Įrašo turinys
የቲክቶክ አካውንታችንን እንዴት ከGoogle authenticator ጋር እንዴት እናገናኛለን? በመጀመሪያ ይህንን ሊንክ በመንካት የጎግል authenticator መተግበሪያን ማውረድ። https://play.google.com/store/apps/details?id=com.google.android.apps.authenticator2 ▣ በመቀጠልም TikTok አካውንታችን ላይ በመግባት እና ሶስት ነጥብጣቡን በመንካት Settings and privacies ከዚያም Security & Permissions ▣ 2-step Verification የሚለውን ስንመርጥ Authenticator የሚል አማራጭ እናገኛለን። copy key የሚለውን በመንካት ሊንኩን copy ማድረግ። ▣ ወደ google Authenticator በመሄድ add የሚለውን መንካትና enter a setup key የሚለውን መምረጥ። ▣ code name የሚለውን tiktok ማለት ትችላላችሁ your kay የሚለው ላይ ደግሞ ከ tiktok copy ያደረጋችሁትን key paste ማድረግ። type of key የሚለውን ደግሞ time based አድርጉት። ▣ በዚህ ጊዜ Google Authenticator በየ30 ሰከንዱ የሚለዋወጥ code generate ማድረግ ይጀምራል። ከዚያም TikTok ላይ Next የሚለውን button መንካት Authenticator generate ያደርገውን code ማስገባት። ይህን በትክክል ካደረጋችሁ TikTok አካውንታችሁና Authenticator app በትክክል connect ሆኗል ማለት ነው። ይህም አካውንታችሁ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል።