የልጥፍ ይዘት
የUpwork አልጎሪዝም እንዴት ነው የሚሰራው? አልጎሪዝሙ በግምት ሳይሆን ግልጽ በሆኑ ምልክቶች (Signals) ላይ ተመስርቶ ነው የሚሰራው። እነዚህም፦ • የፕሮፋይልዎ መታየት (Impressions) እና ተከፍቶ መታየት (Clicks)። • የሚልኳቸው ፕሮፖዛሎች በደንበኞች የመታየት እና ወደ ንግግር የመቀየር ፍጥነት። • የስራ ስኬት ውጤት (Job Success Score) እና ከደንበኞች ጋር ያለዎት ግንኙነት። ________ ፕሮፋይልዎ እንዳያድግ የሚያደርጉ ስህተቶች • ግልጽነት ማጣት፦ ምን አይነት ችግር እንደሚፈቱ በግልጽ አለማስቀመጥ። • የሌሎችን ኮፒ ማድረግ፦ የሌሎችን ሰዎች ፕሮፋይል በChatGPT ወይም በሌሎች AI መሳሪያዎች "ቀይረህ ጻፍልኝ" ብሎ መጠቀም (ይህ ልዩ መታወቅያን ያጠፋል)። • ሰው ሰራሽ (AI) መምሰል፦ ጽሁፍዎ ከልብ የመነጨ እና እውነተኛ ሳይሆን ሲቀር አልጎሪዝሙም ሆነ ደንበኞች እምነት ያጣሉ። ________ ውጤታማ ለመሆን መደረግ ያለባቸው ነገሮች 1. ግልጽነት፦ ፍጹም ለመሆን ከመሞከር ይልቅ የሚሰሩትን ስራ በግልጽ (3-5 መስመር) ማስቀመጥ። 2. ቁልፍ ቃላት (Keywords)፦ የሚሰሩትን ስራ የሚገልጹ ቃላትን በጽሁፍዎ ውስጥ በተፈጥሯዊ መንገድ መጠቀም። 3. ማስረጃዎች (Portfolio & Trust)፦ የሰሯቸውን ስራዎች ማሳየት፣ የቪዲዮ መግቢያ ማካተት እና የደንበኞች ምስክርነት (Testimonials) ማግኘት። 4. መቀናጀት (Alignment)፦ ፕሮፋይልዎ፣ የምትልኩት ፕሮፖዛል እና የምታደርጉት እንቅስቃሴ አንድ አይነት መልእክት ሲኖራቸው አልጎሪዝሙ ፕሮፋይልዎን ለብዙ ሰዎች እንዲታይ ያደርገዋል። ባጭሩ፦ Upwork ላይ ስኬታማ መሆን በእድል ሳይሆን በውሂብ (Data) እና በግልጽነት ላይ የተመሰረተ ነው።