Post content
እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት አደረሰች። ኢራንም የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ጀምራለች። እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመተባበር በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ሰፊ እና ተከታታይ የአየር ጥቃት መጀመሯን አስታውቃለች። በቴህራን ከተማ ከፍተኛ የፍንዳታ ድምፆች እየተሰሙ ሲሆን ጥቃቱ የኢራንን የደህንነት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ለማፈራረስ ያለመ መሆኑን አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለአልጄዚራ ገልጸዋል። እስራኤል ለሚቀጥሉት 4 ቀናት የሚቆይ ከፍተኛ የጋራ ጥቃት ለማካሄድ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን የገለጸች ሲሆን፣ ከጥቃቱ በኋላ ቴህራን የቀድሞ መልኳን አትይዝም ስትል አስጠንቅቃለች። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በግል ትሩዝ ሶሻል ገፃቸው ላይ በለቀቁት የስምንት ደቂቃ ተንቀሳቃሽ ምስል አሜሪካ ኢራን ላይ በተፈፀመው ጥቃት መሳተፏን አረጋግጠዋል። ፕሬዝዳንቱ ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር ውጤት እንደሌለው ተናግረዋል። "ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲኖራት ፈጽሞ አንፈቅድም" ያሉት ትራምፕ፣ ድርድሩ ካልተሳካ የሀይል አማራጭን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ ዝተዋል። በተያያዘ መረጃ ኢራን የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ጀምራለች። ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች በእስራኤል ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተገልጿል። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ኢራን የሚሳዔል ጥቃት መፈፀሟን አረጋግጧል። ከአፀፋ እርምጃው በፊት አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣን፣ "ኢራን ምላሽ የማትሰጥበት ጥቃት የለም" ሲሉ ተናግረዋል። ባለስልጣኑ አክለው፣ "እርምጃችን አስከፊና አውዳሚ ነው" ሲሉ ዝተዋል። የኢራን የመከላከያ አመራሮች በከባድ መሳሪያ አጠቃቀም ላይ ምክክር እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። #Ethiopia#Iran#Israel#UnitedStates#middleeast#war