TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← GitHub Trends

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @githubtrending · Post #15021 · Aug 1

#go#argocd#cloud_native#cncf#container_management#devops#ebpf#hacktoberfest#istio#jenkins#k8s#kubernetes#kubernetes_platform_solution#kubesphere#llm#multi_cluster#observability#servicemesh KubeSphere is an easy-to-use, open-source platform that helps you manage Kubernetes clusters across clouds, data centers, and edge devices from one place. It offers a friendly web interface, supports multi-cluster and multi-tenant management, and automates DevOps tasks like CI/CD pipelines. You get built-in monitoring, logging, alerting, and security features such as role-based access control. It also includes an App Store for quick deployment of applications and supports various storage and networking options. This makes managing complex Kubernetes environments simpler, faster, and more secure, saving you time and reducing operational challenges. https://github.com/kubesphere/kubesphere

Results

4 similar posts found

Search: #ethiopianelection

当前筛选 #ethiopianelection清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53906 · 04/23/2026, 03:57 PM

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ **************** ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 50.5 ሚሊዮን መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ እስከ ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሲከናወን የነበረው የመራጮች ምዝገባ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸዋል። ከሰብሳቢዋ መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በአጠቃላይ ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 5.5 ሚሊዮን የሚሆኑት "በምርጫዬ" የሞባይል መተግበሪያ (App) አማካኝነት የተመዘገቡ ናቸው። ይህ አኃዝ የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱ ለዜጎች ምቾትን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ያሳያል ተብሏል። ቦርዱ የምዝገባ ሂደቱ በሰላም መጠናቀቁን ገልጾ፣ ለሂደቱ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አካላትና ለመራጮች ምስጋና አቅርቧል። በለሚ ታደሰ #Ethiopia#EBC#EthiopianElection#NEBE#VoterRegistration#MirechayeApp

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #52008 · 03/03/2026, 12:45 PM

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸው ሦስት ዘመናዊ አማራጮች ***************** ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚከናወነው የመራጮች ምዝገባ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ባገናዘበ መልኩ በሦስት ዋና ዋና አማራጮች እንደሚከናወን ቦርዱ አስታውቋል። የመጀመሪያው አማራጭ መራጮች በተለመደው አሠራር በአካል በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ምዝገባ የሚያከናውኑበት መደበኛ ሂደት ነው። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሂደቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ 'ምርጫዬ' የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ በቅርቡ ተደራሽ ያደርጋል። መራጮች ይህንን መተግበሪያ ከፕሌይ ስቶር (Play Store) ወይም ከአፕ ስቶር (App Store) በማውረድ ባሉበት ሆነው ራሳቸውን መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን፥ ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን የዌብ አማራጭ ሊንክም በቦርዱ ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል። ሦስተኛው አማራጭ ደግሞ በምርጫ ጣቢያዎች በሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች እገዛ በታብሌት (Tablet) የሚከናወን የዲጂታል ምዝገባ ሂደት መሆኑ ተገልጿል። በምርጫ ጣቢያም ሆነ በግል ስልክ የሚከናወኑት የዲጂታል ምዝገባ አማራጮች ተፈጻሚ የሚሆኑት ቦርዱ የኢንተርኔት ተደራሽነትን መሠረት በማድረግ ይፋ በሚያደርጋቸው የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ብቻ መሆኑ ታውቋል። በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል። #Ethiopia#Election2018#DigitalRegistration#NEBE#EthiopianElection#NewsUpdate