TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← 云游Cloud|40%AFF诚招推广|永久免费

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @yunucloud_Channels · Post #21 · Aug 10

#通知 即日起,每次刷屏扣除30积分。

Hashtags

Results

1 similar post found

Search: #landslideresponse

当前筛选 #landslideresponse清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52298 · 03/12/2026, 07:50 AM

በጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍና አስቸኳይ ምላሽ ለመስጠት እየተሠራ ነው፦ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ******************** በጋሞ ዞን ደጋማ አካባቢዎች የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በደረሰው የናዳ አደጋ እስከ ትላንት አመሻሽ ድረስ የ52 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተመላክቷል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለጹት፤ በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች ለሰብዓዊ ሥራዎች ቅድሚያ በመስጠት አስክሬን የማፈላለግና ድጋፍ የማድረስ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል። የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ውይይት፣ አደጋው የደረሰባቸውን ዜጎች በፍጥነት ወደ ቀድሞ ማኅበራዊ ሕይወታቸው ለመመለስ የሚያስችሉ ዐቢይና ንዑስ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ሥራ እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል። የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) በአደጋው የ52 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት ሰብዓዊ ድጋፎችን ወደ ሥፍራው ለማድረስ የመንገድ ከፈታና የጥርጊያ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል። በተመስገን ተስፋዬ #ጋሞ#ኢትዮጵያ#የተፈጥሮአደጋ#ሰብዓዊድጋፍ#Gamo#Ethiopia#LandslideResponse