TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← GitHub Trends

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @githubtrending · Post #15607 · Apr 7

#python#ai_agents#ai_tutor#clawdbot#cli_tool#deepresearch#interactive_learning#large_language_models#multi_agent_systems#rag DeepTutor v1.0.0 is an open-source AI tutoring tool with personalized TutorBots, unified chat modes for solving problems, quizzes, research, and math animations, plus knowledge bases from your PDFs, persistent memory of your learning style, AI co-writing, and guided plans—all via easy web, Docker, or CLI setup. You benefit by getting a smart, evolving study companion that adapts to you, boosts understanding with interactive tools, and saves time on tough topics without starting over. https://github.com/HKUDS/DeepTutor

Results

2 similar posts found

Search: #irancrisis

当前筛选 #irancrisis清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53143 · 04/07/2026, 03:32 PM

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለኢራን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጡ፤ ኢራን ዜጎቿ የኃይል መሠረተ ልማትን እንዲጠብቁ ጠይቃለች ************************* የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ‘ትሩዝ ሶሺያል’ በተሰኘው የማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በአስቸኳይ ስምምነት ላይ ካልደረሰች "መላው ሥልጣኔዋ ዛሬ ምሽት ይጠፋል፤ ዳግመኛም ተመልሶ አይመጣም" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህ እንዲሆን እንደማይፈልጉ ቢገልጹም፣ የተሰጠው የሰዓታት ቀነ-ገደብ እየተጠናቀቀ በመሆኑ "ሳይሆን አይቀርም" በማለት ክስተቱ የማይቀር መሆኑን አመልክተዋል። ኢራን ስትራቴጂካዊውን የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዝጋት የዓለምን ኢኮኖሚ "አግቻለሁ" በማለት የምታደርገውን ሙከራ እንደ ትልቅ ስህተት እና የአስገዳጅነት ስልት የቆጠሩት ትራምፕ፣ ለ47 ዓመታት የዘለቀው ማስፈራራት፣ ሙስና እና ሞት ዛሬ ምሽት ያበቃል ብለዋል። አክለውም በዓለም ረጅም ታሪክ ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሆነው ውጤት ዛሬ ምሽት እንደሚታወቅ እና ምናልባትም "አስደናቂ አብዮታዊ ለውጥ" ሊመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል። ኢራን በመካከለኛ ወገኖች በኩል የቀረበላትን የጊዜያዊ ተኩስ አቁም የሰላም ዕቅድ ውድቅ ማድረጓን የገለጸች ሲሆን፣ ዘላቂ ድርድር ሊጀመር የሚችለው አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃታቸውን አቁመው ለደረሰው ጉዳት ካሳ ሲከፍሉ ብቻ መሆኑን አስታውቃለች። በተጨማሪም ማንኛውም የወደፊት ስምምነት የሆርሙዝ ወሽመጥ በኢራን ቁጥጥር ሥር ሆኖ በሚያልፉ መርከቦች ላይ ቀረጥ የመጣል መብቷን ሊያከብር እንደሚገባ የሀገሪቱ ከፍተኛ ምንጮች አመልክተዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። #Trump#IranCrisis#HormuzStrait#BreakingNews#MiddleEastConflict