TGTGInsighttelegram intelligenceLIVE / telegram public index
Turinys
Įrašo turinys
በቀይ ባህር ስር የተዘረጋው የኢንተርኔት ገመድ በመቆረጡ ምክንያት Azure የተሰኘው የmicrosoft platform ችግር እንደገጠመው ተነገረ። Microsoft Azure የMicrosoft cloud platform ሲሆን ለድርጅቶች እና ለግለሰቦችም የተለያዩ የcloud ሰርቪሶችን ያቀርባል። Microsoft እንደገለፀው በቀይ ባህር ላይ የሚገኙ የኢንተንኔት ኬብሎች በመቆረጣቸው ምክነያት azure የፍጥነት መቀነስ ችግር አጋጥሞታል። ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚያልፈው እና ወደ አውሮፓ እና እስያ የሚሄደው ትራፊክ ሳይቆረጥ እንዳልቀረ የተገለፀ ሲሆን ጥቃቱን ማን እንደፈፀመው ግን በውል አልተገለፀም። እንደ ኔትብሎክስ ዘገባ ከሆነ ከmicrosoft በተጨማሪ ህንድ እና ፓኪስታንም የኢንተርኔት መቆራረጥ እንደገጠማቸው ተጠቅሷል