TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #119

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች270የዕይታ ቁጥር
ታትሟልሴፕቴ 1818/09/2024 09:13 ጥዋት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

Death in the air! አብዛኛዎቻችን 911 ንን እናውቀዋለን የ2001 የመንታ ህንፃዎች ጥቃት። በዚህ ጥቃት ማግስት ከ23 አመት በፊት ልክ በዛሬው ቀን በአሜሪካ የ5 ሰዎች ህይወት የቀጠፈ የሞት ደብዳቤ ለሴናተሮች እና ለሚዲያ ባለሞያዎች ደርሶ ነበር። ደብዳቤው ሞትን የሚያረዳ ሰይሆን እጅግ አሰቃቂ ሞትን በውስጡ የያዘ ነበር። የአንትራክስ ስፖሮችን! አንትራክስ፤ ባሲለስ አንትራክስ በተባለ ባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጣ ከባድ ተላላፊ በሽታ ነው። ባክቴሪያው ለመራባት እና ለመኖር ምቹ ያልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሲሆን ራሱን በጠንካራ ሽፋን በማልበስ ህይወቱን ያቆያል። ይሄ ዘዴ ' Sporulation' በመባል ይታወቃል። በዚህ ስልት ራሱን Dormant አድርጎ እስከ 40 አመታት ሊቆይ ይችላል። ብዙውን ጊዜ ጎርፍ እና ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት ለእኚህ ስፖሮች ከብቶች ተጋላጭ ስለሚሆኑ በበሽታው ይጠቃሉ። ሰዎች በአንትራክስ የሚጠቁት እኚህን ስፖሮች ወደ ሳንባቸው ሲተነፍሱ ፣ ከሚመገቡት ምግብ ጋር አብረው ወደ ሰውነታቸው ሲያስገቡት፣ ወይንም በአንትራክስ ስፖር የተበከለ ወሃ የጠጡ እንደሆን አልያም ክፍት በሆነ የቆዳ ክፍል ውስጥ ዘልቆ የገባ እንደሆን ነው። ባሲለስ አንትራክሲስ ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ ' Activate' ይሆናል። በፍጥነት በመባዛት እና ወደ ሰውነት ውስጥ በመሠራጨት መርዝ ይረጫል። ይህ እስከሞት ለሚያደርስ ከባድ የህመም ስቃይ ይዳርጋል። ወደ አሜሪካ የተላከው የሞት ደብዳቤ የያዘው እንግዲህ እኚህን ስፖሮች ነው። ደብዳቤውን ላይ ለእስራኤል እና አሜሪካ ሞትን የሚመኝ ጽሑፍ ሰፍሯል ደብዳቤው የተከፈተበት ስፍራ አየር በገዳይ ስፖሮች ተበከሏል። ደብዳቤውን ከከፈቱት መካከል 5ቱ ህይወታቸው አለፈ 17 የሚሆኑት ደግሞ በጽኑ ታመሙ። ይህ በአሜሪካ ታሪክ እጅግ ውስብስብ ከሆኑ የወንጀል ምርመራ ፋይሎች ውስጥ አንዱ ነው። ብዙ ሰዎች ተጠርጥረውበታል። ተጠርጣሪዎች በFBI ዱካቸው ሲጠና ራሳቸውን አጥፍተዋል ወይንም ተገድለው ተገኝተዋል። እስካሁን ግን የዚህ ትቃት ጠንሳሽ እና ፈጻሚ ማንነት እንቆቅልሽ ሆኖ 'Amerithrax' በሚል የወንጀል ምርመራ ፋይል ውስጥ ሳይፈታ ተቀምጧል። ስለ ባዮሎጂካል የጦር መሣርያዎች ካነሳን አይቀር ጣልያን ሀገራችንን ለማንበርከክ የሞከረችበትን ሌላ የባዮሎጂካል የጦር መሣርያ ማንሳት ግድ ይለናል። Rinderpest! (የደስታ በሽታ) በሽታው በከብቶች ላይ ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል አንዱ እንደ መፈንጠዝ ያለ ነውና የሀገሬ ሰው ደስታ ፣ ወተቴ እያለ ይጠራዋል። በቅኝ ግዛት ሙከራ ወቅት ጣልያን የባዮቴሬሪዝምን በሀገራችን ላይ እንዳደረሰች ይነገራል። በአፍሪካ ምድር የማይታወቀው Rinderpest ጣልያን ከኢትዮጵያ ጋር ለነበራት ውግያ ለወታደሮቼ ከቀለብ በሚል ሰበብ ካመጣቻቸው ከብቶች ጋር አብሮ ገባ። ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነ የሚያምኑ ፤ የለም ድንገቴ ነው የሚሉም አሉ። እኛ ጉዳቱ ለአላማቸው በር የከፈተ ነው እና የታቀደበት ነው እንላለን። በሽታው በአፍሪካ በ19ተኛው ክፍለ ዘመን መባቻ እጅጉን ተስፋፋ ለጣልያን እንዳሰበችው የኢትዮጵያ እግር ለማንበርከክ ከግዛቶቿ መካከል ካርታዋን ለመዶል ባይረዳትም ከአድዋ ማግስት ለተከሰተው የ "ክፉ ቀን" ረሃብ ግን የደስታ በሽታ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።የቅኝ ግዛት ቀንበርን ሰባብሮ ከጦር ጀብዱ የተመለሰው አርበኛ ገበሬው ነውና የእርሻ ቀንበሩን የሚያሳርፍበት የጦር ዜማውን እያዜመለት የሚያርስበት በሬው ተረፈረፈበት። በዚያ ዘመን እርሻ ያለ በሬ እንዴት ይሆናል? ጦርነት ነበር እና ጎተራም ሙሉ አይደለም። ሌሎች ችግሮች ተጨማምረው ቸነፈር ህዝቡን ገረፈው። ይህ የደስታ በሽታ ወደ አፍሪካ መግባት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ለቅኝ ገዢዎች ቀኝ እጅ ለአርበኞች ደግሞ ራስ ምታት ሆኖባቸው ነበር። ትግላቸው ከአፈ ሙዝ ከሚወጣ እሳት ጋር ብቻ አልነበረም። በጋሻቸው ከማይመክቱት ድንበር ከማያሰምሩለት ረቂቅ ተዋሲህ ጋር ጭምር እንጂ። በRinderpest በሚሊዮን የሚቆጠሩ ከብቶች አለቁ። ከብቶቹ በነበሩ ወቅት የሚሰማሩባቸው ጥጆች የሚፈነጩባቸው መስኮች ቁጥቋጦ ወረሳቸው። ቁጥቋጦው ለቆላ ዝንብ ሁነኛ መራቢያ ሆነ። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የቆላ ዝንብ በአፍሪካ ምድር የገንዲ በሽታን አዳረሰች። ሌላ ጉዳት ሊላ ሰቆቃ! ይህ አፍሪካን ለመቀራመት አውሮፓውያኑ ያሳረፉት አርፎ ሲነሳ ሰንበሩ ብቻ የሚታይ ረቂቅ ጅራፍ ነው! የሆነ ሆነ እና በሦስት በበሽታው የተያዙ ከብቶች ወደ ሀገራችን የገባው Rinderpest በሀገራችን ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የክትባት ግኝት አማካኝነት ከአለም ጠፍቷል። የክትባት ዘመቻውን የሚያስታውስ ሃውልትም በቢሾፍቱ በሚገኘው የብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ኢንስቲትዩት ተሰርቶለታል።