የልጥፍ ይዘት
በበዓል ቀን ስለዶር እርባታ! በ1993ዓ.ም ስለ ዶሮ እርባታ የሚያትት ጥንቅቅ ያለ መጽሐፍ በአማርኛ ለኢትዮጵያውያን አመቺ እንዲሆን ተደርጎ መጻፉን ሳይ ተገርምያለሁ። ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው በዶ/ር ዓለሙ ያሚ ነው። ዶ/ር አለሙ የመጀመርያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከዓለማያ እርሻ ኮሌጅ በእንስሳት ሣይንስ ያገኙ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከቀድሞዋ ምዕራብ ጀርመን የጌቲንገን ዩኒቨርስቲ በእንስሳት ስነ ምግብና ፊዝዮሎጂ ተቀብለዋል። እኝህ ምሁር ከትምህርታቸው ባሻገር 1970-1986 ድረስ በዓለማያ ዩኒቨርስቲ (በአሁኑ አጠራር ሐረማያ ዩኒቨርስቲ) እንዲሁም በሃላፊነት እስከ ድህረ ምረቃ ዲንነት ያገለገሉ መሆናቸውን መጽሐፉ ላይ ያገኘሁት መረጃ ያሳያል። በመጽሐፉ ጥንቅቅ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። በተለይም የዘመናዊ ዶሮ እርባታ በሀገራችን የነበረውን አጀማመር ማወቅ ለሚፈልግ ሰው። እንዲሁም ሳይንሱን ሀገር በቀል እውቀት እና ሀብት ማዛመድ ለሚፈልግ ባለሞያ ወይንም አርቢ ከተጻፈ ከ25 ዓመት በኋላም እጅግ ጠቃሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ለዚህም የዶ/ር ዓለሙ በደብረዘይት ግብርና ምርምር ማዕከል በከፍተኛ ተመራማሪነትና በዶሮ ላይ የሚካሄደውን የምርምር ተግባር በብሔራዊ ደረጃ አስተባባሪ የነበሩ መሆናቸው። እንዲሁም ከ100 በላይ የምርምር ጽሑፎችን በተላያዩ ሳይንሳዊ ጆርናሎች ላይ ያሳተሙ ትልቅ ባለሞያ መሆናቸው አስተዋጽኦ እንደነበረው ግልጽ ነው። እንደ መጽሐፉ ገለጻ የዶሮ እርባታ ለገቢ ምንጭነት እንዲውል ከተፈለገ እንደ አንድ አትራፊ የሥራ ዘርፍ ሊወሰድ ይገባል። በልማድ በቀላሉ የሚከናወን ስራ አይደለም። ሳይንሳዊ የሆኑ እና ስፔሻላይዝድ የሆኑ መንገዶችን ልንከተል ግድ ይላል። በአሀገራችን ቀድሞ ይከናወን የነበረው በሀገር ውስጥ ዝርያዎች ምንም አይነት ግብአት ሳይኖረው ዶሮዎቹ በራሳቸው የሚያስፈልጋቸውን ምግብና ውሃ ፈልገው ራሳቸውን የሚንከባከቡበት እርባታ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለገበያ መቅረብ የሚችለው ምርት በጣም ጥቂት ነው። መጽሐፉ ሲዘጋጅ ድክ ድክ ይል የነበረው ዘመናዊ የዶሮ እርባታ አሁን እጅግ ብዙ ሰዎች ኑሯቸውን ያስመረኮዙበት ትልቅ እንደስትሪ እየሆነ መጥቷል። ከሌላው አለም አንጻር ገና ብዙ መጓዝ የሚጠበቅበትም ነው። ስለ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ካነሳን አይቀር የውጪ ዶሮዎች ዝርያዎችና የተሻሻለ የዶሮዎች አያያዝ ዘዴ ወደ ሀገራችን የገባው ቀደም ሲል በሚስዮናውያን አማካኝነት እንደሆነ መጽሐፉ ያትታል። እ.ኤ.አ ከ1953 ጀምሮ ደግሞ ዝርያዎችን የማስተዋቁ ስራ መሠራት ተጀምሯል። ይህም በጅማ ፣ ዓለማያ(ሐረማያ) ፣ ደብረዘይት (ቢሾፍቱ) የእርሻ ትምህርትቤቶች እና የምርምር ጣብያዎች መቋቋም ጋር የተያያዘ ነው። የዘመናዊ እርባታን ታሪኳዊ ዳራ በአጭሩ ካስቃኙን በኋላ ዶ/ር ዓለሙ ግዙፍ ወደሆነው ትዕግስት ፣ ጥረት እና እውቀት ወደሚፈልገው የዶሮ እርባታ ኢንደስትሪ ይዘውን ይዘልቃሉ። በአስራምስት ምነው ባለለቁ የሚያሰኙ የስራ ሞራልን በሚቀሰቅሱ ምዕራፎች ስለ ዘመናዊ የዶሮ ዝርያዎች እና ባህሪያቸው ፣ የዶሮ እርባታ አመሠራረት ፣ ለዶሮ እርባታ የሚሆን ቦታ አመራረጥ ፣ የዕንቁላል አፈጣጠር ፣ የዶሮዎች መኖ እና አመጋገብ፣ የዶሮዎች አያያዝ እና ሌሎች መሠረታውያንን ከረጅም ጊዜ ልምዳቸው እና ሳይንሳዊ እውቀታቸው እያያዙ ያስቃኙናል። የእውነት አጃኢብ እያልኩ እያነበብኩት ነው። ከዚህ በፊት ስለ ዶ/ር ዓለሙ ያሚ መረጃው አልነበረኝም። መጽሐፉንም ያገኘሁበት አጋጣሚ እጅግ አዝናኝ እና በአስገራሚ ገጠመኝ ነው። ዶ/ር ዓለሙ አሁን የት ናቸው? ስለሳቸው የምታውቁ እስቲ ይበልጥ አስተዋውቁን። ይህም መጽሐፍ ማሻሻያ ተደርጎበት እያደገ ላለው የዶሮ እርባታ ዘርፍ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ በድጋሚ ይታተም። ይህንን የመሠለ መጽሐፍ ላዘጋጁልን ታላቅ ምሁር ዶ/ር ዓለሙ ያሚ ባሉበት ምስጋናና አክብሮቴ ይድረስዎ🙏 መልካም በዓል💙 ያሬድ ኤርሚያስ @Campus_Voice_2016