TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
ይዘት
የልጥፍ ይዘት
ሰውዬው ሳይሆን የተገነባው ስርአት ብርቱ ይሆናል። ምናልባት የነ ናፖልዮን ስህተት ይሄ ይመስለኛል። ሀገር የመለወጥ ቀናይነታቸው የሚጎመዥ እና ሊደረስበት የማይቻለው እንጂ ከእነሱ የመነጨ እንደሆ የማያስቡ የጦር ሀይሎች መገንባት። በጉዞ ላይ ሙሴን የመሆን ሞኝነት። (የእስራኤል መሪ ሙሴ ሳይሆን እግዜር ነውና፣ እግዜር የሌለው ሙሴ ምንድነው?) ስልጣን፤ የትኛውም አይነት ስልጣን የሚመነጨው ከተመሪው ነው። ለምሳሌ ንጉስ የማይከሰሰው ንጉስ አይከሰስም ሰማይ አይታረስም ብሎ በሚያምን ህዝብ ውስጥ ነው። አንባ ገነን ባለ ስልጣን የሚመራው ህዝቡ የሚያርፍበትን ጅራፍ የሚቋቋም ደንዳና ልብ ሲኖረው ነው። ስልጣን ከሃይል መንጭቶ አያውቅም። ለመኖር ሲል ሀይልን ይሁን ብሎ ከመቀበል እንጂ። ስለዚህ ስልጣኑን በሀይሉ ያመጣ የሚመስለው ንጉስ ሁሉ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሀሳቡን ሩቅ እያየ ከቅርብ መና ሆኖ ይቀራል። (ምንም ያህል ቢያይል) ስለዚህ የግድ ሰዎች ስልጣኑ ውስጥ ድርሻ እንዳላቸው የሚያምን እና ያን እንደሚያከብር የሚያሳይ። እየፈጸመ ያለው ሀሳብ የራሱ ሳይሆን የእነሱ መሆኑን የሚናገር መሪ ያስፈልጋል። በርግጥ ይሄ ቀላል የሆነ ፖለቲካው ጥበብ አይደለም😁 "ቡና እየጠጣህ ነው መሠለኝ፣ ይሄን እማ ቁጭ ብለን ማውራት አለብን፤ የት ነህ?"