማዕታትም ወገን ቢሆን ከቶ እንዳች የምወደው ማንም የለ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ አንቺን መጠጊያ ስለአደረግሁ በአንቺ ከመታመን በቀር ሥራየ ኃጢአት ብቻ ሆኗልና ለእርዳታየ ፈጥነሽ ድረሽልኝ፡፡ ፭፤ ኢትኅድግኒ ዐቂበ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ በምሄድበት ጎዳና በማድርበትም ቦታ ሁሉ በመዓልትም በሌሊትም ጥበቃሽ አይለየኝ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ነፍሳትን ሁሉ የምትመግቢ ነሽና የልብስና የምግብ ችግር ባለ ዘመኔ ሁሉ አታሳይኝ፤ ረኅብና ብርድ ጸሎትን ያስረሳሉና፡፡ ፮፤ ኀበ ሖርኩ ሑሪ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ አሁንም በሄድኩበት መንገድ ሂጅ፤ በአደርኩበትም በዚያ ቸርነትሽ ጠባቂ ይሁነኝ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ በማንኛውም ወገን ንግግሬን አሳምሪ ቀኝ እጅሽን በራሴ ላይ አኑሪ፡፡ የሚፃረሩኝን ተፃረሪ ክፉ ምክራቸውንም አንድ በአንድ ዘርዝሪ፡፡ ፯፤ ንዒ ማርያም እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ከኃጢያት ሁሉ መተዳደፍ በማየ ንስሐ ንጹሕ እምኃጢአት ታደርጊኝ ዘንድ በረድኤት ወደኔ ቅረቢ እያንዳንዳችንንም በሥላሴ ስም ባርኪን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ እንደኔ ያሉትን ኃጥአኖች በጸሎትሽ ወደ ንስሐ እንዲመለሱ መንፈሳዊ ጥበብን ግልጭላቸው፤ ጻድቃንንም በምግባራቸው በትሩፋታቸው ጸንተው እንዲቆዩ ጠብቂያቸው፡፡ ፰፤ ንዒ ማርያም እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ጸሎቴን ተቀብለሽ ወደላይ ወደሰማይ ታሳርጊ ዘንድ ከላይ ከሰማይ ዳርቻ ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ዘወትር የርኅራኄሽን ጠል በኔ ላይ አርከፍክፊ፡፡ የምድር ብልጽግና ግን ኃላፊ ጠፊ በመሆኑ በቸርነትሽ ጽድቅን ታተርፊልኝ ዘንድ የተገባ ነው፡፡ ፱፤ ንዒ ማርያም ሆይ፤ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ የአዳም ልብሱ ግርማ ሞገሱ የሄኖክ የራስ ወርቅ አንች ነሽ እኮን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ብልህ አዋቂ የሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ያፈቅራል፤ ሰነፍ ልበ ቢስ ግን በከንቱ ይጠላሻል፤ ዳሩ ግን በመከረው የተንኮል ምክር ወጥመድ እሱ ራሱ ይጠመድ፡፡ ፲፤ ንዒ ማርያም፤ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ዘር ያልወደቀባት ገበሬ ያልጣረባት የቅዱስ ቁርባንን አዝመራ ያፈራሽ ገራህት ሆይ፤ ከትጉሃን መላእክት ጋር ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ዓለም እኮ የወደዳትን መልሳ ታጠፋዋለች፡፡ በወጥመዷም አስገብታ ብዙውን ሕዝበ በመርዟ እንደገደለች ይህን ሥራዋን የሚያውቅባት ከቶ እንደምን ያለ ብልህና ዐዋቂ ይሆን ስለሆነም በመጥመዷ እንዳታጠምደኝ መረቧን በጣጥሰሽ ጣይልኝ፡፡ ፲፩፤ ንዒ ማርያም እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ለዕውራን ብርሃናቸው ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኅዘን ለማን እነግረው ይሆን፡፡ ፲፪፤ ንዒ ማርያም እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ የመለኮቱ የእሳት ግለት ያላቀጠለሽ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነሽና ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ በየዘመኑ በየዕለቱም ሁሉ ማሪኝ ይቅር በይኝ አንቺ ከማርሽኝ ይቅር ካልሽኝ ማነው እሱ የሚፈርድብኝ በሥጋና በነፍስ የሚፈርድ ልጅሽ ነውና ፲፫፤ እስእለኪ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ የሰማይና የምድር ንጉሥ እናት ነሽና ኃጢአቴን ሁሉ ፈጽመሽ ለማጥፋት ፈጥነሽ ወደኔ ትመጭ ዘንድ እማልድሻለሁ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ የሥጋና የነፍስን ችግር ሁሉ ከኔ ላይ አስወግጅ፡፡ ይልቁንም ወዲያና ወዲህ በማለት ቀኑ በከንቱ እንዳይመሽብኝ በቁም ነገር ሥራ ላይ እገኝ ዘንድ፤ እኔ በደለኛው አገልጋይሽ እማልድሻለሁ፡፡ ፲፬፤ አተከዝኩኪ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ሥፍር ቁጥር በሌለው የዚህን ዓለም ፍለጋ በመከተል እኔ ኃጥኡ ጎስቋላው አገልጋይሽ አሳዘንኩሽ ይሆን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ታዲያ ከቀድሞ ጀምሮ ቂም በቀልን ይቅር ማለት ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ መሐሪዋ እናት ሆይ፤ አረጋጊኝ እንጂ አትተይኝ፡፡ ፲፭፤ አተከዝኩኪ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ በመሴሰንና የዝሙት ሥራ በመሥራት ሐሰት በመናገር አሳዘንኩሽ ይሆን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ነገር ግን አንቺን በፍጹም ልብ መውደድ ቀላል አይመስለኝም ሰባ ስምንት ነፍሳትን የበላ በላዔ ሰብእ በጥርኝ ውሃ ገነት ለመግባት በቅቷልና፡፡ ፲፮፤ ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ርኅሩኋ እመቤቴ ሆይ፤ አደፍ ጉድፍ ሳይኖርብሽ በድንግልና ጸንተሽ ያለሽ የአንች ፍቅር እሳት ሆኖ አንጀትን ያቃጥላል እኮን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ሁል ጊዜ በጎ በጎ ነገርን አድርጊልኝ፡፡ እንደ ሥራየ ሞት ይገባኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ንስሐ የምገባበት ጥቂት ጊዜ ታገሽኝ፡፡ ፲፯፤ እለ ትወርዱ ታሕተ እናንተ በዚህ ዓለም እያላችሁ ወደላይ ወደታች የምትወጡና የምትወርዱ ሁሉ የእመቤታችን ፍቅር ከቶ ቀላል አይምሰላችሁ፡፡ በየጊዜው ስሟን እየጠራ በእመቤታችን ፍቅር የተማመነ በአማላጅነቷም ጥላ ሥር የተጠለለ ዘማዊ ወይም ሴሰኛም ቢሆን፤ ፍጹም ድንግል ይሆናልና፡፡ ፲፰፤ ተአምረኪ ብዙኃ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ የእግዚአብሔር ማደሪያ እንደ መሆንሽ ብዙ የሆነ ልዩ ልዩ ተአምራትሽን በጆሮየ ሰምቻለሁ በዓይኔም አይቻለሁ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ እኔን ከርታታውን አውታታውን በዚህ ዓለም የሚያረጋጋኝ የሚያጽናናኝ አጥቻለሁና፡፡ ርኅሩኋ እናት ሆይ፤ እስኪ ቀረብ ብለሽ የማጽናኛ ቃል አሰሚኝ፡፡ ፲፱፤ ተአምረኪ ብዙኅ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ፍጻሜ የሌለው የብዙ ብዙ የሆነ ተአምርሽ በደመናና በጉም አምሳል በዓለም ላይ ተሠራጨ፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ የሮማው ጳውሎስ የመዛነቢያው ድንኳን ነሽ እኮን እኔም ንስሐ ሳልገባ እንዳልሞት ዕድሜ ትጨምሪልኝ ዘንድ ሰሎሜ ባዘለችው ልጅሽ እማፀንሻለሁ፡፡ ፳፤ ናዛዚትየ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ከኅዘን የምታረጋጊኝ እርጅናዬን በወጥትነት የምትለውጭልኘ ዘመን የማይቆጠርለት ሕፃን በማኅፀንሽ አደረ እኮን፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋቸው ነሽና ጸሎትንና ዕጣንን እንዲሁም ቅዱስ ቁርባንን በማቅረብ ጊዜ እኔ አገልጋይሽን ለማጽናናት በዚህ ቦታ ተገኝ፡፡ ፳፩፤ ስምኪ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ስምሽ ኃጥኣንን ያጸድቃል ሰነፎችንም ብልህና ትጉህ ያደርጋል፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ እኔ የአእምሮ ድኃ የሆንኩ አገልጋይሽ ብቻ ቀርቻለሁና፡፡ ብዙውን የልቤን ኅዘን ነግሬሽ ከኅዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ፈጥነሽ ወደኔ ነይ፡፡
ታትሟል ኤፕሪ 25
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች pinned a photo
ታትሟል ኤፕሪ 25
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ 🚀 ከማለፍ በፊት ይጀምሩ 🪙 ብዙ ሰወች የNEX ሳንቲሞችን እየሰበሰቡ ነው ቀድመው ይቀላቀሉ። 💵 ጓደኞችን ስንጋብዝ = በአንድ ሪፈራል 10,000 NEX (እስከ $1,000 ዋጋ ያለው 💵) ኤርድሮፕ እናገኛለን 👥 ጓደኞችን ሲጋብዙ ተጨማሪ ሳንቲሞች ይሰጣል ✔️ 🌐 በማህበረሰቡ ውስጥ ተጨማሪ ሽልማቶች አሉ 🔥 እስካሁን ካልጀመራችሁ እንዳያመልጣችሁ 😏 በዚህ ይመዝገቡ ለመጀመር፦ https://m.novaexai.com/register?inviteCode=ZdNcKg ☄️💵 ይህንን ኮድ ስትጠቀሙ 1000$ ይሰጣል ፦ ZdNcKg ✅ Website፦ https://novaexai.com/ ✅ የመተግበሪያ ማውረድ አገናኝ፦ https://novaexai.com/download 💬 የማህበረሰብ መዳረሻ፦ https://t.me/NovaEx_Ai 🔔 ለትልቅ ነገር አይዘገዩ
ታትሟል ኤፕሪ 23
✞ሰማዕትነት አያምልጣችሁ !🔔 በጥንቱ ዘመን ሰማዕትነት ከዓላዊያን ነገሥታት ጋር ነበር። ዓላዊያን ነገሥታት ክርስቲያኖችን ያሳድድዋቸዋል። ክርስቲያኖችም ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ይሰደዳሉ። ስለ ሃብት ንብረታቸው፣ ስለ ምድራዊ ክብራቸው፣ ስለ ሚስቶቻቸው፣ ስለ ልጆቻቸው፣ ስለ ምድራዊት ኑሮአቸው ብዙም አይጨነቁም። ዋናው ጭንቀታቸው ነፍሳቸው ከአምላክዋ ከወዳጅዋ ከሞተላት አፍቃሪዋ ርቃ እንዳትሰደድ ነበር። ታዲያ ለዚህ ብለው የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ግማሾቻቸው ዱር ለዱር፣ ግማሾቻቸው ተራራ ለተራራ፣ ግማሾቻቸው ዋሻ ለዋሻ፣ ግማሾቻቸው ፍርክታ ለፍርክታ ተቅበዘበዙ። ብዙ የብዙም ብዙ መከራ ተቀበሉ። ነፍሳቸውን ለማትረፍ ብለው ራሳቸውን በየመቃብሩ፣ በየበረሃው ይደብቁ ነበር። በጣም የሚያስደንቀኝ ግን ይህን ያደረጉት በጣም ብዙ እናቶችም መኖራቸው ነው። ልጆቼ የእኛ ሰማዕትነት ግን እንዲህ አይደለም። የእኛ ሰማዕትነትና ውጊያ በላያችን ላይ ካሉት ነገሥታት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከምኞቶቻችን ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከስግብግብነት፣ ከእንቅልፍ፣ ከዋዛ ፈዛዛ፣ ከስንፍና፣ ከውሸት፣ ከሐሜት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት በጠዋት ተነሥቶ ለጫወታ መሮጥ ሳይሆን ለጸሎት፣ ለስግደት ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ነው። የእኛ ሰማዕትነት ወንበራችን እስኪጎደጉድ ድረስ ፊልም ማየት ሳይሆን ቃለ እግዚአብሔርን ማንበብ ነው። ስለዚህ ልጆቼ! ከምኞቶቻችን ጋር ተጋድሎ እንግጠም። ነፍሳችንን ከአምላክዋ ጋር ከሚያጣሉ ደግሞም ለጊዜው ሳይሆን ለዘለዓለም ከሚለይዋት ፍላጎቶቻችን ጋር እንጋደል። ስለ ምድራዊ ሃብት፣ ስለ ምድራዊ ዝና፣ ስለ ጊዜአዊ ደስታ ብለን ነፍሳችንን ለዓላውያን ነገሥታት (ለምኞቶቻችን) ትንበረከክ ዘንድ አሳልፈን አንስጣት። ነፍሳችንን ከእነዚህ ነገሥታት መከራ እናድናት። እነዚህን ነገሥታት ድል አድርገን ከአምላክዋ ጋር እናገናኛት። ከእንቅልፍ ጋር ተዋግተን ድልም አድርገን ጠዋት ለጸሎት ፣ ለስግደት እናበርታት። የእኛ ዘመን ሰማዕትነት ይህ ነውና። ........ ✞ ✞ ✞ .......... ☞ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ[ትርጉም-ገብረ እግዚአብሔር ኪደ] ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
ታትሟል ኤፕሪ 19
ሰአሉ ለነ ሰማዕታተ ሊብያ ሰአሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን፣(2) ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት።(2) ከምድረ ሊብያ ተጣራ ኢየሱስ፣ በተዋሕዶ ልጆች ስሙ እንዲቀደስ፣ ኢየሱስ አምላክ ነው እያሉ በጽናት፣ መንግሥተ ሰማይን ህጻናት ተሻሟት።(2) ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት(2) በመከራ ጊዜ ሚዛን ላይ ወጣችሁ፣ በክርስቶስ ጸጋ እንደ ዕንቁ አበራችሁ፣ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይፍን ሳትፈሩ፣ እግዚአብሔር ይመስገን በቃችሁ ለክብሩ።(2) አዝ----- እዩት ሲያንገላቱት ሲያዳፉት ጨክነው፣ ምንም አልቀመሰም ወንድሜ ጾሙን ነው፣ ግን እንደ ሰርገኛ በደስታ ይጓዛል፣ በሰይፍ ፊት ቆሞ ለወንጌሉ ታምኗል፣ መከራውን ንቆ ለወንጌሉ ታምኗል። አዝ----- ግርፋት ወይስ ሞት መታረዱ ነው ወይ፣ ከክርስቶስ ፍቅር እኛን የሚለየን፣ ያመለክነው አምላክ እውነት ስለሆነ፣ ለክብር ተፋጠኑ ልባቸው ጨከነ።(2) ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት(2) የኋልዮሽ ታስረው እንደበግ ሲነዱ፣ ይመስሉ ነበረ ለሰርግ የሚሄዱ፣ በጉድጓድ ተከተው ለቀናት ቢራቡ፣ በውኃ ጥም ዝለው አልተነዋወጹም። አዝ----- ገዳዮች ድል ሆኑ ሙታን ሆኑ እነርሱ፣ የተዋሕዶ ልጆች በድል ገሰገሱ፣ በደማቸው ጸዳል ዓለምን ቀየሩ፣ የኢትዮጵያ ከዋክብት በሊብያ አበሩ፣ የኢትዮጵያ ከዋክብት በዓለም አበሩ። ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ከዋክብት(2) በሊቀ መዘምራን ይልማ ኅይሉ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
ታትሟል ኤፕሪ 19
ሚያዝያ ፲፩ ዝክረ ሰማዕታተ ሊብያ🩸 አሥራ አንደኛ ዓመት 🕯🕯 አመ ዐሡሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት አዕረፉ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ:: በረከቶሙ የሃሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡ @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox
ታትሟል ኤፕሪ 18
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም: ተነስቷል በዚህ የለም(2): መድኃኔዓለም ሞት የማይችለው የበረታ: ኃያል ነው ማይረታ ማኅተሙን የፈታ: የትንሳኤው ጌታ። *አዝ* ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና: ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና: ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን ምንዘምረው: መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው : ዳንን የምንልው። *አዝ* ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘለዓለም: በመቃብር ሞት ይይዝህ ዘንድ ከቶ አልቻለም: ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ: ዘመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ: ከፍ በል በእልልታ። *አዝ* ሞቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር: ጌትነትህ ሥራህ ይኖራል ሲመሰከር: ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ: ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጠላት ፈራ: ዕፁብ ያንተ ሥራ። *አዝ* መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና: መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና: ከተማዋ አንዳች ሆናለች በለሊቱ: በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ: ከበሮውን ምቱ። በዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን @Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox