TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Dev Determination

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find lignende indhold

Kildekanal @devdetermination · Post #21 · 19. jun.

Занимательный факт Как оказывается одно из наших устройств было расположено посреди популярного маршрута у бегунов. Люди пробегая мимо останавливались возле устройства, чтобы повысить свою решимость и избавиться от чувства усталости #redev#determination#device#hitechnology

Resultater

1 lignende opslag fundet

Søg: #temesgentiruneh

当前筛选 #temesgentiruneh清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52343 · 12.03.2026, 18.15

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ ተሳተፉ ***************** ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ከመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች፣ ከኢንቨስትመንት አጋሮችና ከእምነቱ ተከታዮች ጋር በአንድነት አሳልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በእስልምና አስተምህሮ አብሮ መብላትና መረዳዳት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው እሴት መሆኑን ገልጸው፤ “ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄንና የጋራ ደስታን በተግባር መተርጎም እንደሚገባ የሚያሳይ ሕያው የሕይወት ስንቅ መሆኑን አብራርተዋል። የዕለቱ የኢፍጣር መርሐ ግብር የኢትዮጵያን የብዝኃነት ውበት፣ አብሮነትና አንድነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚመዘገበው ስኬት ትርጉም የሚኖረው በታላቅ የፍቅርና የመተሳሰብ ሰንሰለት ተሳስረን ለትውልድ የምትተርፍ ጠንካራ ሀገርን በጋራ መገንባት ስንችል መሆኑን አስገንዝበዋል። ብልጽግና የሚረጋገጠው እንዲህ ባሉ የዳበሩ ማኅበራዊ እሴቶች ጭምር መሆኑን በመጠቆም ለሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የረመዳንና የኢባዳ ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል። #EBC#Ethiopia#TemesgenTiruneh#Iftar#Ramadan2026#UnityInDiversity