TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← GZ学习频道

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @olddriverGDstudy · Post #12 · Mar 17

#语录 【关于cj中的曲线救国】 一定要好好对待每一段男女关系 要相信 一切都是最好的安排 我们要感恩生活中每一次不期而遇的温暖 做不成男女朋友 那就是要做炮友 渣男怎么了 渣男也有爱 虽然我们爱的比较短暂 直接 毕竟我是职业打针选手 有时候 要善于把痛点转化成卖点 dym来了又怎样 虽然不至于浴血奋战 但是可以曲线救国

Hashtags

Results

3 similar posts found

Search: #eotc

当前筛选 #eotc清除筛选
Borkena

@borkena · Post #5891 · 02/28/2026, 05:14 PM

አባ ሳዊሮስ በአርሲ በደረሰው የምዕመናን ግድያ ሀዘናቸውን ገለፁ። የሀዘን መግለጫ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን እንገልጻለን። በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ በታጣቂዎች ጥቃት የካቲት 19 ለ 20 አጥቢያ አንድ ካህን፣ ሁለት ሴቶች እና 18 ወንድ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለጽሕፈት ቤታችን ከጻፉት ደብዳቤ ስንመለከት እጅግ በከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል። በመሆኑም በሀገረ ስብከቱ በተለያዩ ጊዜያት በኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመውና የተፈጸመው ዘግናኝና እጅግ አሳዛኝ ግድያዎች የኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችንን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በነጻነት የመኖርና ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን የመፈጸም መብትን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥታት ጉዳዮን በልዩ ሁኔታ መከታተልና የማያዳግም መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ መፈለግ እንዳለባቸው እያሳሰብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም የአካባቢው ችግር በመሰረቱ እስከሚፈታ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን። በመጨረሻም በዚህ ዘግናኝና አሳዛኝ ግድያ ሕይወታቸውን ላጡ ልጆቻችን እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርስልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥልን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዘወትር ጸሎቷ መሆኑን እንገልጻለን። አባ ሳዊሮስ #Ethiopia#Oromiyaa#ArsiZone#ethiopianorthodoxtewahedochurch#EOTC

Borkena

@borkena · Post #5897 · 03/01/2026, 04:36 PM

ሲኖዶሱ በአርሲ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ። ​ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ የተፈጸመው የንጹሐን ግድያ ለዘመናት የዘለቀውን የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር እሴት ለመናድ የታለመ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ድርጊቱን በጽኑ አውግዟል። በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት በአዲስ መልክ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖች ሕይወት በግፍ ማለፉን ቋሚ ሲኖዶስ በመሪር ኃዘን ገልጿል። ኦርቶዶክሳውያን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው ሊከበር ይገባል ያለው ቋሚ ሲኖዶሱ፤ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት እርምጃዎች በአፋጣኝ እንዲወስዱ አሳስቧል። በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፣እንዲሁም ለተፈጸመው ግፍ አፋጣኝ ፍትሕ እንዲሰጥና ገዳዮች በሕግ እንዲጠየቁ እና የዜጎችን ደኅንነትና ንብረት የማስጠበቅ የመንግሥት ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፤የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጣ ቋሚ ሲኖዶስ አሳስቧል ። ​በመጨረሻም ቋሚ ሲኖዶስ ስለስሙ መከራን ለተቀበሉ" ንጹሐን ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኝቷል። #Ethiopia#AddisAbaba#Oromia#EOTC#Arsi#Ethiopiannews#ዜና#አርሲ