TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← GitHub Trends

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @githubtrending · Post #15607 · Apr 7

#python#ai_agents#ai_tutor#clawdbot#cli_tool#deepresearch#interactive_learning#large_language_models#multi_agent_systems#rag DeepTutor v1.0.0 is an open-source AI tutoring tool with personalized TutorBots, unified chat modes for solving problems, quizzes, research, and math animations, plus knowledge bases from your PDFs, persistent memory of your learning style, AI co-writing, and guided plans—all via easy web, Docker, or CLI setup. You benefit by getting a smart, evolving study companion that adapts to you, boosts understanding with interactive tools, and saves time on tough topics without starting over. https://github.com/HKUDS/DeepTutor

Results

2 similar posts found

Search: #nationaldefense

当前筛选 #nationaldefense清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51965 · 03/01/2026, 08:49 AM

ትውልድ ከአያቶቹ ታሪክ በመማር ለሀገር ሉዓላዊነት የበኩሉን ሊወጣ ይገባል - አቶ ታገሰ ጫፎ ******************* ወጣቱ ትውልድ ከቀደምት አያት አባቶቹ ታሪክ በመማር ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡ የትናንት ጀግንነትን የሚያወሳ፣ የዛሬን ጥንካሬ የሚያሳይ እና የነገን ተስፋ የሚጠቁም የመከላከያ ሙዚየም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ተመርቆ ተከፍቷል። በምረቃው ወቅት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንደገለጹት፤ የጀግኖች አባቶችን ታሪክ የሚዘክር ሙዚየም መኖሩ ወጣቱ ትውልድ የቀደምቶችን ገድል ተረድቶ የራሱን አዲስ ታሪክ እንዲሠራ ትልቅ በር የሚከፍት ነው። ወጣቱ ትውልድ ከታሪኩ በመማር ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት መጠበቅ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። የመከላከያ ቅርስ ጥናት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ በበኩላቸው፤ ሙዚየሙ 118 ዓመታትን ያስቆጠረውን የመከላከያ ሠራዊት የጀግንነት ታሪክ ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia #DefenseMuseum#NationalDefense#History#Sovereignty

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #53153 · 04/07/2026, 07:26 PM

ሕይወቴን ለሀገሬ እሰጣለሁ፦ የኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ***************** በመካከለኛው ምስራቅ የቀጠለውን የአሜሪካና የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ፣ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ለሀገራቸው መስዋዕት ለመሆን ቃል ከገቡ 14 ሚሊዮን ኢራናውያን ጋር ተቀላቅለዋል። ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት፣ "እኔም እንደ 14 ሚሊዮኑ ኩሩ ኢራናውያን ሁሉ ሕይወቴን ለሀገሬ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ፤ ሁሌም ለኢራን እኖራለሁ" ሲሉ ገልጸዋል። ይህ የሕዝብ ንቅናቄ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ የኢራን ምክር ቤት አባላትም ንቅናቄው ሕዝቡና መንግሥት ለሀገራቸው ዳር ድንበር ያላቸውን ዝግጁነት በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በገጠርና በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ጠላትን ለመመከት እያደረጉት ያለው ተጋድሎ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል ተብሏል። ባለፈው ወር አጋማሽ የአሊ ካሜኒን መገደል ተከትሎ የተቀሰቀሰው ይህ ጦርነት፣ ኢራን በአሜሪካና በእስራኤል ላይ የአጸፋ እርምጃዎችን እንድትወስድ አድርጓታል። አሁን የተጀመረውና ቁጥሩ በየሰዓቱ እየጨመረ የሚገኘው ይህ የራስን ሕይወት ለሀገር አሳልፎ የመስጠት ዘመቻ፣ በኢራናውያን ዘንድ ያለውን ጠንካራ ብሔራዊ ስሜትና አንድነት ለዓለም ያሳየ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል ሲል ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል። #Iran#Pezeshkian#NationalDefense#MiddleEastCrisis#BreakingNews