TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
ይዘት
የልጥፍ ይዘት
የአንትሮፒክ ኩባንያ "ክሎድ" የተሰኘውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሉን አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያን በቅርቡ እንደሚያካትት ይጠበቃል። በኩባንያው ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ በሚገኘው "የሚደገፉ ሀገራት" ዝርዝር ላይ ኢትዮጵያ ተካታ መታየቷን የሚያሳዩ መረጃዎች ወጥተዋል። ይህ ይፋዊ እንቅስቃሴ ሲጠናቀቅ፣ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች እንደ 'ቪፒኤን' ያሉ አቋራጭ መንገዶችን መጠቀም ሳያስፈልጋቸው የክሎድን የላቀ የኤአይ ቴክኖሎጂ በቀጥታ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ይህም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ እርምጃ ይሆናል።