TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← #HaSab
#HaSab avatar

TGINSIGHT POST

Post #76

@Hasab_2016

#HaSab

ዕይታዎች63የዕይታ ቁጥር
ታትሟልሜይ 1212/05/2024 09:19 ጥዋት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

ሌላው ከሚመታህ እኔ ልምታህ! አንድ ቀን ጂሙ የሰውነት ቅርጻቸውን ለማስተካከል በሚለፉ ወጣቶች በተሞላበት ሞ! ወደ ውስጥ ገባ። ሞ ማነው እንዳትለኝ! ግራ ከገባህ የትናንት ፖስቴን ግባ እና ተመልከት። "ሰውነት ያለ ቴክኒክ ምን ያደርጋል?" ሁላችንም ዞር ብለን ተመለከትነው። ሞ ስፖርት የሰውነት ቅርጽ ብቻ ሳይሆን የቴክኒክ እውቀቶችም ሊኖርት እንደሚገባ ያምናል። ስፖርት ሰርቶ ሰውነቱ ደንዳና የሆነ ነገር ግን ቢሰነዘር መከላከል የማይችል ሲሰረቅ ለነፍሴ ብሎ ቆሞ የሚያይ እንዲኖር አይፈልግም። ጥሩ የቦክስ ውድድር ልምድ አለው። ከተማዋን ወክሎ አሸንፈቀል። ያለውን ልምድ በነፃ ሊያካፍለን በነፃ መሰረታዊ የቦክስ ቴክኒኮችን ሊያሰለጥነን መወሰኑን እና እንድንመዘገብ ነግሮን ወጣ። ደስ ብሎን ተመዘገብን። አንተ! ቦክስ የዋዛ ስፖርት እንዳይመስልህ። የሰውነት ጥንካሬ እና ቅልጥፍናን፣ የአእምሮ ፈጣን መላሽነት እና አስተውሎትን እንዲሁንም በተገጣሚው እንቅስቃሴ መሰረት ፈጣን ብልሃቶችን መዘየድን ይጠይቃል። የምንግዜም ምርጥ ከሚባሉት ስፖርተኞች መካከል የሚመደበው አሁን ጓንት የሰቀለው አሜሪካዊው professional Boxer Floyd Mayweater Jr. "Boxing is not about your feeling. Its about performance" ይላል። ይህም Mindsetቱ የተገነባባበት መሠረት እንደሆነ ይናገራል። Mayweater በመከላከል ብቃቱ ፣ ፍጥነቱ እና ከተጋጣሚው ለሚደርሱት ስንዘራዎች ፈጣን ምላሾች(Counterpunching) የሚታወቅ ሲሆን ይህ ሊገነባ የሚቻለው ከውጪ በሚመጣ ጊዚያዊ Motivation እና ሞራል በላይ በልምምድ፣ ዲሲፕሊን እና በቂ ዝግጅት መሆኑን በጽኑ ያምናል። ወደ ቀድሞ ነገራችን ስንመለስ ይሄ ሁሉ የገባኝ በመጀመርያው ቀን ነው። የተጨበጠ ቡጢ ለመሰንዘር ብቻ ሳይሆን አይን እና አገጭን ለመከላከል እንደሚጠቅም መች አውቄ? ቡጢ ለመሰንዘር የእግር እንቅስቃሴ ሳይቀር ወሳኝ እንደሆነ መች አስቤ? ወላ ለቦክስ ትንፋሽ እንደሚያስፈልግ ታውቃለህ? አንድ ሁለት ቴክኒኮችን ስሜታዊ ሆነህ እንደሞከርክ፤ ሳንባህ ይሄ ልጅ አላኖረኝም ካልወጣሁ ይላል። ልብህ የአውሊያ ቤት ድቢ ያስንቃል። እጅህ ይከዳሃል። ቢሆንም ቢሆንም ደስ ይላል። ሞ! ታድያ በእጁ ላይ ባጠለቀው ጓንት የነገረንን ቴክኒክ እንድንሞክር ያደርጋል። ትኩረታችን መሠንዘር ላይ ሆኖ መከላከል ሲዘናጋን በክፍተቷ ተጠቅሞ ይመታናል። ታድያ ከዚህች ምት በኋላ ሁሌ የሚናገራት ቃል አለች። "ዋ! ሸፍነህ ሰንዝር። እመታሃለው! ሌላው ከሚመታህ እኔው እዚህ ብመታህ ይሻላል"😂 ይህቺ አባባሉ ደስ ትለኛለች! አሁን አሁን ብዙዎቻችን የምንፈልገው ከሚነቅፈን ይልቅ የሚያሞግሰንን፣ ስራችን ላይ አሉታዊ አስተያየት ካለው ይልቅ በጭፍን የሚያደንቀንን እየሆነ የመጣ ይመስለኛል። በ 'አንቂዎቻችን' የምናደርገው ልክ እንዳልሆነ ከሚነግሩን ሰዎች እንድንርቅ ተመክረናል። በአንድ በኩል ምንም ብንሆን ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች አሉ። ወዲህ ደግሞ ክፍተታችንን ሲያዩ እንድንሸፍነው የሚመቱን እንደ ሞ! ያሉ ሰዎች አሉ። ግሳጼ ደስ የሚል ስሜትን የሚፈጥር ነገር አይደለም። እኚህ ሰዎች ሊሰብሩን ሳይሆን ስለ ስብራት እንዲገባን የሚጎስሙን ናቸው። እድገታችንን የሚሹ። ያለን ክፍተት ቡጢ የምንቀምስበት እንዲሆን የማይፈቅዱ። እነሱ በተመቱበት እንዳንወድቅ የሚጥሩ። ግሳጼያቸው፣ ቁጣቸው ለብርታት የሆነ። በህይወታችን ውስጥ እንዲህ ያሉ ሰዎች ያስፈልጉናል። በሰዎች ህይወት ውስጥ እንዲህ ያለ ሰው መሆን ይገባናል። ሰላምህ ይብዛ ሞ! ቸር ያቆየን