TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← python-telegram-bot

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Find similar content

Source channel @pythontelegrambotchannel · Post #89 · Oct 7

The v13 release is not just a release either, it is also our official announcement of participation in the annual #hacktoberfest. 💻🥨 We know that we're a few days late to the party, but v13 had to get ready before. 😉 This year, the fest is opt-in for projects and we definitely want to opt into taking part in this great event! If you ever thought about starting coding or giving back to your favourite open source repositories, now is the time! Head over to the hacktoberfest website to learn more about it. We already prepared some issues on our repositories and aim towards opening more issues for starters, but feel free to begin a hunt for improvements and fixes by yourself!

Results

1 similar post found

Search: #gediontimotheos

当前筛选 #gediontimotheos清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51995 · 03/02/2026, 03:05 PM

ሰርጌይ ላቭሮቭ ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ******************** የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ የዓድዋ ድል በአፍሪካ ታሪክ አንዲት ሀገር በቅኝ ገዥ ኃይል ላይ የተቀዳጀችው የመጀመሪያው ድል በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጽዕኖ የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ድሉ የኢትዮጵያውያንን የጽናት መንፈስ ከማረጋገጡ ባለፈ በመላው አፍሪካ ለሚካሄዱ የነፃነት ትግሎች መነሻ መሆኑንም አክለዋል። ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ የወዳጅነት ታሪክ እንዳላቸው የጠቀሱት ሰርጌይ ላቭሮቭ፤ በየተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ፍትሃዊ የዓለም ሥርዓት እንዲኖር በጋራ እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ እና በባህል ዘርፎች ትብብሮች እያደጉ መሆናቸውን መግለጻቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታን ጨምሮ፣ የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታልን መልሶ መገንባት እና የጋራ ባዮሎጂካል ምርምር ማዕከል መመሥረት ዋና ዋናዎቹ የትብብር ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል። #EBC#Ethiopia#Russia#Adwa130#Diplomacy#SergeyLavrov#GedionTimotheos#BRICS