TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Elyas tube
Elyas tube avatar

TGINSIGHT POST

Post #27

@ethiotech20

Elyas tube

Peržiūros34Peržiūrų skaičius
Paskelbta09-042025-09-04 16:41
Turinys

Įrašo turinys

እንዴት የላፕቶፓችንን የባትሪ ይዞታ ማወቅ እንችላለን? ላፕቶፕ በምትገዙበት ጊዜ የላፕቶፓችሁ ባትሪ ሲመረት የነበረው እና አሁን ላይ ያለውን የባትሪ ይዞታ/መጠን ቼክ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ይህንንም ለማድረግ በመጀመሪያ windows+R ተጭነን የሚመጣልን textbox ላይ cmd ብለን እንፅፋለን። በመቀጠልም፦ powercfg /batteryreport ብለን በመፃፍ enter እንነካለን። ከዚያም እንደዚህ አይነት/ተቀራራቢ/ ፅሁፍ ይመጣልናል። battery life report saved to file path C:\Users\yourname\battery-report.html . በመጨረሻም start ብለን ፅፈን ከጎኑ የፋይሉን path ብቻ copy አድርገን paste እናደርጋለን። ለምሳሌ፦ start C:\Users\yourname\battery-report.html አሁን ስለ ላፕቶፓችን የተለያዩ መረጃዎችን እናገኛለን። ትንሽ ዝቅ እንዳደረግን DESIGN CAPACITY እና FULL CHARGE CAPACITY የሚሉ ምርጫዎች የምናገኝ ሲሆን DESIGN CAPACITY ከሚለው አጠገብ ያለው ባትሪው ሲመረት ያለው አቅም በmWh ሲሆን ከFULL CHARGE CAPACITY አጠገብ ያለው ደግሞ አሁን ላይ ያለው የባትሪው የመያዝ አቅም በmWh ነው።