የልጥፍ ይዘት
ሞ! ጂም የሚሄድ የCVMA ተማሪ ስለማን እንደጻፍኩ ይገባዋል😅🔥 በደዘ ወጣቶች ስለሚወደደው እና እጅግ ስለሚከበረው ሰው ልንገራችሁ። ደዘ ቢሾፍቱ ነች። የሚወዷት የቀድሞ መጠርያዋን አሳጥረው ደዘ አልያም ቢሼ እያሉ አፋቸው ላይ ያጣፍጧታል። ምርጥዬ ከተማ ነች። የሰባት ሀይቆች እመቤት፣ የኤረር ተራራ ግርጌ፣ ከዋሽንት የሚፈልቅ የሚመስለው ነፋሷ ነፍስን የሚዳስስ ነፍስ የሆነች ከተማ። ሞ! የስፖርት ሰው ነው። ከተማዋን ያስጠራ የቦክስ ተወዳዳሪ። ስፖርት እጅግ በጣም ይወዳል። ልጅነቱ ከጀግኖች የሀገር ወታደሮች ጋር ያሳለፈ በመሆኑ ስፖርትን እና ዲሲፕሊንን አብሮ ይዟል። ካገኘሁት ጀምሮ ትንሽ ትልቁን ያከብራል። ትንሽ ትልቁ ያከብረዋል። ከተማ ውስጥ "ብርት መግፋት ያስጀመረኝ ሞ ነው" ፣ "ኳስ መጫወት የወደድኩት ሸማኔ ሜዳ ነው "የማይል ወጣት መኖሩን እንጃ። የከተማዋን ልዩ ትዝታዎች አንጣላ ከያዘችው ሸማኔ ሜዳ ጀርባ ሞ ጂም አለችው። እዛች ጂም ውስጥ የሚፈረጥመው ጡንቻ ብቻ አይደለም። ስብዕና ይገነባል፣ ታላቅን ማክበር ባህሪ ይሆናል፣ ታናሽን ማስተማር ባህል ነው። ያቺ ጂም አክብሮ የሚከበር ወጣት መፍለቅያ ነች። ይህ የሆነው ደግሞ በ ሞ! ነው። ማሞ። ማሞ ከድር። ለደብረዘይት ወጣትና ስፖርት ትልቅ ዋጋ የከፈለ ጀግና ሰው! ሞ! አቀርቅረህ እንድትራመድ አይፈልግም። ቀና በል ወንድ ልጅ ነህ ይልሃል። ሞ ቀጥነህ አልያም ቦርጫም ሆነህ ማየት አይፈልግም። መንገድ ላይ እንዲያ ሆነህ ቢያይህ ነገ ቀጥ ብለህ ጂም ና ይልሃል። ሞ! ስፖርት ትጥቅ ሳትለብስ ጂም ስትመጣ ማየት አይፈልግም። ለስፖርት ክብር ይኑርህ ይልሃል። ሞ! ከፍያለሁ ብለህ ባሻህ ሰአት መጥተህ ባሻህ ሰአት ጂም እንድትቀር አፈቅድልህም። ዲስፕሊን ከሌለህ ምን ጥቅም ይልሃል።ስትሳሳት ያርምሃል፣ ስፖርት ሰራሁ ብለህ ሰፈር ብትበጠብጥ ያስጠነቅቅሃል። ብቸኛ ከሆንክ ጓደኛ ይሰጥሃል።ይህን ሁሉ ሲያደርግ ደስ እያለው ነው። የሚቀመጥባት ቦታ አለች። ገና ወደ ግቢው ስትገባ ፊትለፊት ታየዋለህ። ግርማ ሞገስ አለው። ሰላምታ ይሰጥሃል። የጁምኣ ቀን ከሆነ ነጭ ጀለቢያውን ለብሶ ድምቅ ብሎ ይቀመጣል። ከውጪ ሆነው የሚሰሩትን እየተመለከተ ያርማል። በቃ መኖሩ ብቻ ድባብ የሆነ ሰው ነው። ወደዛች ጂም በሄዱኩባቸው ጊዜያት ሁሉ ስለ Social wealth አሰላስያለሁ። አንዳንድ ሰዎች ሀብታቸው ሰው ነው። በለ ግዙፍ ስብዕና ናቸው። የሚወደዱት ስለሚወዱ ነው። የሚከበሩት ስለሚያከብሩ ነው። የሚፈሩት ከመውደድ በመነጨ ፍርሃት ነው። Social wealth ካሉት አምዶች መካከል ሦስቱ Strong social network, High level of social influence and Supportive relationship ናቸው። እነሲህ አምዶች ሰው ሆነው በማሞ ከድር ተገልጠዋል። ሞ ያለው ሀብት ብዙ መሪዎች ቢኖራቸው የተመኘት ነገር ግን ያልታደሉት ነው። ሰሞኑ ከዚህ ሰው የተማርኳቸው ነገሮች ጭንቅላቴ ውስጥ ተመላለሱ እና ልጽፍ ወደድኩ። ቆይ አንድ የማጋራችሁ ጽሑፍ አለኝ! እስከዛ የሞን ታሪክ በዚህ ቃለ ምልልስ ከአንደበቱ አድምጡልኝ🙏 https://youtu.be/8NRm6rF5B68?si=1dA_QYQmjO5qlavk