TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← JIFAR CAREER
JIFAR CAREER avatar

TGINSIGHT POST

Post #117

@JIFAR1

JIFAR CAREER

ዕይታዎች271የዕይታ ቁጥር
ታትሟልጃን 2828/01/2025 07:35 ከሰዓት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

ጥንቃቄ #CBE አደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ‼️ ከጫናችሁ ያለፈቃድ ገንዘብ ይቆረጥባችኃል! ደንበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳስቧል። ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል። ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል። መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል። ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል። ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።