TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #101

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች277የዕይታ ቁጥር
ታትሟልኦገስ 1010/08/2024 05:51 ከሰዓት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

ሮትራክት ምንድነው? ብላችሁ ለምትጠይቁ...ይህ ጽሑፍ ለእናንተ ነው። የሮታሪ ኢንተርናሽናል መርሆችን በመከተል እድሜያቸው ከ18-35 ባሉ ወጣት በጎ ፍቃደኞች የሚንቀሳቀስ ከማንኛውም ፖለቲካዊ እና ሐይማኖታዊ ተሳትፎ ነፃ የሆነ እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች የሚሰራ ክበብ ነው። ሦስት ነገሮች ሮትራክትን ልዩ ያደርጉታል:- 1) Service Above Self ይህ ከራስ በላይ ለማህበረሰብ የሚል መርህ ሮታራክተሮች 'ራስ ወዳድ' ከሆነ እና ለማህበረሰብ የማይበጅ ተግባር እንዲቆጠቡ የሚያስተምር ሲሆን። ለሰው ልጆችም ሁሉ የሚበጅ እንዲሁም በአከባቢያችን ያለን ማህበረሰብ የሚያግዙ ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ያበረታታል። በዚህም መሠረት ሮትራክት ኩሪፍቱ ባለፉት ሁለት አመታት የተለያዩ የደም ልገሳ መርሃግብሮችን በማዘጋጀት እንዲሁም የአረጋውያን መርጃ ማዕከላትን በማገዝ እና አቅም ላጡ የስራ እድል በመፍጠር ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። 2) Rotaract Opens opportunities ክለቡ ለአባላቱ ሞያዊ ክህሎታቸውን የሚያሳድጉበት እድል ይሰጣል። ይህም የሚሆነው በተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች እንዲሳተፉ በማድረግ እንዲሁም ክለባቸውን ራሳቸው እንዲያስተዳድሩ እድል በመፍጠር ነው። 3) Friendship እስካሁን ካየኋቸው አማራጮች ሮታራክት ጥሩ ጓደኞች ለማፍራት ቀላሉ ቦታ ነው። በስራዎቻቸው ላይ የሚደጋገፉ፣ አብረው የሚሰሩ እና ወዳጅነታቸው ከክለብ ያለፈ ሰዎች ተመልክቼበታለሁ። ከማህበረሰብ አገልግሎቶች በተጨማሪ የሚኖሩን የቡና ጊዜዎች እና የወዳጅነት ሰዓቶቻችን በደንብ እንድንተዋወቅ አግዘውናል። ጠቅለል ስናደርገው:- The purpose of Rotaract is to provide an opportunity for young men and women to enhance the knowledge and skills that will assist them in personal development, to address the physical and social needs of their communities, and to promote better relations between all people worldwide through a framework of friendship and Service. ሮትራክትን ለኔ እንደ ሁለተኛ ቤተሰቤ በሉት። ትልቅ ነጻነት የሚሰማኝ ቦታ ነው። የምትሰጡትን በፍቅር እና በፈግታ የሚቀበል። እሱም የሚሰጠው በዚያ መልክ የሆነ ክለብ ነው። once a rotaractor always a rotaractor! ይህ ለሁሉም አለም ይሰራል። የትም ሀገር ቤትሄድ ሮታራክት አለ። ሮታራክት ካለ አንተም ሮታራክተር ነህ። የእኛ ሮትራክት ኩሪፍቱ ደግሞ ነገ እሁድ በአሻም አፍሪካ ሆቴል እና ሪዞርት አሜሪካን ሀገር መቀመጫውን ካደረገው Osri University (https://www.facebook.com/OsiriUniversity) ጋር በመተባበር ያከብራል። ግራጫ ቃጭሎች የንባብ ቤት በጥበብ ስራዎች፣ ሂሊሲቲ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የእለቱ ድምቀቶቻችን ናቸው። ሁላችሁም ከ8:00 ጀምሮ ተጋብዛችኋል። ተማሪዎችን ለማገዝ የሚሆን ማንኛውም የትምህርት መርጃ መሣርያ ይዞ መምጣት ብቻ ነው። አደራ እንዳትቀሩ!