TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← OnePlus Guide

TGINSIGHT SIMILAR POSTS

Trouver du contenu similaire

Chaîne source @OnePlusGuide · Post #2221 · 31 août

~ ANDROID Q DP5 PER OP7 E OP7PRO ~ #OXYGEN#Q#BETA#OP7#OP7PRO Sistema: • Miglioramento delle funzioni di sistema • Aggiunte le gestures OnePlus • Basato su Android 10 Beta 6 Problemi noti: • Problemi di compatibilità con le app • Possibilità di lag e altri problemi • Problemi con Google Pay Ricordo che OnePlus potrebbe rilasciare OxygenOS 10 il 3 settembre, ma trattandosi solo di un rumor non dateci troppo peso almeno non vi scandalizzerete se non sarà così Pierre

Résultats

5 posts similaires trouvés

Recherche : #houseoffederation

当前筛选 #houseoffederation清除筛选
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow · Post #51894 · 23/02/2026 07:28

ለክልሎች የሚተላለፍ የጋራ ገቢ መጠን እያደገ መጥቷል - አቶ አገኘሁ ተሻገር *************** ለክልሎች የሚተላለፈው የጋራ ገቢ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ። ምክር ቤቱ በገቢዎች ሚኒስቴር እና በማዕድን ሚኒስቴር ተሰብስቦ በቀመሩ መሠረት የሚተላለፈው የክልሎች ድርሻ በትክክል መድረሱን ለማረጋገጥ በተከናወነ የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት ግኝት ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፤ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚሰበሰበው የጋራ ገቢ ለክልሎች ለማስተላለፍ የሚሰላበት ቀመር ማሻሻያ እንደተደረገበት አስታውሰዋል። ከማሻሻያው አስቀድሞ ክልሎች ከጋራ ገቢ የሚያገኙት ድርሻ 4.2 ቢሊዮን ብር ብቻ እንደነበረ ጠቁመው፤ አሁን ላይ መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልጸዋል። እንደ አፈ-ጉባኤው ማብራሪያ፣ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ ከጋራ ገቢ ለክልሎች የሚከፋፈለው ድርሻ 91.73 ቢሊዮን ብር ደርሷል። በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ከ71 ቢሊዮን ብር በላይ ማከፋፈል መቻሉ በመድረኩ ተመልክቷል። የውይይት መድረኩ በኦዲት ግኝት ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር በመምከር፣ የሀብት ክፍፍሉ ፍትሐዊነትና ሕጋዊነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚቀጥል ታውቋል። በሳምሶን ገድሉ #EthiopianBroadcastingCorporation#Ethiopia#HouseOfFederation#BudgetAllocation#RegionalRevenue

Borkena

@borkena · Post #5832 · 23/02/2026 10:56

የፌደሬሽን ምክርቤት አከራካሪ የምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው እንዲቆዩ ወሰነ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አወዛጋቢ ቦታዎች ላይ ውሳኔ አሳልፏል። የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል አከራካሪ በሆኑ አምስት የምርጫ ክልሎች ላይ ልዩ ውሳኔ ማሳለፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ምክር ቤቱ ለቦርዱ በላከው ደብዳቤ መሠረት ሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም አፍላ፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ የይገባኛል ጥያቄያቸው እልባት እስኪያገኝ ድረስ ከትግራይ ክልል ውጭ ሆነው እንዲቆዩ ወስኗል። በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም ለፌዴራል ብቻ በቀጥታ ድምፅ እንዲሰጡ ይደረጋል ብሏል። በአካባቢዎቹ ያለው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት እልባት እስኪያገኝ ድረስ፣ የክልል ምክር ቤት ምርጫ ለጊዜው ተራዝሞ ወደፊት እንዲካሄድ መወሰኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፣ ከጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚያካሂደው የመራጮች ምዝገባ ይህንኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ተፈጻሚ ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። #​​Ethiopia #AddisAbaba#ElectoralBoardofEthiopia#news#ዜና#HouseofFederation

Borkena

@borkena · Post #5975 · 11/03/2026 14:35

ክሱን በፍቃዳቸው አቋረጡ። እነ አቶ ጌታቸው ረዳ በምርጫ ቦርድ ላይ የመሰረቱትን ክስ አነሱ የዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ላይ መስርተውት የነበረውን ክስ በገዛ ፈቃዳቸው ማንሳታቸውን ለፍርድ ቤት አስታውቀዋል። ​ ከሳሾች ክሱ አሁን ባለው ሁኔታ ውጤት እንደማያመጣ በማመናቸው በፈቃዳቸው አንስተዋል ተብሏል። ክሱ በመነሳቱ ምክንያት ቀደም ሲል በቦርዱ ውሳኔ ላይ ተጥሎ የነበረው የጊዜያዊ እገዳ ትዕዛዝ ተሰርዟል። ​ በዚህም መሰረት የምርጫ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ በቀጥታ ተፈጻሚ ይሆናል። ​​#Ethiopia#AddisAbaba#Ethiopian_news#news#houseoffederation#GetachewReda#NBE#ዜና#ምርጫ#ጌታቸውረዳ