የቅርብ ጊዜ ልጥፎች
ገጽ 1 ከ 21 · 252 ልጥፎች
ታትሟል ከ27 ቀናት በፊት
🔶ብሩኖ ፈርናንዴዝ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ በእግርኳስ ፀሀፊዎች ማህበር የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝን የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል፤ከ 2010 በኋላ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ያገኘ የመጀመሪያው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሆኗል። ሁለተኛ ዴክላን ራይስ እንዲሁም ሶስተኛ ሀላንድ በመሆን አጠናቀዋል። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 27
🔶የዳናዊት መክብብ የባንክ አካውንትና ንብረት ታገደ ታዋቂዋ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢና የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ዳናዊት መክብብን ጨምሮ በአምስት ተከሳሾች ላይ ተመስርቶ የሚገኘውን የአጭበርባሪነት ክስ ተከትሎ፣ የንብረትና የባንክ ሂሳብ እግድ መጣሉ ተሰምቷል። እንደ ኢትዮጲካንሊንክ ዘገባ፣ ዳናዊት መክብብና ሌሎች አራት ግለሰቦች የተከሰሱት "ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን" በሚል ከ13 ከሳሾች እያንዳንዳቸው 437 ሺህ ብር ተቀብለው ሳይልኩ ቀርተዋል በሚል ነው። ይህንኑ የክስ ሂደት መሠረት በማድረግ የቦሌ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 4ኛ ፍትሐብሔር ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ፣ የተከሳሾቹ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እንዲሁም የባንክ ሂሳቦች እንዲታገዱ ተደርጓል። የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ለፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ሰነድ መሠረት፦በአንደኛ ተከሳሽ ቤተልሄም ታደሰ ስም በኮልፌ ቀራኒዮ ቅርንጫፍ የተመዘገበ አውቶሞቢል፤ በሁለተኛ ተከሳሽ ዳናዊት መክብብ ስም በልደታ ክፍለ ከተማ የተመዘገበ አውቶሞቢል መታገዳቸው ታውቋል። በተጨማሪም ባንኮች ለፍርድ ቤቱ በላኩት መረጃ መሠረት፣ በዳናዊት መክብብ የባንክ ሂሳብ ውስጥ የሚገኝ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጓል። በቀሪዎቹ ሦስት ተከሳሾች ስም ግን እስካሁን የተገኘ ንብረትም ሆነ የባንክ ጥሬ ገንዘብ አለመኖሩ ተጠቁሟል። ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ቀጣይ ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙ ታውቋል። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 27
🔶በፌስቡክ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸው የአፍሪካ መሪዎች በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ መሪዎች ከመደበኛው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን በበለጠ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ከዜጎቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እያጠናከሩ ይገኛሉ። በቅርቡ የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው፣ መሪዎቹ የሥራ አፈጻጸማቸውንና አገራዊ መረጃዎችን ለሕዝብ ለማድረስ ፌስቡክን ዋነኛ መድረክ አድርገውታል። በአህጉሪቱ በፌስቡክ ገጻቸው ከፍተኛ ተከታይ በማፍራት የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል-ሲሲ በ12 ሚሊዮን ተከታዮች ቀዳሚነቱን ይዘዋል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በበኩላቸው በ6.8 ሚሊዮን ተከታዮች በአህጉሪቱ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካላቸው መሪዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። በምሥራቅ አፍሪካ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በ3.9 ሚሊዮን ተከታዮች የዲጂታል ተደራሽነታቸውን እያሰፉ ሲሆን፣ በደቡባዊ አፍሪካ ደግሞ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀካይንዴ ሂቺሌማ በ2.2 ሚሊዮን ተከታዮች ተጠቃሽ ናቸው። የጋናው ጆን ድራማኒ ማሃማ (1.8 ሚሊዮን) እና የሩዋንዳው ፖል ካጋሜ (1.7 ሚሊዮን) ተከታዮችን በማፍራት ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል። በምዕራብ አፍሪካ የሴኔጋሉ ኡስማን ሶንኮ በ1.4 ሚሊዮን ተከታዮች ከፍተኛ እድገት እያሳዩ ሲሆን፣ የቦትስዋናው ዱማ ጊዴዎን ቦኮ እና የኮትዲቯሩ አላሳን ዋታራ እያንዳንዳቸው 1.3 ሚሊዮን ተከታዮች አሏቸው። የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ በበኩላቸው በ1.1 ሚሊዮን ተከታዮች በአህጉሪቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ መሪዎች ተርታ ተመድበዋል። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 27
🔶የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል። በዛሬው ዕለት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ1.3% ጭማሪ አሳይቶ በበርሜል 106.68 ዶላር ሲገባ፣ የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ደግሞ በ1% አድጎ 95.35 ዶላር ደርሷል። ይህ የዋጋ ንረት የታየው በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የነበረው የሰላም ተስፋ በመዳከሙና ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ የባህር መስመር ላይ የንግድ ፍሰቱ በመገደቡ ነው። የዲፕሎማሲው ጥረት መጓተቱ የታወቀው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የልዩ መልዕክተኞቻቸውን የፓኪስታን ጉዞ መሰረዛቸውን ተከትሎ ነው። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በሆርሙዝ ስትሬት ላይ ፈንጂ በሚጥሉ የኢራን ጀልባዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ በሰጡት ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ምክንያት በገበያው ላይ የጦርነት ስጋት እንዲነግስ አድርገዋል። በአሁኑ ወቅት ኢራን የባህር መስመሩን በከፊል የዘጋች ሲሆን፣ ዋሽንግተንም በኢራን ወደቦች ላይ ማዕቀብ መጣሏ የነዳጅ አቅርቦቱ እጅግ እንዲቀንስ አድርጎታል። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 26
🔶ትራምፕ ግብዣ ላይ ተኩስ_ተከፈተ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለኋይት ሃውስ ቋሚ ዘጋቢዎች ባዘጋጁት የእራት ግብዣ ስነስርአት ላይ ተኩስ ተከፍቷል። ትላንት ምሽት በዋሽንግተን ሂልተን ለኋይት ሀውስ ቋሚ ዘጋቢ የሚዲያ ባለሙያዎች በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ፣ ምክትል ፕሬዝደንት ጄ.ዲ. ቫንስና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የታደሙ ሲሆን ተኩስ እንደተከፈተ በፍጥነት በደህንነት አባላት ሽፋን ተሰጥቶአቸው ከስፍራው ተወስደዋል። ተኩስ የከፈተው ግለሰብ ፕሬዝደንቱ በሚገኙበት 50 ያርድ ርቀት ገደማ ወደ መድረኩ እየሮጠ እንደነበር የተጠቆመ ሲሆን፣ በተኩሱ አንድ የደህንነት አባል በቅርብ ርቀት በጥይት ቢመታም ባደረገው የጥይት መከላከያ ጃኬት ከሞት መትረፍ መቻሉ ተገልፆአል። ፕሬዝደንቱ ተኩሱን የከፈተው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ይፋ አድርገው በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ጥቃት ተሰንዝሮበት ሕይወቱ የተረፈውን የደህንነት ባልደረባ አግኝተው ማናገራቸውንና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ነው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቆሙት። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 26
🔶ጆኒ ተጋጣሚዉን አሸነፈ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዉ በሆነዉ በድብልቅ ማርሻል አርት ውድድር ጆኒ ተጋጣሚዉን በማሸነፍ የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነ በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተዉ እና በርካታ ተመልካቾችን ያስገረመዉ ታሪካዊ የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በስዊት ቦክስ እና በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል። ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ይህ ስፖርታዊ ዉድድር በዐድዋ ድል መታሰቢያ መዘጋጀቱ አዲስ አበባን በስፖርት ቱሪዝም ረገድ ተመራጭ ከማድረጉም በላይ መዲናዋ የዲፕሎማሲ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ዉድድሮች የሚካሄዱባት የስፖርት ማዕከል መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው። በንቃተ ህሊና እና የጆኒ መካከል በተደረገዉ ብርቱ ፉክክር ጆኒ ተጋጣሚውን በመጀመሪያው ዙር በማሸነፍ የ1ሚሊዮን ብር ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተረክቧል። በመድረኩ ላይ ከዋናው የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ፍልሚያ በተጨማሪ፣ የቦክስ እና የሞይታይ (Muay Thai) ውድድሮች ተካሂደዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የስፖርት አፍቃሪዎች መታደማቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 23
🔶ዳንኤል ክብረት የብልጽግና ፓርቲ እጩ ሆነው ለምርጫ ቀረቡ በስደስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በግላቸው ተወዳድረው ፓርላማ የገቡት ዳንኤል ክብረት፣ ዘንድሮ በሚካሄደው ሰባተኛው ምርጫ ግን ብልጽግናን ተቀላቅለዋል፤ እጩ ሆነውም ቀርበዋል። በእርግጥ በ2013ቱ ምርጫም ብልጽግና በአዲስ አበባ ዕጩ ያላቀረበበት የምርጫ ክልል ዳንኤል የተወዳደሩበት ብቻ ነበር። ዳንኤል የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ መሆናቸውም ይታወቃል ሲል አዲስ ማለዳ ዘግቧል። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 22
🔶እስራኤል ግብረሰዶማዊነትን ተቀበለች! እስራኤል ግብረ ሰዶማዊነትን በይፋ በመቀበል በመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ ለመጀመሪያው ጊዜ የግብረሰዶማውያንን ቀን በሚቀጥለው ሰኔ ወር ልታካሂድ ነው፡፡ የእስራኤል ቱዴይ ዘገባ መሰረት፣ ‹‹የኩራት ምድር›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ኢ ምግባራዊ በዓል የሚከበረው በመጽሀፍ ቅዱስ በተጠቀሱት ሰዶም እና ገሞራህ ከተሞች ነው፡፡ ይህ ክበረ በአል በእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና አዘጋጅነት የተሰናዳ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 20
🔶አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ስለ ገጽታቸው መቀየር ማብራሪያ ሰጡ። የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሰሞኑን በነበረው የኮፕ 32 ዝግጅት ግምገማ ወቅት ገጽታቸው ተቀይሮ መታየታቸው ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ነበር። ምን ሆነው ነው ? የሚል ጥያቄም ሲነሳ ቆይቷል። አምባሳደር ሬድዋን ማብራሪያ ባለመስጠታቸው የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ግምታዊ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ነበር። ዛሬ አምባሳደር ሬድዋን " ደረሰብኝ ስላሉት " ጉዳይ መረጃ አጋርተዋል። ምን አሉ ? " ከሁለት ሳምንታት በፊት በሀገራዊ ጉዳይ የሚመክር ስብሰባ አስተናግደን ለምሳ እንዳረፍን ንፋስ ለመከላከል የተጋረደ የእንጫት አካፋይ ( Partition Wall ) ሚዛን ስቶ ሲወድቅ አናቴ ጋርና ትንሽ ገባ ብሎ አገኘኝ። ስንጥቁ መሰፋት ስለነበረበት ሀኪሞች በከፊል ላጩት። እኔ ደሞ ሙሉውን ቢሆን ይሻላል ብዬ እስከሚደርቅ አነሳሁት። እንደልጅነቴ ተመልጬ ሳየው አልጠላሁትም። ወዳጆችም እንዲያውም ሸጋ ነው አሉኝ። በተመልካች አስተያየት ተበረታትቼ ትንሽ ደሞ በአዲስ መልክ ልሞክረው ብዬ ዘለቅኩበት። የሆነው ይኽው ነው። የታከምኩትም አሚን ሆስፒታል ነው።እናማ እንኳን ለህክምና ለስራም ወደ ውጭ ሀገር አልወጣሁም። ምንም ያልተባለውም ምን አዲስ ነገር አለ በሚል ነው። ለማንኛውም ለተጨነቁት ምስጋናና አክብሮቴ ይድረስ " ብለዋል። Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1
ታትሟል ኤፕሪ 18
🔶በየቀኑ 1.4 ሚሊዮን ሰዎችን እያጓጓዝኩ ነው የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በቀን ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን እያጓጓዘ መሆኑን አስታወቀ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በዋና ከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርገው እንቅስቃሴ፣ በቀን በአማካይ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ተጓዦችን ከቦታ ቦታ እያጓጓዘ መሆኑን ገልጿል። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ የነዋሪውን የትራንስፖርት እንግልት ለመቀነስ በተከናወኑ የማሻሻያ ሥራዎችና በተሰማሩ ተጨማሪ አውቶቡሶች አማካኝነት የዕለታዊ ተጓዦች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ችሏል። ይህም ተቋሙ በከተማዋ የሕዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ድርሻ የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
🔶#ፊንቴክ በ"ፊንቴክ" ኢንቨስትመንት ስም በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ታዋቂ አርቲስቶች እና የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ይሁን እንጂ ፖሊስ ከወንጀሉ ውስብስብነት አንፃር ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቋል። ጠበቆቹ የፖሊስን ጥያቄ ተቃውመው መከራከሪያቸውን አቅርበዋል። የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍ/ቤቱ፣ፖሊስ የጠየቀው የተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ላይ ለመወሰን ለሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
Hashtags
ታትሟል ኤፕሪ 18
🔶"ሥራ የሚገኘው በዘመድና በዘር መሆኑን አውቃችሁ ተንቀሳቀሱ" — ዶክተር አረጋ ይርዳው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው፣ ተማሪዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመርቀው ወደ ሥራው ዓለም ሲሰማሩ ያለው ነባራዊ ሁኔታ "በዘመድ፣ በፓርቲ አሠራር እና በዘር" ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተረድተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ማቅረባቸውን ኖር ሬድዮ በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ከተገኙ እንግዶች ሰምቷል። ዶክተር አረጋ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የ44ኛው ዙር ተማሪዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ፕሬዚዳንቱ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት የሥራ ዓለም መመሪያ ላይ በሀገሪቱ ያለውን የሥራ ቅጥር ሁኔታ በግልጽ እንደሚከተለው ገልጸውታል፦"ተመርቃችሁ ስትወጡ ሥራ የሚገኘው በዘመድ፣ በፓርቲ አሠራር፣ በዘር እና በጐጥ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ መልኩ እንድትንቀሳቀሱ እንደሚያስፈልግ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህንን ንግግር ያደረጉት ተመራቂዎች ከዩኒቨርሲቲ መውጣታቸውን ተከትሎ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ተጨባጭ ፈተና ለማሳወቅና አስቀድመው እንዲዘጋጁበት ለማሳሰቢያ እንደሆነ ተመልክቷል። በብቃትና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አሠራር እንዲኖር በሚወተወትበት በዚህ ወቅት፣ እንዲህ ዓይነት ነባራዊ እውነታን የጠቆመ ንግግር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም መሪ መሰማቱ ልዩ ትኩረትን ስቧል። ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1 ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1