TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
ወደ ቻናሎች ዝርዝር ተመለስ
ESAT (ኢሳት🇪🇹)® avatar

TGINSIGHT CHAT

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

@esat_tv1

News and media

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉@Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

ደምበኞች21.3万የአሁን ደምበኞች
የተከታተሉ ልጥፎች1,001የተዘረዘሩ ልጥፎች ቁጥር
የቅርብ ጊዜ ደረሻ748,100የቅርብ ጊዜ ዕይታዎች ድምር
የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

የቅርብ ጊዜ ልጥፎች

ገጽ 1 ከ 84 · 1,001 ልጥፎች

ታትሟል ሜይ 4

ኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ ከአሜሪካ ምላሽ ማግኘቷን የአገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ‼️ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሜሪካ የሰጠችው ምላሽ በፓኪስታን በኩል እንደደረሳቸው እና እየተመለከቱት መሆኑን መናገራቸውን ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል። አሜሪካ እስካሁን ድረስ ለቴህራን የሰላም ዕቅድ ምላሽ መስጠቷን በይፋአላሳወቀችም። ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እሁድ ዕለት ለእስራኤሉ ካን ኒውስ ዕቅዱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል። የኢራን መገናኛ ብዙኃን የቴህራን ባለ 14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ዋሺንግተን ጦሯን ከድንበር አካባቢ እንድታርቅ፣ የኢራን ወደቦች ላይ ያለቸውን እገዳ እንድታነሳ እንዲሁም የትኛውም ግጭት፣ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመውን ጨምሮ እንዲቆም የሚጠይቅ ነው ሲሉ ዘግበዋል። ዕቅዱ በሁለቱ አገራት መካከል በሰላሳ ቀናት ውስጥ ስምምነት እንዲደረስ ይጠይቃል። የኢራን መገናኛ ብዙኃን አክለውም የሰላም ዕቅዱ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች አሁን ያለውን የተኩስ አቁም ከማራዘም ይልቅ “ጦርነቱን በማስቆም” ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ይጠይቃል። መገናኛ ብዙኃኑ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይን ጠቅሰው “አሁን ባለው ደረጃ ስለ ኒውክሌር ድርድር የለም” ማለታቸውን ዘግበዋል። ኢራን በተደጋጋሚ የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል መሆኑን ትናገራለች። ነገርግን ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ባይኖራትም ዩራኒየምን የጦር መሣሪያ ለማምረት በሚያስችል ደረጃ ያበለጸገች ብቸኛ አገር ናት። @Esat_tv1 @Esat_tv1

24,200 views

😱ተጀመረ #በአዲስአበባ ፤ #ባህርዳር፤ #ደሴ_ኮምቦልቻ፤ #ደ_ብርሀን እንዲሁም #በወልዲያ በ 1850 ብር ብቻ 3500 ብር የሚሸጠዉን የፂምና የፀጉር ሼቨር ባሉበት ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ይቀበሉ😱 ‼️አዲስ አበባን ጨምሮ በጠቀስናቸዉ ከተሞች በ 30 ደቂቃ ዉስጥ ያሉበት ስናደርስ🚚 በሌሎች ከተሞች በፖስታ📩 ቤት እንልካለን ። ጥቂት ፍሬዎች ብቻ ሰላስገባን ፈጥኖ በመደዉል በዕድሉ ይጠቀሙ። 👇👇👇👇👇👇 👉📞0954633900 👉📞0954633900 👉📞0954633900 ✍ወይም ስልኮንና አድራሻዎን በ👉@dubaitera_shop ላይ ይላኩልን! ✂️መብራት ጠፋ..ፀጉር ቤት ወረፋ ይሆን ብለዉ ሳያስቡ ሁሌም ከቤቶ ሲወጡ ፀጉሮም ሆነ ፂሞ እንዲያምርበት የሚያደርግ ማሽን። ✂️በየትኛዉም የሰዉነት ክፍሎች ላይ ያለዉን ፀጉር ማፅዳት የሚችል። ✂️በአንድ ቻርጀር 45 ቀን የሚቆይ ቻርጀር እና 4 የጥርስ መቀያየሪያዎች ያሉት። ✂️ኦሪጅናል እና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ። ✂️ ለፀጉር እና ለፂም ቅርፅ ተመራጭ። ✂️ለህፃናት ፀጉር ለመቁረጥ የሚመች። ✂️ሁሉም ወንድ ሊኖረዉ የሚገባ ምርጥ ዕቃ ‼️ለማዘዝ እና መረጃ ለማግኘት‼️ 👇👇👇👇👇👇👇 📞0954633900 📞0954633900 ይደዉሉልን! ✍ወይም ስልኮንና አድራሻዎን በ👉@dubaitera_shop ላይ ይላኩልን! 🎁ሌሎች ዕቃዎችን ለማየት🎁 @Dubai_tera2 ን 👆👆👆join ይበሉ!

23,300 views

ታትሟል ሜይ 3

በአማራ ክልል አፍቲት መጠለያ ጣቢያ በሱዳናውያን ስደተኞች ላይ ለስድስተኛ ጊዜ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃት ተፈጸሙ‼️ በኢትዮጵያ አማራ ክልል በሚገኘው አፍቲት መጠለያ ጣቢያ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ስድስተኛ ዙር ጥቃት በርካታ ሱዳናውያን ስደተኞች መቁሰላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ታጣቂዎቹ ወደ መጠለያዎች በመግባት ንብረት በዘረፉበትና ቤተሰቦችን በደበደቡበት ወቅት መሆኑ ተጠቁሟል። ይህን ተከትሎም ስደተኞቹ በቂ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ወይም ወደ ሱዳን እንዲመለሱ በመጠየቅ በተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በምስራቅ ቻድ በሚገኙ መጠለያዎችም በእሳት አደጋና በታጠቁ ጥቃቶች ምክንያት የጸጥታ ስጋት መንገሡና የቻድ ፕሬዝዳንት ድንበር ላይ ወታደራዊ ዝግጁነት እንዲጨምር ማዘዛቸው ታውቋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

35,500 views

ታትሟል ሜይ 1

በምሥራቅ ጉራጌ ዞን አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ‼️ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ አምስት ሰዎች በታጣቂች ተገደሉ።ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ያደረሱት ትናንት ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ በተኙበት ገብተው መሣሪያ በመተኮስ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የሟች ዘመዶች ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳ ኢንሴኖ በተባለ ከተማ ውስጥ መሆኑን ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ የሟች የቅርብ ዘመድ «ታጣቂዎቹ በተለምዶ አየር ጤና ተብሎ በሚጠራው መንደር እየተኮሱ ነው የገቡት፡፡ወደ መኖሪያ ቤት በመግባት አምስት ሰዎችን ተኩሰው ከገደሉ በኋላ ተመልሰው ሄደዋል፡፡ከሟቾቹ መካከል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ እናት ከሦስት ልጆቿ ጋር ነው» ብለዋል ፡፡ በከተማው ነዋሪ የሆኑ ሌላ የዐይን አማኝ በበኩላቸው ግድያው መፈጸሙን አረጋግጠው ጥቃት አድራሾቹ በአካባቢው በሽፍትነት የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተናግረዋል፡፡ዶቼ ቬለ ጥቃቱን በተመለከተ ለማነጋገር በስልክ ያገኛቸው የምሥራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ሰረላ መረጃውን አሰባስበው እንደሚገልጹ ቀጠሮ ይዘው ነበር፡፡ነገር ግን በቀጠሮው ሰዓት ሥልካቸው ዝግ በመሆኑ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ @Esat_tv1 @Esat_tv1

50,300 views

ታትሟል ኤፕሪ 28

ኢራን የመከላከያ ቴክኖሎጂዋን ለሻንጋይ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገለጸች‼️ ኢራን ያሏትን የመከላከያ ትጥቅና የቴክኖሎጂ አቅሞች ለ‹‹ገለልተኛ ሀገራት›› በተለይም ደግሞ ለሻንጋይ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች። የኢራን ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ሬዛ ታላይ-ኒክ እንደገለጹት፤ ቴህራን በራሷ አቅም ያበለጸገቻቸውን የመከላከያ ትጥቆችና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለወዳጅ ሀገራት ለማጋራት ፍላጎት አላት። ምክትል ሚኒስትሩ በተለይ ትኩረት የሰጡት የሻንጋይ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራትን ሲሆን፤ ኢራን ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያላትን ወታደራዊና የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር እንደምትፈልግ ጠቁመዋል። ይህም ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል። ኢራን በቅርብ ዓመታት በተለይም በሚሳዔል እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ቴክኖሎጂ ከፍተኛ እድገት ማሳየቷ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጥሪ የቀረበው ሀገሪቱ በምዕራባውያን አገራት ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስና ከምስራቁ ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በምታደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ተነግሯል። የሻንጋይ የትብብር ድርጅት እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ፓኪስታን ያሉ ሀገራትን በአባልነት የያዘ ሲሆን ኢራንም በቅርቡ የድርጅቱ ሙሉ አባል መሆኗ ይታወቃል ሲል አል-አረቢያ ዘግቧል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

68,700 views

ታትሟል ኤፕሪ 27

በማሊ ወታደራዊ ተቋማት ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ የተቀናጀ ጥቃት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሳዲዮ ካማራ ተገደሉ‼️ በማሊ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ የተቀናጀ ጥቃት፣ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ጄነራል ሳዲዮ ካማራ መገደላቸውን የመንግሥት ቃል አቀባይ አረጋገጡ። የመንግሥት ቃል አቀባዩ ኢሳ ኡስማን ኩሊባሊ እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫ፤ ጄነራል ሳዲዮ የተገደሉት ታጣቂዎች መኖሪያ ቤታቸውን ኢላማ አድርገው በፈጸሙት ጥቃት መሆኑን ገልጸዋል። በካቲ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሚኒስትሩ መኖሪያ ቤት ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ጥቃት የደረሰበት ሲሆን፣ ጥቃቱ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ባላቸው ታጣቂዎች እና በቱዋሬግ አማፂያን በጋራ የተፈጸመ መሆኑ ተመላክቷል። ጄነራል ሳዲዮ በ2012 እና 2013 ዓ.ም. በተካሄዱት ተከታታይ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን በያዘው ወታደራዊ መንግሥት ውስጥ ቁልፍ ሰው ነበሩ። የአልጄዚራው ዘጋቢ ኒኮላስ ሐክ ስለ ጉዳዩ ሲናገር፤ “ጄነራል ሳዲዮ በገዥው ወታደራዊ አመራር ውስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ከነበራቸው ግለሰቦች አንዱ ሲሆኑ፣ አንዳንዶችም እንደ ወደፊት የማሊ መሪ አድርገው ይመለከቷቸው ነበር” ብሏል። አክሎም “የእሳቸው መሞት ለሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ትልቅ ኪሳራ ነው” ሲል ገልጿል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

67,800 views

ታትሟል ኤፕሪ 24

የታሸገ ውሃ የዋጋ ጭማሪ በዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ‼️ በቅርቡ በታሸጉ የውሃ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በዓለም አቀፍ አለመረጋጋት የተፈጠረ እንጂ በሀገር ውስጥ ካለው የምርት አቅርቦት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደበበ ወርቁ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። የታሸገ ውሃ አምራቾች የጥሬ ዕቃ ግብዓቶችን ከውጭ ሀገራት የሚያስገቡ በመሆኑ፣ አሁን ላይ ግብዓቶቹን በሚፈለገው መጠን ማስገባት አለመቻሉን ሥራ አስኪያጁ ገልጸው፤ በዚህም ምክንያት በምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አስረድተዋል። ቀደም ሲል በታሸገ ውሃ አምራቾች በኩል የሚነሱ የውጭ ምንዛሬ እና የግብዓት አቅርቦት ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተው፣ በአሁኑ ወቅት ከአንድ መቶ በላይ አምራቾች ወደ ዘርፉ መቀላቀላቸውን ሥራ አስኪያጁ አስታውሰዋል። ያሉት አምራቾችም በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ በመሆኑ ከአቅርቦት ጋር የተያያዘው ችግር መፈታቱን አብራርተዋል። በቅርቡ በሁሉም የታሸጉ የውሃ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ወቅታዊ መሆኑን የገለጹት አቶ ደበበ፣ የዓለም አቀፍ ገበያው ሲረጋጋ ችግሩ እንደሚቀረፍ አመልክተዋል። በመጨረሻም በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ወደ ዘርፉ የሚገቡ አምራቾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው፤ በምርት ሂደት ላይ የሚታዩ የዋጋ፣ የጥራት እና መሰል ችግሮች እንዲፈቱ ተቋሙ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። @Esqt_tv1 @Esat_tv1

87,300 views

ታትሟል ኤፕሪ 23

ኢራን ለተኩስ አቁም ስምምነቱ እውቅና እንደማትሰጥ አስታወቀች‼️ በመካከለኛው ምስራቅ የነበረው ደካማ ሰላም አደጋ ላይ ወድቋል፤ ቴህራን ወታደራዊ እርምጃ ልወስድ እችላለሁ በማለት ዝግጅቷን እያሳየች ነው። የኢራን መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን ባስተላለፉት አስቸኳይ መረጃ መሠረት፣ ሀገሪቱ በቅርቡ የተደረሰውንና የተራዘመውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደማታውቀው በይፋ ገልጻለች። የቴህራን ባለሥልጣናት እንደተናገሩት ከሆነ ኢራን በማንኛውም ስምምነት የምትገዛው የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ብቻ መሠረት በማድረግ ሲሆን፣ ይህንን ጥቅሟን ለማስከበር ስትልም አስፈላጊውን ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ወደኋላ እንደማትል ፍንጭ ሰጥተዋል። ይህ ያልተጠበቀ አቋም ቀጣናውን ወደ ከፍተኛ ውጥረትና አለመረጋጋት የከተተው ሲሆን፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት አሁን ላይ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበታል። የኢራን ባለሥልጣናት በሰጡት ማብራሪያ ሀገራቸው ለማንኛውም ዓይነት የኃይል እርምጃ ዝግጁ መሆኗን በማሳሰብ፣ ቀጣይ ውሳኔዎቻቸው በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታዎችና በብሔራዊ ደህንነታቸው ላይ ብቻ የተመሰረቱ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

77,200 views

ታትሟል ኤፕሪ 22

ተኩስ አቁሙን አራዝመናል ‼️ 🗣️ትራምፕ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ለሊት ያበቃው ከኢራን ጋር የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲራዘም መወሰናቸውን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ውሳኔ ያስለለፉት ቴህራን ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችል የሰላም ስምምነት የውሳኔ ሃሳብ እንድታቀርብ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ምክንያት የታቀደው ወታደራዊ ጥቃት ለጊዜው እንዲቆይ መታዘዙን ትራምፕ አመልክተዋል። ይህ የተኩስ አቁም ማራዘሚያ የተደረገው በፓኪስታን አደራዳሪዎች ጥያቄ መሆኑን አሳውቀዋል። ትራምፕ ከዚህ ውሳኔያቸው ቀደም ብለው የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማራዘም ፍላጎት እንሌላቸውና " ኢራን ጊዜው እያለቀባት " መሆኑን በመግለጽ ሲዝቱ ነበር። አሁን ግን የኢራን የሰላም ስምምነት ሃሳብ ቀርቦ ውይይቶች እስከሚጠናቀቁ ድረስ ስምምነቱ ተራዝሞ ወታደራዊ ዝግጁነቱና ከበባው ግን እንዲቀጥል ትዕዛዝ ሰጥተዋል። በጉዳዩ ላይ ከኢራን በኩል እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ ባይኖርም የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ግን የቴህራን አቋም በቀጣይ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

86,000 views

ታትሟል ኤፕሪ 21

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብ መቆጣጠሯን ተከትሎ ኢራን የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ዛተች፤ በአዲሱ የሰላም ንግግር ላይም ለመሳተፍ “ውሳኔ ላይ አልደረስኩም” አለች‼️ አሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ አቅራቢያ የኢራን ሰንደቅ ዓላማ ያረፈበትን የጭነት መርከብ መቆጣጠሯን ተከትሎ ኢራን የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች። ድርጊቱ በአሜሪካ ወታደራዊ ከበባ ሳቢያ እየናረ የመጣውን ውጥረት ይበልጥ አባብሶታል። የአሜሪካ ባሕር ኃይል የኢራን ሰንደቅ ዓላማ ያረፈበትን የጭነት መርከብ የተቆጣጠረው “ከበባውን ለማስፈጸም” በወሰደው እርምጃ አካል በከፈተው ነው ያለ ሲሆን፣ ይህም ከቴህራን ጠንከር ያለ ምላሽ አስከትሏል። የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ድርጊቱ “ያለ ምላሽ እንደማያልፍ” ያስጠነቀቁ ሲሆን፣ ስትራቴጂካዊ በሆነው የባሕር መስመር ላይም ተጨማሪ ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዳግም ስለሚጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እርግጠኛ ያልሆኑ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል። ጄዲ ቫንስ እና ሌሎች የአሜሪካ ተደራዳሪዎች ለአዲስ ዙር ንግግር ወደ ፓኪስታን ያመራሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ ኢራን ግን እስካሁን ተሳትፎዋን አላረጋገጠችም። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀረበው የድርድር ጥሪ ላይ ስለመካፈል “ምንም ዓይነት ውሳኔ አልተላለፈም” ያለ ሲሆን፣ ይህም ውጥረቱ እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት ውይይቱን ለመቀጠል የሚደረገውን ጥረት ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

76,900 views

ታትሟል ኤፕሪ 20

ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት መጀመሯን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ‼️ ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እያደረገች ያለው ሽግግር ወደ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች (ገልባጮች) መሸጋገሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ እሁድ ሚያዝያ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መረጃ መሠረት፤ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች አሁን ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቱ ቀደም ሲል የጀመረችውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽግግር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ገልጿል። እንደ ሀገር የኤሌክትሪክ መኪኖች ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ የተጀመረው ሽግግር፣ አሁን ላይ አዲስ የፖሊሲ ለውጥ በመደረጉ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም መሠረት “በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና የኢንዱስትሪ መሣሪያዎች አሁን የእቅዱ አካል ናቸው” ሲል ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ መንግሥት የነዳጅ ወጪን ለመቀነስና የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲዎቹ ሳቢያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አጠቃቀም ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ሲገልጽ ሰንብቷል። አሁን የተጀመረው “ወደ ኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች” ሽግግርም የሎጂስቲክስ ዘርፉን ይበልጥ ዘመናዊና ወጪ ቆጣቢ እንደሚያደርገው ሚኒስቴሩ ገልጿል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

75,200 views

ታትሟል ኤፕሪ 19

ትራምፕ ልዑካቸው ለድርድር ወደ ፓኪስታን መጓዙን ገልጸው ንግግሩ ካልተሳካ የኢራንን ኃይል ማመንጫዎች እንደሚያወድሙ ዛቱ‼️ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ልዑክ ከኢራን ጋር ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር ወደ ፓኪስታን ማቅናቱን ገለጹ። በአሁኑ ድርድር አሜሪካ የምታቀርበውን ስምምነት ኢራን የማትቀበል ከሆነ በአገሪቱ የሚገኙ “የኃይል ማመንጫዎች እና ድልድዮችን እንደሚመቱ” ዝተዋል። ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኀበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ “የእኔ ተወካዮች ወደ ኢስላማባድ፣ ፓኪስታን እየሄዱ ነው። ነገ ማታ ለድርድር እዚያ ይሆናሉ” ብለዋል። አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን አሸማጋይነት ባለፈው ሳምንት ድርድር አድርገው የነበረ ቢሆንም ያለ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል። በመጀመሪያው ዙር ድርድር የአሜሪካ ልዑክ የተመራው በምክትል ፕሬዝዳንቱ ጄዲ ቫንስ ሲሆን የኢራን ተደራዳሪ ቡድን ደግሞ በአፈ ጉባኤው ሞሐማድ ባገር ጋሊባፍ ተመርቷል። ትራምፕ በዛሬው ጽሑፋቸው፤ “እጅግ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ ስምምነት አቅርበናል፤ እንደሚቀበሉት ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል። አክለውም ግን “የማይቀበሉት ከሆነ አሜሪካ ኢራን ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን የኃይል ማመንጫ እና ድልድይ ትመታለች” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። @Esat_tv1 @Esat_tv1

75,700 views
123•••5•••10•••15•••20•••25•••30•••35•••40•••45•••50•••55•••60•••65•••70•••75•••80•••8384
← ቀዳሚገጽ 1 ከ 84ቀጣይ →