TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Back to channels
GOFERE_GRAPHICS avatar

TGINSIGHT CHAT

GOFERE_GRAPHICS

@ethio_logodesign

Design

Call for digital content design's 0953682941

Subscribers198Current channel subscribers
Tracked posts47Indexed post count
Recent reach480Sum of recent post views
Recent posts

Recent posts

Tag: #fastmereja · 1 posts

当前筛选 #fastmereja清除筛选

Posted Mar 11

ዓባይ ባንክ 7 ሚሊዮን ብር ያወጣበትን አዲሱን የንግድ ምልክት ይፋ አደረገ። #FastMereja ባንኩ ነባሩን የንግድ ምልክት እና መገለጫ የቀየረው በተለየ መልኩ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት እና ለእድገት እና ለፈጠራ ያለውን ትጋት ለማስረዳት በማሰብ ነው ተብሏል። የባንኩን አዲስ መለያ የተዘጋጀው በአቶ ያየህይራድ ታደሰ እና በስቱዲዮኔት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ለስራውም 7 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ተብሏል። አዲሱ የንግድ ምልክት የዓባይ ወንዝ ዋና መገለጫ ከሆነው የጢስ ዓባይ ፏፏቴ የተነሳ እና በሰባት አራት ማዕዘናዊ ቋሚ መስመሮች የተወከለ መሆኑን ተጠቅሷል። ይህም የባንኩን እድገት፣ ችግሮችን የመቋቋም አቅም፣ አስተማማኘነት እና ታማኘነት ያመለክታል ሲባል ሰምተናል፡፡ የባንኩ የመለያ መገለጫ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ታማኝ አገልጋይ ወደ "Source of Greatness" መቀየሩንም ሰምተናል። የእንግሊዝኛው አቻ የአማርኛ ፍቺም እየታሰሰበት ነው ተብሏል። አዲሱ የንግድ ምልክት መገለጫው የደንበኞቹ ትልቅ የመሆን ተስፋ፣ ምኞት እና እቅድ ምንጭ በመሆን፤ ወደ ከፍታ ለመድረስ በሚደረግ ጉዞ የማያለሰልስ የባንኩን የፋይናንስ ድጋፍ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ዓባይ ባንክ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ሀብቱ 60 ቢሊዮን ብር፣ የተቀማጭ 48.6 ቢሊዮን ብር፣ የተከፈለ ካፒታል 5.8 ቢሊዮን ብር ፣ አጠቃላይ ካፒታሉ 8.7 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል። ከ533 በላይ ቅርንጫፎች እና 3.2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችም አሉኝ ብሏል። Via: ሸገር ኤፍ ኤም *** በቴሌግራም መረጃ ማቅረብ ጀምረናል ተከተሉን ❗https://t.me/fastmereja ❗https://t.me/fastmereja

480 views

Hashtags