የልጥፍ ይዘት
🔶አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስለ ገጽታቸው መቀየር ማብራሪያ ሰጡ። የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሰሞኑን በነበረው የኮፕ 32 ዝግጅት ግምገማ ወቅት ገጽታቸው ተቀይሮ መታየታቸው ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ነበር። ምን ሆነው ነው ? የሚል ጥያቄም ሲነሳ ቆይቷል። አምባሳደር ሬድዋን ማብራሪያ ባለመስጠታቸው የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ግምታዊ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ነበር። ዛሬ አምባሳደር ሬድዋን " ደረሰብኝ ስላሉት " ጉዳይ መረጃ አጋርተዋል። ምን አሉ ? " ከሁለት ሳምንታት በፊት በሀገራዊ ጉዳይ የሚመክር ስብሰባ አስተናግደን ለምሳ እንዳረፍን ንፋስ ለመከላከል የተጋረደ የእንጫት አካፋይ ( Partition Wall ) ሚዛን ስቶ ሲወድቅ አናቴ ጋርና ትንሽ ገባ ብሎ አገኘኝ። ስንጥቁ መሰፋት ስለነበረበት ሀኪሞች በከፊል ላጩት። እኔ ደሞ ሙሉውን ቢሆን ይሻላል ብዬ እስከሚደርቅ አነሳሁት። እንደልጅነቴ ተመልጬ ሳየው አልጠላሁትም። ወዳጆችም እንዲያውም ሸጋ ነው አሉኝ። በተመልካች አስተያየት ተበረታትቼ ትንሽ ደሞ በአዲስ መልክ ልሞክረው ብዬ ዘለቅኩበት። የሆነው ይኽው ነው። የታከምኩትም አሚን ሆስፒታል ነው።እናማ እንኳን ለህክምና ለስራም ወደ ውጭ ሀገር አልወጣሁም። ምንም ያልተባለውም ምን አዲስ ነገር አለ በሚል ነው። ለማንኛውም ለተጨነቁት ምስጋናና አክብሮቴ ይድረስ " ብለዋል። Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1