የልጥፍ ይዘት
Dosis Sola facit Venenum ከ500 አመት በፊት አጀብ ያስባለ ጽንሰ ሀሳብ ነው። ምክንያቱም ከጥንት ጀምሮ በገፍ የተሰጠ ጥሩ ነገርን የመሠለ ምንም የለም የሚል እሳቤ አለ። ከላይ የጠቀስኩት ጽንሰ ሀሳብ ይህንን የናደ ይመስላል። የእንግሊዝኛ አቻው "The Dose makes the poison" ማለት ነው። በጤና ዘርፍ የተማራችሁ ወይንም Toxicology የማጥናት እድል ያገኛችሁ በደንብ ታውቁታላችሁ። የToxicology ሀሁ ነው። ወደ አማርኛ ስንተረጉመው 'መርዙ የወሰድከው ነገር ሳይሆን የወሰድክበት መጠን ነው።' እንደማለት ነው። ቆጣ ያለ የአባት ምክር አድርገን ከገለጽነው ደግሞ በሁለት ቃል: 'ልክህን እወቅ!' የሃሳቡ ባለቤት Paracelsus ይባላል። ሙሉ ስሙ የጀማሪ ግጥም ነው የሚመስለው። phillippus Aureolous Theophrastus Bombustus Von Hoheneim. ያው ቤት ግን አልመታም። ሰውዬው በዘመኑ የነበረው የትምህርት ስርአት ስልችት ያለው አፈንጋጭ ነበር። ትኩረቱን በሳቡት ነገሮች ላይ እስከ ጥግ አንብቧል፣ ተመራምሯል ፣ የተሻለ እውቀት ፍለጋ ከተወለደባት ሲውዘርላድ ተነስቶ አውሮፓን ዞሯል። ዋና ትኩረቶቹ ህክምና ፣ ኬሚስትሪ ፣ ፍልስፍና እና ስነ ከዋክብት ነበሩ። በእነዚህ ዘርፎች ብዙ የተናገራቸው ግራ አጋቢም እውቀት ገንቢም ነገሮች አሉ። ከእነዚህ መካከል አሁን እያወራንበት ያለው ጽንሰ ሃሳብ አንዱ ነው። The Father of Toxicology አስብሎታል። በህክምናው ዘርፍ Groundbreaking የምንለው አይነት ጽንሰ ሃሳብ ነውና። ሀሳቡ በዋናነት ለሁለት ነገር ትልቅ ጥቅም የሰጠ ነው። የመጀመርያው:- it described the phenomenon in which poisonous substances can be medicinal in small dosage. መጠን ከሆነ መርዝን መርዝ ያደረገው መርዝም መድሃኒት ሊሆን ይችላል እንደማለት ነው። ለምሳሌ hydrogen peroxideን እንመልከት የጥርስ ሳሙናችን ውስጥ የሚገኝ Chemical ነው። አፋችን ውስጥ ያሉ ባክቴሪያዎችን ለመግደል ይጠቅማል። ይህ ኬምካል ግን መጠኑ ከፍ ብሎ ወደ ሰውነት ሲገባ መርዛማ ነው። ሊገድልም ይችላል። ልኩን እስካወቅን ግን 'አያሳስብም' ሌላኛው የዚህ ጽንሰ ሃሳብ ትልቅ ጥቅም:- its a base for public health standard , which specify maximum concentration in food , public drinking water, and the environment. ለምሳሌ ከዚህ በፊት ስለ አፍላቶክሲን ጽፌላችሁ ነበር። አፍላቶክሲን ለካንሰር አጋላጭ ነው። ይህ መርዛማ ኬሚካል በወተት አልያም በእንስሳት መኖ ላይ ሊገኝበት የማይገባ መጠን አለ። ከዛ መጠን ካለፈ አደጋ አለው። መጠኑን እስካልተሻገረ ግን ችግር የለውም። እንደ እውነቱ ከሆነ 'ዜሮ የአፍላቶክሲን መጠን ያለበት ምግብ' ለማለት ይቸግራል። መጠኑን እስካወቅን ግን 'አያሳስብም' አኔ ደግሞ አንድ ልጨምር። ፍካሬያዊ ፍቺ በሉት። የAI ነገር። አሁን አሁን በብዙ ተማሪዎች ጥቅም ላይ ሲውል እንደማየቴ ያሳስበኝ ጀመሯል። ያሳሰበኝ መጠቀሙ አይደለም። እንደ እውነቱ ከሆነ እኔም ወድጄ የምጠቀመው እና የማደንቀው ፈጠራ ነው። ችግሬ ከመጠኑ ነው። የምንጠቀምበት መጠን የፈጠራ ችሎታችንን እንዳያቀጭጨው እፈራለሁ። ጭንቅላታችን ጉልበት ማባከን የሚወድ አይደለም። ቶሎ እፎይ ማለት ይፈልጋል። በቶሎ በሚገኝ እፎይታ አንዳንዴ በመሥራት ሂደት ውስጥ የምናገኛቸውን 'ኢዮሪካ' የሚያስብሉ ሀሳቦች ልናጣ እንችላለን። ምንም ቴክኖሎጂ አጀብ የሚያስብልበት ዘመን ላይ ብንሆን አሁንም አቧራ በለበሱ የላይብረሪ መጽሐፍት ውስጥ እልፍ እውቀቶች፤ ያልተጨመቁ እንብበን ስንጨርስ በሚገርም ሁኔታ ጨምቆ የመረዳት ክህሎት የሚሰጡ ሀሳቦችን እናገኛለን። ምን ጊዜ ቢከንፍ እኔ እና ቤቴ ግን ቁጭ ብሎ ማሰላሰል የሚበጅበት ጊዜም አለ ብለን እናምናለን። ስለዚህ በፍጥነት መጓዝን እና ፈጠራ የታከለበት ማዝገምን ማመጣጠን ከኛ የሚጠበቅ ነው። መጠኑን እስካወቅን ግን 'አያሳስብም' Bona nocte!