TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← adsevanz

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Знайсці падобны кантэнт

Канал-крыніца @adsevanz · Post #2349 · 9 кра

Low pass в исполнении лучшего бомбера❤ #эксклюзив

Вынікі

Знойдзена 2 падобных паведамленняў

Пошук: #islamicaffairs

当前筛选 #islamicaffairs清除筛选

የረመዳን ጾም፣ ጨረቃ ነገ ምሽት ከታየች ረቡዕ፣ ካልሆነ ግን ሐሙስ ይጀምራል ************** የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1447ኛው ታላቁ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት የመልካም ምኞት መግለጫ ሰጥቷል። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት መረጃን ጠቅሰው እንዳሉት፤ የረመዳን ጾም መጀመሪያ ዕለት በጨረቃ መታየት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። በዚሁ መሠረት ጨረቃ ነገ ማክሰኞ ምሽት ከታየች፣ የረመዳን ጾም ረቡዕ የካቲት 11 ይጀምራል። ጨረቃ ማክሰኞ ምሽት ካልታየች ግን፣ ጾሙ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን እንደሚጀምር ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ ረመዳን የአንድነት፣ የሰላም እና የኢባዳ (የአምልኮ) ወር መሆኑን ገልጸው፤ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ እንደ ሃይማኖቱ አስተምህሮ የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ እንዲያሳልፈው አደራ ብለዋል። በመጨረሻም ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን እና ወደምትመኘው ሁለንተናዊ ብልጽግና እንድትሸጋገር ምዕመኑ በረመዳን ዱዓ እንዲያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በዘሃራ መሃመድ #Ramadan2026#Ethiopia#IslamicAffairs#RamadanKareem#EthiopianBroadcastingCorporation