የልጥፍ ይዘት
በአፕወርክ ፕሮፖዛል ላይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች የደንበኛውን ትኩረት ለመሳብ በጣም ወሳኝ ናቸው። ደንበኛው የእርስዎን ፕሮፖዛል እንዲከፍት የሚያደርጉ 7 ውጤታማ መግቢያዎች እነሆ፦ 1ኛ መግቢያ — መፍትሔ አመላካች (ምክር መስጠት) "ሰላም [የደንበኛው ስም]! የሥራ ማስታወቂያህን ካነበብኩ በኋላ አንድ ነገር ወዲያውኑ ታይቶኛል፦ ችግርህ [ደንበኛው የጠቀሰው ችግር] ሳይሆን [አንተ ያስተዋልክበት ትክክለኛው ችግር] ይመስለኛል። ይህንን ችግር እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ በቀላሉ ለመፍታት እነዚህን እርምጃዎች መከተል ትችላለህ፦" ደረጃ 1 ደረጃ 2 ደረጃ 3 "በፈለግከው ሰዓት ደውለህ ልታናግረኝ ትችላለህ። መልካም ጊዜ!" 2ኛ መግቢያ — ዝቅተኛ ስጋት ያለው አማራጭ ማቅረብ "ሰላም [የደንበኛው ስም]! የሥራ ማስታወቂያህን አይቼ ቀላል እና ምንም ስጋት የሌለበት አማራጭ ላቀርብልህ ፈለግኩ። በአፕወርክ ላይ አዲስ ብሆንም፣ ትኩረቴ ከደንበኞች ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት መፍጠር ላይ ነው። የሰራኋቸውን ስራዎች (Portfolio) እዚህ ማየት ትችላለህ፦ [ሊንክ ያስቀምጡ]። ውሳኔውን ላቀልልህ በማሰብ፣ ለምሰጠው አገልግሎት የ20% ቅናሽ አደርግልሃለሁ፤ በምላሹም ያገኘኸውን አገልግሎት በተመለከተ ትክክለኛ አስተያየትህን (Feedback) እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ።" 3ኛ መግቢያ — እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆንን ማሳየት "ሰላም [የደንበኛው ስም]! በ [ደንበኛው እርዳታ በሚፈልግበት ጉዳይ] ላይ እገዛ እየፈለግክ እንደሆነ ተረድቻለሁ። የሥራ ጫናው አስቸጋሪ ሆኖብህ ከሆነ፣ ይህን ስራ ከትከሻህ ላይ አውርጄ በትክክል እንዲከናወን ማድረግ እችላለሁ። በአሁኑ ሰዓት ክፍት የሥራ ጊዜ ስላለኝ፣ ያለምንም ተጨማሪ ውጥረት ላግዝህ እችላለሁ።" 4ኛ መግቢያ — ተመሳሳይ ስራ በቅርቡ እንደሰራህ ማሳየት "ጤና ይስጥልኝ [የደንበኛው ስም]! ያወጣኸው የሥራ ማስታወቂያ ትኩረቴን የሳበው ከጥቂት ቀናት በፊት ልክ እንደዚህ ያለ ተመሳሳይ ስራ ስለሰራሁ ነው። የሰራሁት ስራ ይሄውልህ፦ [ሊንክ]። አሰራሩ አሁንም በአእምሮዬ ትኩስ ስለሆነ፣ በምን መንገድ እንደሰራሁት በዝርዝር እንድንወያይ ብንደዋወል ደስ ይለኛል።" 5ኛ መግቢያ — የደንበኛውን ስኬት ማድነቅ "ሰላም [የደንበኛው ስም]! [ለጀመርከው ፕሮጀክት፣ ለደረስክበት የሙያ ደረጃ ወይም ለድርጅቱ ለውጥ] እንኳን ደስ አለህ፤ ይህ በጣም ደስ የሚል ደረጃ ነው። ልክ አንተ ባለህበት ደረጃ ላይ የሚገኙ ግለሰቦችን ትኩረት ባለው የኢሜይል ማርኬቲንግ ስትራቴጂ በመጠቀም ገቢያቸውን እስከ 10 እጥፍ እንዲያሳድጉ ረድቻለሁ። ቀደም ብዬ ያስመዘገብኳቸውን ውጤቶች እዚህ ማየት ትችላለህ፦ [ሊንክ]።" 6ኛ መግቢያ — ሳይቀጠሩ ዋጋዎን ማሳየት "ሰላም [የደንበኛው ስም]! [ሊቀጥሩት ያሰቡትን የሥራ መደብ] እየፈለግክ እንደሆነ አስተውያለሁ። ለሥራው ብቁ መሆኔን በፍጥነት እንድትገመግም፣ ለዚህ የሥራ ዘርፍ የሚሆኑ ነፃ ናሙናዎችን (Free Samples) አዘጋጅቻለሁ። ካስፈለገም፣ ለተለየ ፍላጎትህ የሚሆን አጭር ናሙና በአንድ የሥራ ቀን ውስጥ ሰርቼ ማሳየት እችላለሁ።" 7ኛ መግቢያ — ብልህ ጥያቄዎችን በመጠየቅ መጀመር "ሰላም [የደንበኛው ስም]! የሥራውን ዝርዝር አይቻለሁ፤ ነገር ግን የመፍትሔ ሃሳብ ከማቅረቤ በፊት ጥቂት ነገሮችን ግልጽ ብታደርግልኝ ደስ ይለኛል፦" [ተዛማጅ ጥያቄ ቁጥር 1] [ተዛማጅ ጥያቄ ቁጥር 2] "ይህም የምሰጠው ውጤት አንተ ካቀድከው ግብ ጋር በትክክል እንዲጣጣም ይረዳል።" ይህ መረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር አድርጉት