TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #181

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች711የዕይታ ቁጥር
ታትሟልሴፕቴ 909/09/2025 09:14 ጥዋት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

ይሄ ግድብ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ቀይ ኮፍያ አድርገው መጀመሩን ካበሰሩባት ቀን ጀምሮ ብሔራዊ ምልክት ሆኖ የኖረ ነው። የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ በየክፍላችን አዋጥተን ቦንድ እንገዛ ነበር። የትኛውም ክፍል ተማር ምን ያክል እንዲያዋጣ እንደተስማማ አይናገርም። ሚስጥር ነው። ኋላ ሁሉም ከጠዛ በኋላ ከፍተኛውን ያዋጣ በሰልፍ ወቅት ስሙ ይጠራል። ይደነቃል። ይህ በልጅ አእምሯችን ትልቅ ትርጉም ነበረው። I do remeber Section a won the competition by contributing the Max. It was Teacher Tewabech Aytenfisus Class and we were Jealous on them. የግድቡ Model ስዕል የሌለበት ትምህርት ቤት የለም። ቤታችን ተከራይቶ ከነበረ ሰአሊ ጋር በምዕራብ አባያ ወረዳ ባሉ ትምህርት ቤቶች የተሳሉ አብዛኛዎቹን ከረቂቅ ጀምሮ አይቻቸዋለሁ። ቀለም አቀብያለሁ። ስእሉ በግድግዳ ተስሎ ከጎኑ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አለማ ጋር ትልቅ ግርማ ነበረው። የመጀመርያ ትምህርቱን የጀመረ ምስሉ በአእምሮው ይቀመጣል የራሱ እንደሆነ ያምናል። ጉባ ሰፈሩ ትመስለዋለች የሚኖረውን ተርባይን ብዛት የሚያመነጨውን ሀይል መጠን ከሀሁ ጋር አብሮ ይሸመድዳል። በየአመቱ መጋቢት 24 የተጀመረበትን የሚያወሳ ዝግጅት በየትምህርት ቤቱ ይዘጋጅ ነበር። It was one of the greatest celebration in school, like Anti-AIDS day, ብሔር ብሔረሰቦች ቀን and ሰኔ 30። I used to sing 😂 MeMignot Ashenafi andHildana Andargacheww. የዛኔ ስማችን "እንጉርጉሮ ይብቃ" ነበር። በርግጥ በጣም ደፋር ነበርን። በዚህ ድምጽ ለመዝፈን ማይክ መያዝ። የዛኔ በየፈረቃው እየመጣን የጮህንባችሁ(የዘፈንላችሁ አልልም) ይቅር በሉን፣ የሀገር ጉዳይ ሆኖብን ነው። ይሄ ምልክታችን አልቆ ማየት ትልቅ ትርጉም አለው። ዘመን የሚሻገር ፣ የፖለቲካ መቀያየር ተጽእኖ የማያሳድርበት የሚዳሰስ ምልክት ነውና! ልጅ እያለሁ አባይ ቢገደብ ኖሮ መብራት ጠፍቶ ሰውለሰውን ከማየት እንደማልቀር አስብ ነበር። አሁንም ምኞቴ ከሱ የተለ አይመስለኝ። May this dam and other infrastructures bring prosperity for our Country! እንኳን ደስ አለን! ፎቶው ሁለት የሀገር ምልክቶችን አብሮ የያዘ ነው!