TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Turinys
Įrašo turinys
ለቴሌግራም አካውንታችሁ የDevice passcode ትጠቀማላችሁ? Local device passcode ለቴሌግራም አካውንታችሁ የማትጠቀሙ ከሆነ ►ስልካችሁ በአጋጣሚ ብትሰረቁ ቀጥታ Telegram አካውንታችሁን ሰዎች access ሊያደርጉት ይችላሉ። ►የቅርብ ሰው ወይም ጓደኛ ድንገት ስልካችሁን አንስቶ ሚስጢራችሁን ሊያይ ይችላል። ስለዚህ On ለማድረግ ►Settings ላይ ከገባችሁ በኋላ privacy and security ከዛ Passcode Lock የሚለውን መርጣችሁ ባለ 4 ድጅት ቁጥር በማስገባት On አድርጉት። ➡ አስታውሱ ►አንዴ On አድርጋችሁት ፓስኮዱን ከረሳችሁት ግን እንደገና ለመግባት አፕሊኬሽኑን ከስልካችሁ ላይ uninstall አድርጋችሁ እንደገና reinstall ማድረግ ይጠበቅባችኋል። እዚህ ጋ uninstall ከማድረጋችሁ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባችኋል። አካውንታችሁ ሌላ device ላይ already login የተደረገ መሆን አለበት። ካልሆነ አካውንታችሁን premium ካላደረጋችሁ በስተቀር login code አይልክላችሁም። ►Passcode እንደምትጠቀሙት device የተለያየ ነው። ለምሳሌ ተመሳሳይ አካውንት በስልክና ኮምፒውተር login ብታደርጉ device ኮዳቸው ይለያያል። #telegram