TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Turinys
Įrašo turinys
ሩዋንዳ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ራሱን በራሱ ማብረር የሚችል የአየር ላይ ኤሌክትሪክ ታክሲ አስተዋወቀች። ሩዋንዳ self-flying ወይም ራሳቸውን በራሳቸው የሚያበሩ የአየር ላይ ታክሲ በመጀመር ከአፍሪካ ፈር ቀዳጇ ሀገር መሆን ችላለች። ከChina Road and Bridge Corporation እና EHang Holdings Limited ጋር በመተባበር እንደተሰራች የተገለፀችው ይህቺ የአየር ላይ ታክሲ ኪጋሊ ላይ በተዘጋጀው የAviation Africa 2025 ፕሮግራም ላይ ለእይታ ቀርባለች። EH216-S የሚል ስያሜ ሲሰጣት ከፍተኛ ፍጥነቷ 130 ኪሎ ሜትር በሰአት እንዲሁም ለ35 ኪሎ ሜትር ወይም ለ21 ደቂቃ መብረር ትችላለች ተብሏል። ሹፌር አልባ የሆነችውና ከelectrically vertical takeoff and landing (eVTOL) የኤርክራፍት ቤተሰብ የምትመደብ ሲሆን ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና የአቪዬሽን ባለሙያዎች በተገኙበት በኪጋሊ ሰማይ ላይ መብረር ችላለች።