TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #61

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች344የዕይታ ቁጥር
ታትሟልኤፕሪ 1717/04/2024 05:25 ከሰዓት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

የማስታወቅያ ሐይል! I took a wonderful lesson from Professor Alemayehu Today. በአአዩ በሚገኘው ኮሌጃችን በየ 15 ቀኑ በተለያዩ በሞያቸው ትልቅ ልምድ ባላቸው መምህራኖቻችን እና ተመራማሪዎች ሴሚናሮች ይቀርባሉ። እስካሁን መገኘት የቻልኩባቸውን ሁሉ የተሳተፍኩ ሲሆን በተለይ በእንስሳት ፣ በጤና እና ተዛማች ጉዳዮች ከሀገር ውስጥ እንዲሁም ከውጪ በመጡ ምሁራን በቀረቡ የጥናት ጭምቀ ሀሳቦች ብዙ ነገር ተገንዝብያለሁ። ክፍል ውስጥ ከምማረው በላይ በሚያነቃቃ እና ለመመርመር በሚያጓጓ መልኩ የቀረቡ ናቸው ብል ማጋነን አይሆንም። በተጨማሪም በቀረቡት ጽሑፎች ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች የሚነሱ ጥያቄዎች እና ክርክሮ ደስ የሚል ጣዕም ያላቸው እና የእኔንም የማወቅ ፍላጎት ያሳደጉ ናቸው። እንዲህ ያሉ ሞያዊ ውይይቶች እና ክርክሮች ደስ ይላሉ! ወደ ዋና ጉዳዬ ስመጣ ዛሬ በፕሮፌሰር አለማየሁ የቀረበው ሴማናር መነጋገርያ የሆነው ገና ማስታወቅያው ከተለጠፈበት ጊዜ ጀምሮ ነበር። "Weird Science" ይላል። Everyone was wondering which part of science is weird. ሰአቱ እየቀረበ ሲመጣ ሰዎች ከፕሮፌሰሩ የእውቀት አድማስ በመነሳት የተለያዩ ግምቶቻቸውን ሲሰነዝሩ ነበር። እኔ እና የድህረ ምረቃ ትምህርቷን በማይክሮ ባዮሎጂ እያጠናች ያለች ወዳጄም ግምታችንሰ ስንከራከርበት ነበር። She said " Microbiology is the weird science" ለራስ ሲቆርሱ ተባብለን ተቀላልደናል። ፕሮፌሸር ገና አዳራሽ ውስጥ ሳንገባ ቀልባችንን ወስደውት ነበር። ዋና ሊነግሩን የፈለጉትን ሀሳብ ሸሸግ አድርገው ብዙ እንድንወያይ ብዙ እንድንጠብቅ አድርገውናል። የማስታወቅያ ሀይል ይህ ነው። -የተደረሳሲን የትኩረት አቅጣጫ ማወቅ። -አእምሮ ውስጥ ጥያቄ መፍጠር። -የጠየቁትን ትያቄ መልስ ማግኛ ቦታው መርሃ ግብሩ ብቻ እንደሆነ እንዲያስብ ማድረግ። Don't judge a book by its cover ቢባልም የሚስብ እና ጥያቄ የሚፈጥር ልባድ ያለው መጽሐፍ ግን ቶሎ የመሸጥ እድል አለው። ፕሮፌሰር ሀሳቡን ምን እንደሆነ ሳናውቅ ነው የሸጡልን። እንደገመትኩት አዳራሹ በሰው ተሞልቶ ነበር። ብዙ ሴሚናር የማይገኙ አዳዲስ ፊቶችም አይቻለሁ። ልክ የሴምናሩ ሙሉ ርዕስ በማቅረብያ ስክሪኑ ሲከፈት በፕሮፌሰር አለማየሁ ለማ weird የተባለውን ሳይንስ አወቅን። የአጥቢ እንስሳት ስነ ተዋልዶ ጉዳይ ነው። እርሳቸው ደግሞ በዚህ ዘርፍ ከሀገር ተርፈው ለአለም ብዙ ያስተማሩ ናቸውና የሚነግሩንን ለመስማት ጆሯችንን አቆምን። የሚናገሩትን ያውቃሉና አላሳፈሩንም። እጅ በአፍ አስይዞ የሚያስቅ የሳይንስ ጉድ ሰምተን ተወያይተንበት ወጣን። ዋናው ልነግርህ የፈለኩት ነጥብ በእጅህ ያለውን ሀሳብ እንዴት አንድርገህ እንደምታስተዋውቀው አስበህበታል ወይ ነው! የያስከው ሀሳብ ምንም ጥኡም ቢሆን ሳቢ በሆነ መንገድ አዘጋጅተህ ጥሱ ማስታወቅያ ሰርተህ ሰሚ ጆሮ ካላዘጋጀህለት መና ይቀራል። ሁሌም ስለ ራስህ፣ ስለ መረጃህ፣ ስለ ምታውቀው ነገር እና ስለ ጥቅሙ የምታስተዋውቅበትን መንድ በሚገባ አስብበት። "Don't judge a book by its cover, but when you're writing a book, it should have a cover that can be judged!" ቸር ያቆየን