TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
ይዘት
የልጥፍ ይዘት
የ15% ነገር ሲሆን ሲሆን ድጋፍ እና ማበረታቻ የሚያስፈልገው ነበር። የእንስሳት እርባታው ዘርፍ ከምን ጊዜውም በላይ መነቃቃት እያሳየ ያለበት ወቅት ነው። በተለይ ለወጣቱ የስራ እድል በማድረግ እና የወር ደሞዝ የለት ጉርስን ለመሸፈን የሚያጥረውን እጅ ለመደገፍ ብዙዎች ወደ እንስሳት እርባታ ፊታችውን አዙረዋል። ያላቸው ላይ ተበድረው ሳይቀር ወደ ስራው ተሰማርተዋል። በተለይ የዶሮ እርባታ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። የእንስሳት እርባታ ትልቁ ወጪ ያው እንደምትገምቱት መኖ ነው። እስከ 70% የወጪ ክፍልን ሊይዝ ይችላል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ታድያ እንዲሁም በተወደደ የመኖ ግዢ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጨመር ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ይመስለኛል። ገና በመቀጣጠል ላይ ያለ የእሳት ብርሃን እፍ አይባልም። ሲሆን ሲሆን ከነፋስ ይጠብቁታል እንጂ። እንደ አንድ ዘርፉ እያሳየ ያለውን መነቃቃት ፣ ለወጣት እየፈጠረ ያለውን የስራ እድል እና እየደገፈ ያለውን የገቢ ምንጭ እንደሚደግፍ ሰው። በእንስሳት መኖ ላይ የተደረገው የተጨማሪ እሴት ታክስ ጭማሪ ጉዳቱ አልተስተዋለም እላለሁ። ያሬድ ኤርሚያስ ከተማሪነት በላይ ለለውጥ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ