TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← 云游Cloud|40%AFF诚招推广|永久免费

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @yunucloud_Channels · Post #21 · Aug 10

#通知 即日起,每次刷屏扣除30积分。

Hashtags

Results

1 similar post found

Search: #mof

当前筛选 #mof清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53803 · 04/20/2026, 10:09 AM

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ *************** በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣ ከ2026 የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የፀደይ ስብሰባ ጎን ለጎን ከአሜሪካ የግምጃ ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አድርጓል። ውይይቱ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትሥሥርን በማሳደግ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በተለይም እንደ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ልማት ባሉ ስልታዊ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን የሪፎርም ጉዞን አድንቀዋል። የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሽግግር በቴክኒክ ድጋፍ፣ በግል ዘርፍ ተሳትፎ እና ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነትም በድጋሚ አረጋግጠዋል። ሁለቱም ወገኖች የጋራ የኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ወደፊት ለማራመድ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እና የሁለቱን ሀገራት የንግድ ትሥሥር ይበልጥ ለማስፋፋት ተስማምተዋል። #EBC#Ethiopia#USA#MoF#ustreasury#diplomacy