TGTGInsightтелеграм анализLIVE / telegram public index
← Такты, стеки, два колеса

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Намери подобно съдържание

Изходен канал @clockstackwheels · Post #971 · 10.04

Если кто-то думает, что настольные игры это скучное перекладывание жетонов с цифрами для душнарей, то посмотрите на "Неон". "Неон" — проект от российских разработчиков в жанре Battle Royale и сеттинге киберпанка. Если киберпанк от настолок ожидать можно легко (видеоигра Cyberpunk 2077 основана именно на настолке 1974 года), то батлрояль это что-то сравнительно новое. По меньшей мере, кажется, что настольному ритму это противоречит: если игрок на личной встрече друзей вылетает из игры навсегда и скучает, то это антипаттерн, и в нормальных играх с проработанной механикой такие вещи стараются не делать (одна из причин, по которым "Мафия" бесконечно хуже, чем "Авалон"). Авторы "Неона", впрочем, решили эту проблему, добавив отдельный дополнительный режим с возрождением: после смерти ты появляешься заново, а игра в таком случае идёт на очки. Причём, довольно хитро сделано, например, так, чтобы убивать только что возродившихся было менее выгодно, чем тех, кто засиделся на арене. Но можно играть и по хардкору настоящий режим на вылет. В остальном очень драйвовая настолка с неплохим балансом, пафосным лутом и простыми правилами, которые постигаются за 10 минут. Присутствует эффект постепенно уменьшающегося мира, как и положено в батлроялях, так что к концу игроки неизбежно стоят рядом и провоцируются на драку. Единственное что, мне кажется, не слишком большая реиграбельность: после пары десятков партий уже будут изучены все предметы и возможные цепочки действий. Надеюсь, авторы выпустят в скором времени дополнение. #games

Hashtags

Резултати

Намерени 227 подобни публикации

Търсене: #ebc

当前筛选 #ebc清除筛选

ኢትዮጵያ እየተገነባች ነው፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ************** ዛሬ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሳምንት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ከፍተናል። መሠረተ ልማት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ግብአቶችን በማመላለስ የኢኮኖሚያችን የደም ሥር፣ የብልጽግናችን መሠረት ነው። በዐውደ ርዕዩ የተመለከትነውም ወሳኝ የልማት ተቋሞቻችን፣ መሠረተ ልማትን እንደ ሀገር በቅንጅትና በትብብር የመምራት አዲስ የሥራ ባህል እየገነቡ መሆናቸውን ነው። ባለፉት ዓመታት ፈጠራን፣ ፍጥነትን እና ጥራትን የጉዟችን መርሕ አድርገን በመሥራት ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበናል። የመንገድ ርዝመታችንን በብዙ ኪሎ ሜትሮች አሳድገናል፤ ታዳሽ ኃይል የማመንጨት ዐቅማችንን ወደ 10 ሺህ ሜጋ ዋት አካባቢ አድርሰናል። በዲጂታል ዘርፍም የሞባይል ተጠቃሚዎችን 97 ሚልዮን እና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 57 ሚልዮን አድርሰናል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራዎቻችን "ከተባበርን የማይቻል የለም" የሚለውን መርሐችንን በተግባር ያሳዩ፣ ፍጥነትና ጥራትን ያስተሣሠሩ ፕሮጀክቶች ናቸው። ጉዟችንን ለማጣጣል ለሚሞክሩም ሆነ የውጤቱ ባለቤት እኛ ነን" ለሚሉ ሁሉ መልሳችን አንድ ነው፤ እውነታውንና ፍርዱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትተን፣ ሥራችንን እንቀጥላለን! https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0gifZyviBDxs3gC1n26Q6xQYoSWVu3nJLiYuDiYLQ7XewrHh3bCVQ4nDAGHP8j7iwl Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#EBC

Ethio-Djibouti Railway S.C.

@ethiodjiboutirailway · Post #3516 · 21.04.2026 г., 17:44

#EBC ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ልጆች የገነባውን የ #AMG_EDR የባቡር መስመር ፕሮጀክትን በተመለከተ ቀጣዩን ዘገባ አቅርቧል።

Hashtags

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ************ የአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዝደንት የሆኑትን ዶክተር ጆርጅ ኢሎምቢን ዛሬ ተቀብያለሁ። በነበረን የጋራ ቆይታ፣ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታችንን በምናጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል። #EBC#ebcdotstream#Ethiopia

"በከተሞቻችን እንደ ውኃ፣ መብራት፣ የፍሳሽ መሠረተ ልማት፣ ጤና እና ትምህርት መሠረታዊ ፍላጎቶችን በጥራት ማቅረብ የመደመር መንግሥት አንዱ ግብ ነው። የከተሞች ጸጥታና ደኅንነት ከዕድገታቸው እና ከግባቸው ጋር መመጣጠን አለበት። በተጨማሪም የከተሞች ክፍሎች የንግድ አካባቢ፣ የመኖሪያ አካባቢ እና የመኖሪያ አካባቢ ተብለው ተለይተው መገንባት አለባቸው። ይህም መሠረተ ልማትን፣ አገልግሎትን እና የሕዝብ ፍላጎትን ያሣልጣል።" የመደመር አንቀፅ ገፅ 237 #EBC#Ethiopia#EBCDOTSTREAM

ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ ዋጋን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ ************************ ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የብድር ሰነድ (Letters of Credit) ይሁን ሌላ ክፍያ መንገድ ሲፈቅዱ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ተመንን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሐምሌ 2016 ዓ.ም ተግባራዊ ያደረገውን የውጭ ምንዛሪ መመሪያን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ይታወቃል። መመሪያው ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር በመደራደር የውጭ ምንዛሪ መሸጫ እና መግዣ ተመኖችን መወሰን እንዲችሉ ይፈቅዳል። በተጨማሪም ባንኮች ቀደም ሲል ይጠቀሙበት የነበረው ዝቅተኛ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ መመሪያ (Minimum Price Directive) በመሰረዙ፤ አሁን ግን በአዲሱ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሠረት የገቢ የዕቃዎችን ዋጋ ትክክለኝነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ይሁን እንጂ፣ ባንኮች ለብድር ሰነድ (Letters of Credit) የሚጠቀሙባቸው ዋጋዎች ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የማጣቀሻ ዋጋዎች ጋር ሲነፃፀሩ ከፍተኛ ልዩነት እንዳላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባደረገው ክትትል አረጋግጧል። በመሆኑም የዋጋ ልዩነቶቹን ለማስተካከልና የዋጋ ማጣቀሻዎችን ለማጣጣም ሁሉም ባንኮች ከጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም (January 27, 2026) ጀምሮ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ተመንን እንደ አመላካች ዋጋ ይጠቀማሉ። ይህም በባንክ ሥርዓቱ እና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መካከል ያለውን የዋጋ ልዩነት ለማስወገድ እና የውጭ ምንዛሪ መረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። #EBC#ebcdotstream#Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ምን ምን አሳኩ? ************************* ✅ የAI ኢንስቲትዩት መመሥረት፦ ለምርምር እና ለፈጠራ ሥራዎች የሚውል ራሱን የቻለ ዘመናዊ ተቋም ተገንብቷል። ✅ የሀገር በቀል ቋንቋዎች ልማት፦ የተለያዩ ቋንቋዎች በዲጂታል ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የትርጉም እና የንግግር AI ቴክኖሎጂዎች በስፋት እየለሙ ነው። ✅ የጤና ዘርፍ አብዮት (ቀድሞ ምርመራ)፦ የጡት ካንሰርን እና የሳንባ በሽታዎችን በAI ምርመራ ቀድሞ ለመለየት የሚያስችሉ መተግበሪያዎች ወደ ሥራ ገብተዋል። ✅ የሰብል ጥበቃ፦ የሰብል በሽታዎችን እና ተባዮችን በAI ቴክኖሎጂ ቀድሞ በመለየት ለምግብ ዋስትና ትልቅ እገዛ እያደረገ ይገኛል። ✅ ዲጂታል ኢትዮጵያ፦ ሀገራችን በዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትመራ የሚያስችል ግልጽ ፖሊሲ እና ፍኖተ ካርታ ተቀርጾ ተግባራዊ እየሆነ ነው። ✅ የሥራ ዕድል፦ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በኮዲንግ እና በዳታ ሳይንስ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ማዕከል የማድረግ ሥራ ተጀምሯል። #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ (Assembly of the AU) ተሹመዋል #Ethiopia#PMAbiyAhmed#EBC

“የጀመርነውን ልማት እንቀጥላለን፤ ግራ ቀኝ ሳንል በትኩረት እና በትብብር መንፈስ የልማት ጉዟችንን እናስቀጥላለን።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #EBC#Ethiopia#PMAbiyAhmed

የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል። የመጀመሪያውን ክፍል ማክሰኞ ሚያዚያ 6/ 2018 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ። Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#EBC #PMOEthiopia

123•••10•••1819
ПредишнаСтр. 1 от 19Следваща