TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Post content
Post content
ቭላድሚር ፑቲን በጋሞ በደረሰው ክስተት ሀዘናቸውን ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ውይይቱ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ፑቲን በጋሞ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በበኩላቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ "ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት አድርገናል" ሲሉ አጭር አስተያየት አስፍረዋል። #Ethiopia#ethiopiannews#Ethiopia_Russia#news#putin#PMAbiyAhmed#VladimirPutin#news#ዜና#ኢትዮጵያ#ሩሲያ#ጋሞ#ቦርከና_ዜና