@borkena · Post #6014 · 03/13/2026, 09:12 PM
የጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ያስነሳው ስሞታ ፤ አማራ ባንክ አተረፍኩ ማለቱ ፤ የተበከለ በርበሬ እና በድሬዳዋ የታፈነው አክቲቪስት https://youtu.be/6b1O6LsLSc0#Ethiopia#EthiopianNews#Gamo#AmharaBank#toxinberbere#Amharic#ዜና
TGINSIGHT SIMILAR POSTS
Source channel @githubtrending · Post #14821 · Jun 11
#typescript#editor#gfm#javascript#markdown#markdown_editor#milkdown#prosemirror#remarkjs#rich_text_editor#typescript#wysiwyg#wysiwyg_editor Milkdown is a flexible, open-source editor that lets you write and edit Markdown in a simple, visual way, just like you see it in apps such as Typora. It is built using powerful tools like ProseMirror and Remark, and everything in Milkdown works as a plugin, so you can add or remove features easily. You can customize its look and feel to match your app, and it supports real-time collaboration for team editing. This means you get a reliable, easy-to-use editor that fits your needs and grows with your projects, making writing and sharing documents smoother and more efficient[1][2][4]. https://github.com/Milkdown/milkdown
Search: #amharabank
@borkena · Post #6014 · 03/13/2026, 09:12 PM
የጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ያስነሳው ስሞታ ፤ አማራ ባንክ አተረፍኩ ማለቱ ፤ የተበከለ በርበሬ እና በድሬዳዋ የታፈነው አክቲቪስት https://youtu.be/6b1O6LsLSc0#Ethiopia#EthiopianNews#Gamo#AmharaBank#toxinberbere#Amharic#ዜና
@borkena · Post #6003 · 03/13/2026, 10:14 AM
አማራ ባንክበስምንት ወራት ውስጥ 1.82 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ። አማራ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት በስምንት ወራት ውስጥ 1.82 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዘገቡንና አጠቃላይ ሀብቱ 52.76 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ። በቅርቡ በአንዳንድ ሚዲያዎች የተሰራጩ ዘገባዎች የባንኩን አሁናዊ ሁኔታ ያላሳዩና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለህዝብ ያቀረቡ ሆነው ተገኝተዋል ያለው ባንኩ፤ ይህን አጋጣሚ የባንኩን እውነታዎችና ግልፀኝነት ለማሳወቅ እንደሚጠቀምበት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። እንደ ባንኩ ገለጻ፤ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ እስከ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 37.9 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የ2017 ዓ.ም አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ ለባለአክሲዮኖቹ የትርፍ ክፍፍል መፈጸሙን አስታውቋል። ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ ከ9.9 ቢሊዮን ብር በላይ ከብድር መሰብሰብ መታሉን የጠቀሰው አማራ ባንክ፤ በአሁኑ ሰዓት የተለየ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የሌለበት መሆኑን አስታውቋል። ይህን ችግር ከፈታው ከአንድ ዓመት በላይ ሁኗል ሲልም ገልጿል። ባንኩ፣ በዲጂታል አነስተኛ ብድር ከ5.1 ቢሊዮን ብር በላይ የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 90 በመቶው ለሴት ተበዳሪዎች የቀረበ መሆኑን እንዲሁም በአጠቃላይ ከ240 ሺህ በላይ ደንበኞች የዲጂታል አነስተኛ ብድር ተጠቃሚ መሆናቸውን በመግለጫው አመላክቷል። የባንኩ መግለጫ፣ የአምስት ዓመት የስትራቴጂያዊ ዕቅዱን በተግባር እያስፈጸመ እንደሚገኝ ጠቅሶ፣ የዚህ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ አካል በሆነው አዲስ መዋቅር መሰረት፣ ከየካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ የደመወዝ ስኬል ተግባራዊ መደረጉን ገልጿል። #Ethiopia#AmharaBank ##Ethiopian_news#ባንክ#አማራ_ባንክ#ዜና#ቦርከና_ዜና