TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #237

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች47የዕይታ ቁጥር
ታትሟልማርች 2727/03/2026 11:09 ጥዋት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

ዘመኑ ያለፈ ጋማው የረገፈ ፤ የጎድን አጥንቱ ፤ ማበጠርያ መሳይ ጠዋት ህያው ፍጡር፥ ሌሊት የጅብ ሲሳይ ከተማው መግቢያ ላይ አቧራ የሚቅም የተጣለ ፈረስ አጋጥሞሽ ፤ አያውቅም? “ካሁን አሁን መጥቶ፤ ይወስደኛል ነድቶ ከጋጣው አግብቶ ፤ ያበላኛል እብቅ “ እያለ ጌታውን ፥ተግቶ የሚጠብቅ የዛሬ ተጎታች ፤ የትናንቱ ሰጋር ተባብሮ የከዳው፤ ጊዜ ከጌታው ጋር የቸገረው አቅም፥ የተጣለ ፈረስ ፤ አጋጥሞህ አያውቅም? ደሞስ መች ይጠፋል? ካንቺም ከኔም መንደር የቀድሞ ወታደር፥ በጨነቀን ጊዜ ፥“በናት ሀገር ጥሪ “ የምናጣድፈው፥ በድል ቀን ከድግስ፥ የማናሳትፈው ከነጣቂ መዳፍ ፥ አገር የሚያስመልስ በገዛ አገሩ ላይ፥ መብቱ ከወፍ አንሶ፤ ጎጆ የማይቀልስ፤ ደሞ መች ይጠፋል፤ ከኔም ካንተም ቀየ መንገድ ላይ ምናልፈው፥ አይተን እንዳለየ የቀድሞ አስተማሪ ላብ እያጣቀሰ ፊደል አስቆጣሪ ቀሪ ሀብት ባይኖረው፤ የቀረውን ዘመን፤ እያሰላ ኗሪ፤ ቪላችንን ሞልተን፥ በሱ ጎጆ ጉድለት ማሰብ አስተምሮን ፥ የማናስበለት ቀኖቹን በትኖ፤ ሌሊቶቹን ዘርቶ ናላውን፥ ጉልበቱን ፥ ውበቱን ሰውቶ የሚጎተት አገር፥ ከግቡ ለማድረስ ሺህ መንገድ አቅንቶ፥ ሺህ ገደሎች መውረስ ሰው ቢሉት ሰው ነው ወይ? የተጣለ ፈረስ :: የተጣለ ፈረስ (በእውቀቱ ስዩም)