TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← GitHub Trends

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @githubtrending · Post #15439 · Jan 27

#rust#protobuf#rust Prost is a Rust tool that turns Protocol Buffers (.proto) files into simple, readable Rust code for proto2/proto3. It keeps comments, uses Rust derives for clean types, handles packages as modules, preserves unknown enums, and serializes existing types easily—add to Cargo.toml and use prost-build in build.rs. You benefit by getting fast, safe, idiomatic Rust for efficient data serialization in gRPC/microservices, saving time on boilerplate while ensuring memory safety and performance. https://github.com/tokio-rs/prost

Results

1 similar post found

Search: #generaltadessewerede

当前筛选 #generaltadessewerede清除筛选
Borkena

@borkena · Post #5819 · 02/21/2026, 09:49 AM

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መከላከያ ወደ ትግራይ ይገባል መባሉን አስተባበለ። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ጽሕፈት ቤት ዛሬ የካቲት 14/2018 ዓ. ም ባወጣው መግለጫ፣ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል በሚገኙ የቀድሞው የሰሜን ዕዝ ካምፖች እንዲሰፍር አለመስማመቱን አስታውቋል፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ ተላልፏል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው በማለት ውድቅ አድርጓል፡፡ ባለፉት ቀናት የፌደራል መንግሥት መከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ክልል እንደሚገባ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ማሳወቁን የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተዋል። ሰራዊቱ በክልሉ የሚገኙ ካምፖችን መልሶ እንዲቆጣጠርና ኤርትራን በሚያዋስኑ ድንበሮች ላይ እንድሰፍር ትዕዛዝ ተላልፏል ተብሏል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ በጉዳዩ ላይ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ለማስፈጸም መስማማታቸውም ተመላክቷል። ነገርግን ጽሕፈት ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ዕዝ ካምፖች እንዲሰፍር ተስማምቷል መባሉን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል፡፡ ይሁን መረጃ የተሰማው የፌደራል መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኘውን ጦር አሰባስቦ ወደትግራይ እያስገባ ነው በሚባልበት ወቅት ነው። ባሳለፍነው ሳምንት የፀጥታ ችግር የተከሰተበትና የ20 ሰዎች ህይወት ያለፈበት የጋሞ ዞን ግጭት መንስዔው፣ መከላከያ ከአካባቢው ወጥቶ ወደ ትግራይ ክልል በመሄዱ መሆኑን ስማቸው እንድገለፅ ያልፈለጉ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አመራር በወቅቱ ተናግረዋል። #Ethiopia#Tigray#ENDF#AbiyAhmed#GeneralTadesseWerede