TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Nor Radio
Nor Radio avatar

TGINSIGHT POST

Post #271

@NorRadio1

Nor Radio

ዕይታዎች653የዕይታ ቁጥር
ታትሟልኤፕሪ 2626/04/2026 05:18 ጥዋት
ይዘት

የልጥፍ ይዘት

🔶ጆኒ ተጋጣሚዉን አሸነፈ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዉ በሆነዉ በድብልቅ ማርሻል አርት ውድድር ጆኒ ተጋጣሚዉን በማሸነፍ የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነ በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተዉ እና በርካታ ተመልካቾችን ያስገረመዉ ታሪካዊ የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር በስዊት ቦክስ እና በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል። ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ይህ ስፖርታዊ ዉድድር በዐድዋ ድል መታሰቢያ መዘጋጀቱ አዲስ አበባን በስፖርት ቱሪዝም ረገድ ተመራጭ ከማድረጉም በላይ መዲናዋ የዲፕሎማሲ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ዉድድሮች የሚካሄዱባት የስፖርት ማዕከል መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው። በንቃተ ህሊና እና የጆኒ መካከል በተደረገዉ ብርቱ ፉክክር ጆኒ ተጋጣሚውን በመጀመሪያው ዙር በማሸነፍ የ1ሚሊዮን ብር ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተረክቧል። በመድረኩ ላይ ከዋናው የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ፍልሚያ በተጨማሪ፣ የቦክስ እና የሞይታይ (Muay Thai) ውድድሮች ተካሂደዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የስፖርት አፍቃሪዎች መታደማቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል። ==================== አሁኑኑ የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/NorRadio1 https://t.me/NorRadio1