የልጥፍ ይዘት
በUpwork የመጀመሪያ ስራን ለማግኘት የሚረዱ ወሳኝ ምክሮች በUpwork ላይ የመጀመሪያውን ስራ ማግኘት በጣም ፈታኝ እንደሆነ ይታወቃል። ለዚህም ዋናው ምክንያት በገጹ ላይ የሰራነው ስራ አለመኖሩና ደንበኞች (Clients) በእኛ ላይ ያላቸው እምነት አነስተኛ መሆኑ ነው። እኔም በዚህ ሂደት ውስጥ ያለፍኩባቸውንና የተማርኩባቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ለእናንተ ላካፍላችሁ ወደድኩ። 1. "Copy-Paste" ፕሮፖዛልን ያስወግዱ ብዙዎቻችን አንድ አይነት ፕሮፖዛል ለሁሉም ደንበኛ በመላክ ስራ ለማግኘት እንሞክራለን። ይህ ትልቅ ስህተት ነው! ለእያንዳንዱ ስራ የተለየና ማራኪ የሆነ ፅሁፍ አዘጋጁ። የተለመዱና አሰልቺ ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ አዲስና ሳቢ የሆኑ ቃላትን ተጠቀሙ። 2. የደንበኛውን ፍላጎት በትክክል መረዳት ፕሮፖዛል ከመፃፋችሁ በፊት ደንበኛው ምን እንደሚፈልግ ደጋግማችሁ አንብቡ። ዋናውን ነጥብ (Core Point) ጨብጡ፡ ደንበኛው የገጠመው ችግር ምንድነው? እንዴትስ ልትፈቱለት ትችላላችሁ? ደንበኛው ጥያቄውን በሚገባ እንደተረዳችሁት ካወቀ፣ ስራውን ለእናንተ የመስጠት እድሉ ሰፊ ነው። 3. ፕሮፋይልዎን በሚገባ ያደራጁ በUpwork ላይ የሰራችሁት ስራ ባይኖርም፣ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ቦታዎች የሰራችሁትን ስራ (Portfolio) ማሳየት ትችላላችሁ። ያለፉ ስራዎቻችሁን እንደ ማስረጃ (Sample) አያይዙ። ፕሮፋይላችሁ የእናንተን ሙያና ብቃት በሚገባ የሚገልጽ መሆኑን አረጋግጡ። ትዕግስትና ጥራት ያለው ስራ ለስኬት ወሳኝ ናቸው። የመጀመሪያ ስራ ማግኜት ከፈለጋችሁ እኔን ማናገር ትችላላችሁ ።