@ebcnewsnow · Post #53588 · 04/16/2026, 03:50 AM
"ምንም ጥርጥር የለውም፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዐሥር ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ አውራ ሀገር ትሆናለች" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#ebcdotstream
Hashtags
TGINSIGHT SIMILAR POSTS
Source channel @olddriverGDstudy · Post #58 · Mar 27
#风哥避孕套如何选择课堂笔记 都说了多少遍了,别TMD买冈本,冈本TMD容易破 油少,一样的价钱不会买旁边的相模啊,玻尿酸套子也有缺点虽然润但是时间久了干的快,沐浴乳我不挑但是有一个沐浴乳我拒绝 ,力士的薰衣草真的不好闻,冈本最大的问题就是他油放的少拿出来就干,要润就玻尿酸 然后赤尾有小储精囊跟无储精囊套 要感觉我都是用浮点的,浮点套女的感觉来得快,有些人就马眼有感觉的这么办 不过无储精囊适合做多了跟射精量不大的用要不然会破的,超市就买杜蕾斯 杰士邦 相模,淘宝你看中啥买啥,然后小科普 0.01都是聚氨酯套 其他的都是乳交套,名流的玻尿酸套还是不错的,套子我是不追求的薄的,套子主要是为了安全还有就是润,很多套子很润但是油少玻尿酸少了也不行,像玻尿酸套子虽然很润但是也干的快,捷古斯也算日本大牌了,蝴蝶套一个形容 牌子叫捷古斯 因为包装上印着蝴蝶,买啥套子真的是最啥太大追求就用JS的套子 干了就跟JS说换个套子 #知识#避孕套
Hashtags
Search: #ebcdotstream
@ebcnewsnow · Post #53588 · 04/16/2026, 03:50 AM
"ምንም ጥርጥር የለውም፤ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዐሥር ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ አውራ ሀገር ትሆናለች" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia#ebcdotstream
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #53310 · 04/11/2026, 07:37 AM
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ************ የአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዝደንት የሆኑትን ዶክተር ጆርጅ ኢሎምቢን ዛሬ ተቀብያለሁ። በነበረን የጋራ ቆይታ፣ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታችንን በምናጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል። #EBC#ebcdotstream#Ethiopia
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #52443 · 03/18/2026, 02:59 AM
"በከተሞቻችን እንደ ውኃ፣ መብራት፣ የፍሳሽ መሠረተ ልማት፣ ጤና እና ትምህርት መሠረታዊ ፍላጎቶችን በጥራት ማቅረብ የመደመር መንግሥት አንዱ ግብ ነው። የከተሞች ጸጥታና ደኅንነት ከዕድገታቸው እና ከግባቸው ጋር መመጣጠን አለበት። በተጨማሪም የከተሞች ክፍሎች የንግድ አካባቢ፣ የመኖሪያ አካባቢ እና የመኖሪያ አካባቢ ተብለው ተለይተው መገንባት አለባቸው። ይህም መሠረተ ልማትን፣ አገልግሎትን እና የሕዝብ ፍላጎትን ያሣልጣል።" የመደመር አንቀፅ ገፅ 237 #EBC#Ethiopia#EBCDOTSTREAM
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #51260 · 01/25/2026, 07:38 AM
ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ ዋጋን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ ************************ ባንኮች ለተመረጡ የገቢ ዕቃዎች የብድር ሰነድ (Letters of Credit) ይሁን ሌላ ክፍያ መንገድ ሲፈቅዱ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ተመንን እንደ አመላካች ዋጋ እንዲጠቀሙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሐምሌ 2016 ዓ.ም ተግባራዊ ያደረገውን የውጭ ምንዛሪ መመሪያን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ይታወቃል። መመሪያው ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር በመደራደር የውጭ ምንዛሪ መሸጫ እና መግዣ ተመኖችን መወሰን እንዲችሉ ይፈቅዳል። በተጨማሪም ባንኮች ቀደም ሲል ይጠቀሙበት የነበረው ዝቅተኛ የገቢ ዕቃዎች ዋጋ መመሪያ (Minimum Price Directive) በመሰረዙ፤ አሁን ግን በአዲሱ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሠረት የገቢ የዕቃዎችን ዋጋ ትክክለኝነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው። ይሁን እንጂ፣ ባንኮች ለብድር ሰነድ (Letters of Credit) የሚጠቀሙባቸው ዋጋዎች ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የማጣቀሻ ዋጋዎች ጋር ሲነፃፀሩ ከፍተኛ ልዩነት እንዳላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባደረገው ክትትል አረጋግጧል። በመሆኑም የዋጋ ልዩነቶቹን ለማስተካከልና የዋጋ ማጣቀሻዎችን ለማጣጣም ሁሉም ባንኮች ከጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም (January 27, 2026) ጀምሮ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ተመንን እንደ አመላካች ዋጋ ይጠቀማሉ። ይህም በባንክ ሥርዓቱ እና በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን መካከል ያለውን የዋጋ ልዩነት ለማስወገድ እና የውጭ ምንዛሪ መረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። #EBC#ebcdotstream#Ethiopia
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #51788 · 02/19/2026, 08:39 AM
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለተኛው ክርክር በኢቢሲ በቅርብ ቀን ይጠብቁን! ብልጽግና ፓርቲ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እናት ፓርቲ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት ፓርቲ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የተደረገ ሁለተኛው የምርጫ ክርክር በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን። በምርጫ ብቻ!! #ethiopianbroadcastingcorporation#EBCDOTSTREAM
@ebcnewsnow · Post #51614 · 02/12/2026, 05:11 PM
የምርጫ 2018 የፖለቲካ ፓርቲዎች የመጀመርያ ክርክር በኢቢሲ በቅርብ ቀን ይጠብቁን! ብልጽግና ኢዜማ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ነፃነትና እኩልነት በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የተደረገ የመጀመሪያ የምርጫ ክርክር በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን። በምርጫ ብቻ!! #ethiopianbroadcastingcorporation #EBCDOTSTREAM
@ebcnewsnow · Post #51565 · 02/09/2026, 04:59 PM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀመሩ ************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት አስጀምረናል ብለዋል። ይህ አገልግሎት ዜጎች የፖሊስ አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያገኙ እንደሚያስችል ገልፀዋል። በተጨማሪም አገልግሎቱ ለፖሊስ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው እና የወንጀል መከላከል ስራውን የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የዚህ አገልግሎት መጀመር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የህግ አስከባሪ አካላት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተጀመረው የሪፎርም ስራን ውጤታማነት የሚያሳድግ ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia
@ebcnewsnow · Post #51212 · 01/23/2026, 01:44 PM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአየር ኃይል 90ኛ ዓመት የአቪዬሽን ኤክስፖን ጎበኙ ***************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 ይፋዊ የመክፈቻ መርሃግብር ላይ ተገኝተዋል። ኤክስፖው “የወደፊቱን የአቬሽን አቅም በጋራ እንገባ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን ኢትዮጵያ ለአቪዬሽን እና ኤሮስፔስ ልማት፣ አለም አቀፍ ትብብርን በማጠናከር እና ሀገራችንን በአቪዬሽን ልማት የቀጣናው እና አኅጉሩ የፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የዘላቂ እድገት ማዕከል ማድረግ ላይ ያላትን ጽኑ አቋም እና ተግባር ያሳያል። #PMOEthiopia#EBC#ebcdotstream
Hashtags
@ebcnewsnow · Post #51543 · 02/08/2026, 12:49 PM
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የኮሪደር ልማት ሥራ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ ሰራተኞች ማዕድ አጋሩ ***************** ዛሬ በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያፋጠኑ ከሚገኙ ታታሪ ሰራተኞች ጋር ማዕድ በማጋራት አበረታተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ እነዚህ ብርቱ ሰራተኞች በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች፤ በተለይም በካዛንቺስ የሕፃናት ዓለም፣ በስፖርት ፓርክ እና በአዲስ አኳሪየም ግንባታዎች፣ እንዲሁም ከኡራኤል እስከ ቦሌ ቪ.አይ.ፒ፣ ከኢንግሊዝ ኢምባሲ 22 እስከ ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል እና ከውኃ ልማት እስከ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ እየተከናወኑ ባሉ መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት አያያዥ መስመሮች ላይ ሌት ተቀን የሚተጉ ናቸው ብለዋል። በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን፤ አዲስ አበባ ሁልጊዜም ታመሰግናችኋለች ሲሉም ገልፀዋል። በከተማችሁ መልማት በመደሰት ሁሌ በማዕድ ማጋራት እና እነዚህን ብርቱ ሰራተኞ በማበረታት መርኃ ግብር እየተሳተፋችሁ ላላችሁ ባለሀብቶች በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#AddisAbaba
@ebcnewsnow · Post #52009 · 03/03/2026, 01:35 PM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በትግርኛ ያደረጉት ቆይታ! ዛሬ ምሽት 2:30 ይጠብቁን! #EBC#ebcdotstream#Ethiopia#AbiyAhmed
@ebcnewsnow · Post #51848 · 02/21/2026, 06:12 PM
የኮሪደር ልማት ስራዎች በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ****************** የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ በሐዋሳ ከተማ በሁለተኛው ምዕራፍ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በዛሬው ዕለት ተመልክተናል ብለዋል። የኮሪደር ልማት ስራዎች የተሻለ ሀገርን ለትውልድ የመገንባት አካል ሆነው በርካታ ከተሞችን እየለወጡ ይገኛሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አጠቃላይ ስራዎቹ እያደገ ለመጣው ከተሜነት ሀገርን ያዘጋጁ መሆናቸውንም ገልፀዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#PMAbiy
@ebcnewsnow · Post #51684 · 02/14/2026, 11:44 AM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦካይ ጋር መከሩ ***************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦካይ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ከላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦካይ ጋር ተገናኝተን በቴክኖሎጂ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተለይም ኢትዮጵያ ለመመስረት ባቀደችው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ በተመለከተ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ebcdotstream#Ethiopia#PMAbiy