TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
← Elyas tube
Elyas tube avatar

TGINSIGHT POST

Post #29

@ethiotech20

Elyas tube

Peržiūros42Peržiūrų skaičius
Paskelbta09-052025-09-05 09:44
Turinys

Įrašo turinys

#እንድታውቁት ቴሌግራም ላይ ሁለት ተመሳሳይ የሚመስሉ ነገር ግን የተለያዩ settings አሉ። የመጀመሪያው settings> privacy and security ውስጥ ከገባን በኋላ የምናገኘው Delete my account ... if away for የሚለው ሲሆን ይህም ወደ ቴሌግራም ለምን ያህል ጊዜ ካልተመለስን አካውንታችንን Delete እንዲሆን የምናስተካክልበት ሲሆን አሁን ላይ ከፍተኛ የጊዜ ገደቡም 24 ወር ነው። ሌላኛው ደግሞ settings> Devices ውስጥ ስንገባ የምናገኘው Automatically terminate old sessions ... if inactive for የሚለው እና አንድ device ላይ ለምን ያህል ጊዜ ቴሌግራም ሳንጠቀም ከቆየን አካውንቱን ከዛ device ላይ ብቻ ያጥፋው የሚለውን የምናስተካክልበት ነው። አሁን ላይ ይህም ከፍተኛው ማድረግ የምንችለው የጊዜ ገደብ 12 ወር ነው።