TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← python-telegram-bot

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @pythontelegrambotchannel · Post #75 · Oct 1

Fellow programmers. Happy #hacktoberfest. This event, hosted over here, is about giving back to open source projects. We encourage you all to check it out and make some contributions. We prepared some issues by ourself, they can be found here, but fear not to take on other issues in our repo. If you have any questions, feel free to ask them away in our chats, we are there to help!

Results

3 similar posts found

Search: #digitalsafety

当前筛选 #digitalsafety清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51347 · 01/29/2026, 11:49 AM

ለዲጂታል ምዝበራ በር እየከፈተ ያለው የግንዛቤ እጥረት ************* በኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ አገልግሎቶች መስፋፋታቸውን ተከትሎ፣ ከግንዛቤ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችና ምዝበራዎች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑ ተገለጸ። ዜጎች ለማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ለባንክ መተግበሪያዎቻቸው የሚሰጡት የደህንነት ጥንቃቄ አናሳ መሆን ለጥቃት ተጋላጭነታቸውን እንዳሰፋው ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር መከላከል ዳይሬክተር መሐመድ ፈረጃ ተናግረዋል። በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ መድረኮች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ዜጎች ለዲጂታል ደህንነታቸው የሚሰጡት ትኩረት አናሳ መሆን ለምዝበራው ዋነኛ መንስኤ መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ ለኢቲቪ ዜና የገለጹት። ጥቃቶቹ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጥቅሞችን ባነገቡ አካላት የሚሰነዘሩ ሲሆን፣ ድንበር ተሻጋሪ መሆናቸው ደግሞ ወንጀለኞቹን በሕግ ቁጥጥር ስር ለማዋልና ለተጠቂዎች ፍትሕ ለማሰጠት ተግዳሮት ሆኗል። ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ዜጎች መተግበሪያዎችን በየጊዜው ካለማሻሻል ባለፈ፣ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) አለመጠቀማቸው ለጠላፊዎች ትልቅ እድል እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል። ተጠቃሚዎች ከምዝበራ እንዲጠበቁ አስተዳደሩ የሚከተሉትን ነጥቦች እንዲተገብሩ አሳስቧል፦ • የምስጢር ኮድ ጥንቃቄ፦ በስልክ የሚደርስ ማንኛውንም ምስጢራዊ ኮድ (OTP) ለማንም አካል አለመስጠት። • አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት፦ በሽልማትና በተለያዩ ስሞች የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን ፈጽሞ አለመክፈት። • የሁለትዮሽ ማረጋገጫ፦ በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫን (Two-Step Verification) ተግባራዊ ማድረግ። • ሪፖርት ማድረግ፦ አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሱ ወዲያውኑ ሪፖርት እና ማገድ (Block) ማድረግ። አፎሚያ ክበበው #EthiopianBroadcastingCorporation#CyberSecurity#Ethiopia#INSA#DigitalSafety