TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← 云游Cloud|40%AFF诚招推广|永久免费

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @yunucloud_Channels · Post #21 · Aug 10

#通知 即日起,每次刷屏扣除30积分。

Hashtags

Results

1 similar post found

Search: #birhanujulla

当前筛选 #birhanujulla清除筛选
Borkena

@borkena · Post #5852 · 02/25/2026, 07:34 AM

በሰሜን ወሎ ዞን ሲሪንቃ ከተማ በተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት የአባትና ልጅ ህይወት አለፈ። የመንግስት ጦር በአካባቢው በፈፀመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት አንድ የ65 አመት አባት እና የ23 አመት ልጃቸው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቦርከና ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ለቦርከና በሰጡት አስተያየት የከባድ መሳሪያ ጥቃቱ በመኖሪያ ቤት ላይ መድረሱን ገልፀዋል። ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈው በቤት ውስጥ ስለነበሩ እንደሆነ ገልፀው፣ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ከቤት ውጭ በመሆናቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውን አስረድተዋል። ከአባትና ልጁ በተጨማሪ በቤት ውስጥ የነበሩ እንስሳቶቻቸው ተገድለዋል ተብሏል። በአካባቢው የነበረው ተኩስ ከባድ እንደነበር የገለፁት ነዋሪዎቹ፣ ከአዲስአበባ እና ከደሴ የመጡ ተጓዦች መንገዱ በግጭቱ ምክንያት በመዘጋቱ ህይወታቸውን ለማትረፍ ከተሽከርካሪ ወርደው በመኖሪያ መንደሮች ለመግባት መገደዳቸውን አብራርተዋል። የአይን እማኞቹ የከባድ መሳሪያ ጥቃቱ የደረሰው ሰሞኑን የፋኖ ሀይሎች በወልዲያ ዙሪያ ሰፍሮ በሚገኘው የመከላከያ ሀይል ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህ ጦርነት ከታጣቂዎቹ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የመንግስት ጦር በወሰደው የአፀፋ እርምጃ ነው ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸው ያለፈው ተብሏል። #Ethiopia#EthiopianNationalDefenceForce#AFNM#fano#AbiyAhmed#BirhanuJulla#news#መከላከያ#ፋኖ#ዜና