TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Elyas tube
Elyas tube avatar

TGINSIGHT POST

Post #23

@ethiotech20

Elyas tube

Peržiūros33Peržiūrų skaičius
Paskelbta09-042025-09-04 15:39
Turinys

Įrašo turinys

iPhone 17 በቅርቡ ሊለቀቅ ነው። ካንዳንድ ምንጮች እንዳገኘነው መረጃ Apple iPhone 17 የተሰኘ የስልክ ሞዴሉን ለመልቀቅ ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርቶታል። መደበኛው iPhone 17 ላይ በርካታ ማሻሻያዎች ሊደረግበት የሚችል ሲሆን ከነዚህም መካከል 6.3 ኢንች ስክሪን፣ 120Hz Display እንዲሁም በአረንጓዴ እና በሐምራዊ ቀለም ሊቀርብ ይችላል። iPhone 17 pro ከጀርባው በኩል ከሌሎቹ ሊለይ ይችላል የተባለ ሲሆን ይህም ከጀርባ ያሉት ካሜሪዎች በአራት መዐዘን ፍሬም ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ።እንዲሁም 128GBን በማስቀረት ከ256GB ጀምሮ የstorage አማራጭ ሊኖረው ይችላል። iPhone 17 pro max ከፍተኛ የባትሪ መጠን እና በጣም ቀጠን ያለ body ሊኖረው እንደሚችል ተገምቷል። በተጨማሪም እስካሁን ካሉት የiPhone ስልኮች ቀጭኑ ሊሆን ይችላል የተባለው iPhone Air ነው። ይህ ስልክ 5.5mm ውፍረት ሊኖረው ይችላል። ዋጋቸውም መደበኛው iPhone 17 ወደ $800 ገደማ፣ iPhone 17 pro $1025 አካባቢ፣ iPhone 17 pro max ደግሞ ወደ $1250 አካባቢ እና iPhone 17 $950 ገደማ ይገመታል። ይሁን እንጅ እስካሁን ድረስ Apple ስለስልኩ ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።